ግልጽ ደብዳቤ በዐብይ አሕመድ ላይ ተስፋችሁ ላልተሟጠጠ አማሮች – መስፍን አረጋ

anti climax in a crisis by gregory copley

 1. ይህ ግልጽ ደብዳቤ ተደራሽነቱ ዐብይ አሕመድን በተመለከተ አሁንም ድረስ ተስፋቸው ላልተሟጠጠ አገር ወዳድ ቅን አማሮች፣ በተለይም ደግሞ ዐብይ አሕመድ ለአማራ ሕዝብ የችግር ምንጭ እንጅ የችግር መፍትሄ እንዳልነበረ፣ እንዳልሆነና መቸም ሊሆን እንደማይችል ገሃዱን ሐቅ ማየት ላልቻሉ፣ ወይም ደግሞ ዓይኔን ግንባር ያርገው በማለት ማየት ላልፈለጉ አማሮች ነው፡፡  ይልቁንም ደግሞ የአማራ ሕዝብ በሕልውናው ላይ የመጣበትን ትልቅ አደጋ መመከት የሚችለው በአማራነቱ በመደራጀት ብቻና ብቻ መሆኑን ሳይገነዘቡ፣ በኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ ሙሉ በሙሉ ተማምነው ላታቸውን እውጭ በማሳደር እየታረዱ ወይም ደግሞ ወገናቸውን እያሳረዱ ላሉ የአማራ በጎች ነው፡፡
 2. ዐብይ አሕመድ የጦቢያ መሪ እስከሆነ ድረስ በሱ ዘመን በአማራ ሕዝብ ላይ ለተፈጸሙ፣ እየተፈጸሙ ላሉና  ወደፊትም ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ዋናው ተጠያቂ እሱ ራሱ ነው፡፡   ስለሆነም፣ ዐብይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ ከእስካሁን ከፈጸማቸውና ካስፈጸማቸው ወንጀሎች በላይ ምን ቢፈጽምና ቢያስፈጽም ነው፣ እናንተ አማሮች በዐብይ አሕመድ ላይ ያሳደራችሀት ተስፋ ተሟጦ የሚያልቀው?
 3. ዐብይ አሕመድ ባለፉት ሦስት ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመውና ያስፈጸመው ወንጀል፣ ወያኔ በሃያ ሰባት ዓመታት ባማራ ሕዝብ ላይ ከፈጸመውና ካስፈጸመው ወንጀል በቁነናም በዝግነናም አያሌ እጥፍ አይበልጥም ወይ?  የዐብይ አሕመድ የመከራ ዘመን፣ የጣልያንን የመከራ ዘመን ከሕጻን ጨዋታ የሚያስቆጥር አይደለም ወይ?  ኦሮሞ ሲያነጥሰው ጉንፋን የሚይዘው ዐበይ አሕመድ፣ ኦነግ ሸኔ የተጫወተባትን አጣየን እስካሁን ድረስ ዞር ብሎ አለማየቱ ብቻ የለየለት ፀራማራ ኦነጋዊ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ አያሳይም ወይ?
 4. ያማራ ፋኖ፣ ሚሊሻና ልዩ ኃይል በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ድባቅ ተመትቶ የነበረው ወያኔ ባጭር ጊዜ ውስጥ አንሰራርቶ ያማራን ሕዝብ ፍዳ ለማስበላት የበቃው በዐብይ አሕመድ ጠቅላይ አዛዥነት፣ በብርሃኑ ጁላ ኢታማዦር ሹምነት፣ በቀንዓ ያደታ መከላከያ ሚኒስተርነት፣ በይልማ መርዳሳ አየር ኃይል አዛዥነት በሚመራው መከላከያ ውስጥ የተሰገሰጉት ፀራማራ ኦነጋውያን በሚፈጽሙት አሻጥርና ደባ አይደለም ወይ?  ዐብይ አሕመድ ሆን ብሎ መንገድ ከፍቶለት እንጅ ወያኔ ከተንቤን እመር ብሎ ሐይቅ በመድረስ የደሴን በር ለማንኳኳት እንዴት ይቻለዋል?  አፋር ክልል ላይ ወያኔን የሚያደባየው የይልማ መርዳሳ አየር ኃይል፣ አማራ ክልል ላይ ዝር የማይለው ለምንድን ነው?
 5. የዐብይ አሕመድ የትግራይ ዘመቻ ዓላማ ወያኔን ለማጥፋት ሳይሆን፣ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በሚከፍለው ከፍተኛ መስዋዕትነት አማካኝነት ኦነግ በወያኔ ላይ ሙሉ የበላይነት ተቀዳጅቶ፣ ወያኔን የፀራማራ አጀንዳው አስፈጻሚ ሎሌ ለማድረግ የመሆኑ ጉልህ ሐቅ የሚያንቃችሁ መቸ ነው?  በሌላ አባባል የዐብይ አሕመድ ዓላማ ወያኔን ለኦሮሞ የማያሰጋ፣ አማራን የሚወጋ ታዛዥ አሽከር ለማድረግ መሆኑን የምትረዱት መቸ ነው?
 6. ዐብይ አሕመድ ቢያደፋፍራት እንጅ፣ አሜሪቃ የዲፕሎማሲ ደንቦችን በመጣስ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብታ ያማራ ልዩ ኃይል ከወልቃይትና ከራያ ይውጣ ለማለት እንዴት ትደፍራለች?  ወያኔና ኦነግ በዘር ማጥፋት ወንጀል ባልተከሰሱበት ምድር ላይ ያማራ ልዩ ኃይል ያለ ኃጢያቱ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ለማድረግ ዐብይ አሕመድ ካንቶኒ ብሊንከን ጋር የሚመሳጠረው ለምን ይመስላችኋል?  ያማራ ክልል አመራሮችን ሄግ ትቀርበላችሁ እያለ በማስፈራራት ሲጠራቸው አቤት፣ ሲልካቸው ወዴት የሚሉ ፍጹም አሽከሮቹ እንዲሆኑለት ለማድረግ አይደለምን?
 7. አሜሪቃ የአማራን ልዩ ኃይል በዘር ማጥፋት ወንጀል ከመውቀሷ በፊት፣ በዐብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ የአማራ ልዩ ኃይል ሰሜን ሸዋ ላይ የዘር ማጥፈት ወንጀል ፈጽሟል የሚል ውንጀላ በመግለጫ መልክ መጋቢት 6 (2013) ላይ ማውጣቱን ለምን ትረሳላችሁ?  በማግስቱ ደግሞ ይሄው የኦነጋውያን የሐሰት ውንጀላ፣ የፓርላማን ደንብ በጣሰ መልኩ ባብይ አህመድ የይስሙላ ፓርላማ ውስጥ ቃል በቃል እንዲነበብና ለመላው የኦትዮጵያ ሕዝብ በቀጥታ እንዲተላለፍ መደረጉን ለምን ዘነጋችሁት?
 8. የዐብይ አሕመድ ዋና አማካሪ፣ አዲሳባን የኦሮሞና የኦሮሞ ብቻ ለማድረግ ምሎ የተገዘተው፣ የኦነጉ መሥራች፣ ቀንደኛው ፀራማራ ዲማ ነገወአይደለም ወይ?  ዐብይ አሕመድ ፊንፊኔ ኬኛ እያለ አዲሳባን ቢያስውብና ቢያሳምር እናንተ አማሮች የምታመሰግኑት ለምንድን ነው?  የደቡብ አፍሪቃ ነጮች ደብረዮሐንስን (Johannesburg) ከዓለም ውብ ከተሞች ተርታ ስላስቀመጧት መመስገን ነበረባቸው እንዴ?  ጣልያንስ ቢሆን ወረራውንና ምዝበራውን ለማሳለጥ ሲል ብቻ በመከራ ዘመን ለሠራቸው መንገዶች ሊመሰገን ይገባዋል እንዴ?
 9. ዐብይ አሕመድ ጦቢያን በሚያንቆለጳጵስባቸው ባዶ ንግግሮቹም ሆነ እነ ዳንኤል ክብረት በሚጽፉለት አማራን መፎገሪያ ጽሑፎች እናንተ አማሮች ዐብይ አሕመድን አሻጋሪ የምትሉት ለምንድን ነው?  የነዚህ ንግግሮችና ጽሑፎች ብቸኛ ዓላማ የአማራን ሕዝብ ለማሻገር ሳይሆን፣ በሰበካ አስክሮ ለሃቹ ለመቅበር እንደሆነ ጠፍቷችሁ ነውን?  አፈቅርሻለሁ እያለ የሚገድል ወይም የሚያስገደል ሰው፣ ነፍሰ ገዳይ እንጅ አፍቃሪ ይባላል ወይ?
 10. ዐብይ አህመድን ማመስገን ማለት በማር የተለወሰ መርዝ የሚሰጥን ሰው ለማሩ ማመስገን ማለት አይደለም ወይ?መርዝም ቢኖረው፣ ለማሩ ሲባል የግድ መመስገን አለበት ከተባለ ደግሞ ኢቲቪ፣ ኢሳት፣ ዜና ቲዩብ … ቀን ከሌት የሚያመሰግኑት አይበቃውም ወይ?  አሁን፣ አሁን ደግሞ ያንዳርጋቸው ጽጌ ሚዲያወችና ባልደረቦች ብቸኛው አማራጫችን ዐብይ አሕመድ ነው የሚሉበት አንዱ ምክኒያት፣ ዐብይ አሕመድ እንዳይታጠቅና ራሱን እንዳይከላከል ያደረገው የአማራ ሕዝብ በአነግና በወያኔ መጨፍጨፉ የዩቲዩብ ገበያቸውን ስላደራላቸው አይመስላችሁም ወይ?  በደቂቃ በሺ የሚቆጠሩ ተመልካቾችን የሚያፈራላቸው ጦርነት በአማራ አሸናፊነት በፍጥነት ቢቆም ጥቅማቸው ስለሚቀርባቸው፣ የጦርነቱን መቀጠል አጥብቀው የሚፈልጉት አይመስላችሁም ወይ?  መቶ ሚሊዮን ሕዝብ በሚኖርባት አገር አንድን ግለሰብ ብቸኛ አማራጭ ማለት ድፍን ጦቢያን መሳደብ አይደለም ወይ?  
 11. ድፍን የጦቢያ ሕዝብ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ በነቂስ ሲደግፈው ጦቢያዊነትን መርጦ በጦቢያ አልጋ ላይ እድሜ ልኩን ሊተኛበት ሲችል፣ የኦነጋዊነት ዐመዱን የመረጠው ዐብይ አሕመድ፣ አብዛኛው የጦቢያ ሕዝብ ዓይንህን ላፈር ባለው በዚህ ፈታኝ ወቅት ጦቢያዊነትን ይመርጥ ይሆናል ብላችሁ እንዴት ታስባላችሁ?  የዐብይ አሕመድ ነገር ያህያ ሥጋ ባልጋ ሲሉት ባመድ መሆኑ ጠፍቷችሁ ነው ወይ?ዐብይ አሕመድ ይሄን ያድርግ፣ ያን አያድርግ እያላችሁ አውቆ የተኛውን ኦነጋዊ ለመቀስቀስ መሞከራችሁን የምታቆሙት መቸ ነው?
 12. ዐብይ አህመድ የጭቆናን ምንነት በቅጡ ሊረዳ በማይችልበት ለጋ እድሜው “ያማራ ጨቋኞችን” ለመታገል ጫካ ገብቶ የወያኔን ጡት እየጠባ ባማራ ጥላቻ ተመርዞና ተሰቅዞ ያደገ፣ አማራዊ ናት የሚላትን ጦቢያን አፈራርሶ በሷ መቃብር ላይ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo empire) ለመመሥረት ቆርጦ የተነሳ አክራሪ ኦነጋዊ ነው፡፡  ይልቁንም ደግሞዐብይ አሕመድ ማለት አክራሪ ኦነጋዊ እንዲሆን በወያኔ ተጠፍጥፎ የተሠራ የወያኔ ሥሪት ወይም ቅጥቅጥ ነው፡፡    የለየለት ፀራማራ ለመሆኑ ደግሞ ጦቢያን ከሚያሞካሽባቸው ዲስኩሮቹ ጋር ሐራምባና ቆቦ (እንጦጦና የረር) የሆኑት ኦነጋዊ ተግባሮቹ ሊስተባበሉ የማይችሉ ማረጋገጫወች ናቸው፡፡  ዐብይ አህመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ፣ አፉና ምግባሩ ሓራምባና ቆቦ፡፡
 13. ዐብይ አሕመድ ካማራ መወለዱና አማራ ማግባቱ አክራሪ ፀራማራ ከመሆን አያግደውም፡፡   ሙሉ ኦሮሞ ያልሆነው ዐብይ አሕመድ የኦሮሞ አክራሪነትን ስለመረጠ፣ የእናቱ አልኦሮሞ(non-oromo) መሆን አክራሪነቱን ያከርረዋል እንጅ አያረግበውም፡፡  ያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ የዚያ ብሔር ጽንፈኛ ከሆነ፣ በብሔር አባልነቱ ሊጠረጠር እንደማይገባው በግልጽ ለማስመስከር ሲል ያማያደርገው ድርጊት የለም፡፡  ለዚህ ደግሞ የግራኝ አሕመድ አባት የተዋህዶ ካህን ነበር የሚባለውን አፈታሪክ ጨምሮ አያሌ ተጨባጭ ምሰሌወችን መጥቀስ ይቻላል፡፡  ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡  ጌታቸው አሰፋ በላኤአማራ የሆነበት አንዱ ምክኒያት አባቱ አማራ ቢሆኑም ‹‹ከሙሉ ትግሬወች›› በላይ አማራጠል መሆኑን ለማስመስከር ነበር፡፡  ጌታቸው ረዳ የአማራን ሕዝብ ቀን ከሌት የሚዘልፈው፣ ባማራነቱ እንደሚጠረጠር ስለሚያውቅ ጥርጣሬውን ለማጥፋት ሲል ነው፡፡ (በሌላ በኩል ግን ደብረጽዮን በትግሬነቱ ስለማይጠረጠር፣ ትግሬነቱን ለማስመስከር አማራን መሳደብ አያስፈልገውም)፡፡  አብዛኞቹ ያሜሪቃ ነጭ ልዕለኛወች (white supremacists) አንግሎ-ሳክሶኖች ከነጭ የማይቆጥሯቸው የደቡብና የምሥራቅ አውሮጳ መደዴወች ወይም ደግሞ የጥቁር ደም አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ግማሽ ነጮች ናቸው፡፡  ሙሉ ጥቁር ነን ከሚሉ አሜሪቃውያን ይልቅ፣ የነጭን ዘረኝነት በጽኑ የታገሉት እነ ፍሬድሪክ ዳግላስ (Frederick Douglass)፣ ዊልያም ድቧ (W.E.B Du Bois)፣ እና ማልኮም ኤክስን (Malcolm X) የመሳሰሉ ግማሽ ጥቁሮች ነበሩ፡፡  ዐብይ አህመድ ደግሞ ግማሽ አማራ ከመሆኑ በተጨማሪ ካማራ ጋር የተጋባ በመሆኑ፣ ፀራማራ ልሁን ካለ ፀራማራነቱ ከጌታቸው አሰፋና ከጌታቸው ረዳ ቢብስ እንጅ አያንስም፡፡
 14. ዐብይ አህመድ፣ ፀጋየ አራርሳና የመሳሰሉት ግማሽ አማራ አነጋውያን በኦሮሞነታቸው ስለሚጠረጠሩ፣ ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቁና እያንዳንዷ ድርጊታቸው ባጉሊ መነጽር እንደምትመረመር አሳምረው ያውቃሉ፡፡  ትንሽ ቢሳሳቱ ግዙፍ ውለታቸው መና ቀርቶ ከሃዲወች እንደሚባሉ ነጋሪ አያስፈልጋቸውም፡፡  እስከጣፈጡ ድረስ ተላምጠው የሚተፉ አገዳወች እንደሆኑ በደንብ ያውቃሉ፡፡  ስለዚህም እነዚህ ግማሽ ኦሮሞወች፣ በኦሮሞነታቸው ሊታሙ እንደማይገባቸው ለማረጋገጥ ሲሉ ብቻ ከሙሉ ኦሮሞወች የጸነፉ ጽንፈኞች መሆን አለባቸው፡፡  ከለማበት የተጋባበት፡፡ዐብይ አሕመድ እናቴ አማርኛ የማታውቅ ኦሮሞ ናት፣ ኦሮሙማነቴን ማንም አይነጥቀኝም … እያለ ሳይጠይቁት የሚለፈልፈው ከዚህ ጭንቀቱ የተነሳ ነው፡፡
 15. ዐብይ አህመድ ለኦነግ ዓላማ መሳካት ሲል ማናቸውንም ጭራቃዊ ድርጊት ለማድረግ ቅንጣት እንደማያቅማማ በስካሁን ድርጊቶቹ በግልጽ ቢያሳይም፣ ግማሽ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ኦነጋውያን መቸም ቢሆን በሙሉ ልብ አያምኑትም፡፡  ስለዚህም ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ከፈለገ ትናንት ካደረገው የከፋ ዛሬ ማድረግ አለበት፡፡  ስለዚህም አማሮችን በተመለከተ የበለጠ እና የበለጠ ጭራቅ እየሆነ ይሄዳል፡፡  ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አህመድ በማንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት (vicious circle) ውስጥ የገባ የኦነግ አውሬ ነው፡፡  ካዟሪቱ ነጻ የሚያወጣው ደግሞ ሞቱ ብቻ ነው፡፡  በኦሮሞነቱ ኦሮሞወች ሙሉ በሙሉ ሚያምኑትለማ መገርሳ በዐብይ አሕመድ ወንበር ላይ ቢቀመጥ፣ ዐብይ አሕመድ በአማራ ላይ የሚጨክነውን ያህል እንደማይጨክን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፣ ምክኒያቱም ኦሮሞነቱን ለማስመስከር ዐብይ አሕመድ እስከሄደው ርቀት ድረስ መሄድ አያስፈልገውምና፡፡  ለምሳሌ ያህል ያሜሪቃ ጥቁሮች በጥቁር ፓሊስ ከመያዝ ይልቅ በነጭ ፖሊስ መያዝን የሚመርጡት በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡
 16. የዐብይ አሕመድ የአማራ ጥላቻ እጅግ የመረረ ከመሆኑ የተነሳ፣ ዐማራ ተጠናክሮ ከሚያይ ይልቅ ወያኔ አዲሳባን ተቆጣጥሮ በስቅላት ቢቀጣው ይመርጣል፡፡  ሰባተኛው ንጉሥ ዐብይ አሕመድ የስልጣን ጥመኛ ቢሆንም፣ የስልጣን ጥሙ ግን ከአማራ ጥላቸው አይበልጥበትም፡፡  አለበለዚያማ ለዐብይ አህመድ ስልጣን ይጠቅም የነበረው በነቂስ ደግፎት የነበረውን አማራን ይበልጥ አጠናክሮ፣ ግማሽ አማራ በመሆኑ ምክኒያት የሚጠራጠሩትን ኦነጋውያን እንዲቆጣጠርለት ማድረግ ነበር፡፡
 17. ሰካራም ባል ሚስቱን አመስግኖ እንደማይጠግብ የታወቀ ነው፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚያወራው ስለሷ መልካምነት ነው፡፡  ይህን የሚያደርገው ደግሞ በሰካራምነቱ ሳቢያ በሚስቱ ላይ የሚደርሰው ዘርፈብዙ ጉስቁልና ሕሊናውን ስለሚሸነቁጠው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ባሕሪ የስነልቦና ሰወች ማካካስ(compensation) ይሉታል፡፡  የዐብይ አህመድ ድርጊቶች ሁሉም የሚጠቁሙት ግለሰቡ በሥርሰደድ (chronic) የማካካስ በሽታ በጽኑ የታመመ የስነልቦና በሽተኛ ሳይሆን እንደማይቀር ነው፡፡  ስለ ሰላምና ስለ ፍቅር አውርቶ የማይታክተው ዐብይ አህመድ፣ የሰላምና የፍቅር ቀንደኛ ጠላት ስለሆነ ይሆናል፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ መግደል መሸነፍ ነው የሚለው ዐብይ አህመድ፣  ማሸነፍ መግደል ነው በሚል መርሕ የሚመራ ደም ጠማሽ ስለሆነ ይሆናል፡፡  አባቱን ስማችውን ሳይጠቅስ እናቱን አለመጥን የሚያሞግሰው ዐብይ አህመድ በናቱ ምንነት አለመጥን ስለሚያፍር ይሆናል፡፡  እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የብቸነት ኑሮ ትገፋ የነበረቸውን እማወራ (single mother) ሚስቱን አለመጠን የሚክባት ደግሞ በጓዳ የሚያዋርዳት የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ ስለሆነ ይሆናል፡፡
 18. የጎሳፖለቲካ ተወልዶ፣ አድጎ፣ ተመንድጓል እንጅ፣ ከያኒ ቴድሮስ ካሳሁን እንዳለው አርጅቶ አልሞተም፡፡  የስልጣን መጨበጫና የሐብት መሟጠጫ እስከሆነ ድረስ ደግሞ ይበልጥና ይበልጥ ይመነደጋል፣ አቀንቃኞቹም ይበልጥና ይበልጥ አክራሪወች ይሆናሉ፡፡  የጎሳ ፖለቲካን የሚገድለው፣ የጎሳ ፖለቲካ ከሚጠቅማቸው በላይ እንደሚጎዳቸው አቀንቃኞቹ ወያኔወችና ኦነጋውያን በግልጽ ከተገነዘቡ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ይህ የሚሆነው ደግሞ ጦቢያዊነት ማተቡ የሆነው የአማራ ሕዝብ ባማራነቱ ተደራጅቶና ተጠናክሮ ለጎጠኞች ቀይ መስመር ሲያቀመጥና መስመሩን ባለፉ ቁጥር፣ ባለፉበት መጠን ሊቀጣቸው ሲችል ብቻ ነው፡፡  ጎጠኞች ራሳቸውን እያጠናከሩ፣ የአማራን መጠናከር እንደ ጦር የሚፈሩበትም ምክኒያት ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድም ያማራ ብሔርተኝነት የጦቢያ ስጋት ነው ያለው፣ የኦነጋውያንና የወያኔወች ስጋት ነው ለማለት ነው፡፡
 19. ስለዚህም የአማራ ሕዝብ በአማራነቱ ተደራጅቶና ተጠናክሮ የጎጠኞች የበላይ መሆን፣ ለጦቢያ ሕልውና አስፈላጊም በቂም(necessary and sufficient) ነው፡፡  በመሆኑም፣ በአማራ ሕልውና ላይ መምጣት ማለት በጦቢያ ሕልውና ላይ መምጣት ማለት ነው፡፡  ጣልያን ያደረገው፣ ወያኔና ኦነግ እያደረጉት ያለው ይሄንኑ ነው፡፡
 20. የአማራ ሕዘብ ከዐብይ አሕመድ አፍዝ አደንግዝ ከተላቀቀ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

9 Comments

 1. ዲባቶ መስፍን አረጋ የደበተው ይመስላል። ይዘላብዳል። የአገሩ ልጅ አመጸኛው ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ሤራ ሲያካሄድ ተነቅቶበት መወገዱ አልዋጥ ብሎታል። ከህወሓት ባላነሰ የዘር ጥላቻ መርዙን ይረጫል፣ የሚቀበለው ግን አላገኘም። ምን ይዋጠው? ለነገሩ የአገር አመራር እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ሂደት ብዙም እንዳልገባው ያስታውቃል! “ዐብይ አሕመድ ቢያደፋፍራት እንጅ፣ አሜሪቃ የዲፕሎማሲ ደንቦችን በመጣስ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብታ ያማራ ልዩ ኃይል ከወልቃይትና ከራያ ይውጣ ለማለት እንዴት ትደፍራለች?” ብሎ የሚከራከር ገና ጥሬ ቢሆን ነው።

  • አለም ይህን ቱባ ምሁር አቅም ካለ በተመጣጣኝ እውቀት መረጃና ማስረጃ መፋለም እንጂ እንዲህ ሚዛኑ በቀለለ ስድብ እራስን ማቅለል ምን የሚሉት ነው? አንችና መሰሎችሽ ባለፈበት የማጣጣል ስድብ ልታስቆሙት አትችሉም ፍልሚያችሁ ከመስፍን ሳይሆን ከሳይንስ ጋር ይሆናል ።

   ያስበረገጋችሁ የመስፍን ጽሁፍ ሳይሆን የእሱን ሀሳብ ተከትሎ የሚመጣው ታሪክን ማቃናት ነው። በተረፈ ወደ ኮምፒተር ጣትን ከመቀሰር ሀሳቡ እስኪገባሽ ደጋግመሽ አንብቢው። ምን የሚሉት አመል ነው በግርድፍ ግንዛቤ ለትችት መንጠራራት? በዚህ ላይ አፍ ሲከፈት……የሚሉት ብሂልንም ማሰብ ጥሩ ነው። በየቦታው እየተክለፈለፍሽ በጥሬ ግንዛቤሽ ሊቃውንቶችን አትሞልጭ። በነገራችን ላይ ይህ ጽሁፍ ግንዛቤሽን ለመሞረድ ስለሚጠቅመሽ በማህደርሽ አስቀምጥሽ መሰረት እስኪይዝልሽ ደጋግመሽ አብላይው። አይ እኔ ለዚህ አልታደልኩም ካልሽ የአቶ አንዳርጋቸው መጽሀፍ ከትራስጌሽ አይለይ።

 2. ልጅ መስፍን – እኔ የሚገርመኝ ችግር ጠቋሚ መቼ ጠፋ። አሁን እኮ ተይዞ ያለው መለፍለፍ ነው። መፍትሄ ነው የጠፋው። ዶ/ር አብይ ብቻውን የሃገር ጠላትና አማራ ጠል ነው ብሎ ማመን ከውስልትናው ፓለቲካ ጋር የተቀየጠ እውነት ነው። እንዲህ ሲባል መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች የሉም ማለት አይደለም። አሉ። የሰሜን እዝን ወያኔ ካጠቃው በህዋላ የተፈጠረው ችግርና የጭካኔ መጠን እየታወቀ ያለምንም ዝግጅት ጦሩ ትግራይን ለቆ መውጣቱ አጠያያቂ ነው። ከተወጣም በህዋላ ወያኔ ጥቃት እንደሚከፍት እየታወቀ የአፋርና የአማራን ህዝብ ለመከራ በማጋፈጥ ጦሩ ወደ ኋላ እንዲሸሽ የተደረገበት ጉዳይ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ይህ በዚህ እንዳለ ወያኔ የአፋርና የአማራ ቦታዎችን ወሮ በህዝብና በንብረት ላይ ያደረሰውን የሰቆቃ ጎርፍ ህዝብ እንዲያውቀው በሥፍራው በመገኘት ለምን እንደማይዘገብ ጭራሽ አይገባኝም። የሞተ ሰውና የቤት እንስሳት ለመቅበር ከመቸኮል ሁሉን ዘግቦ መያዝ አስፈላጊ ሆኖ እያለ በሽፍንፍን መታለፉ አሁንም አማቺ ሁኔታ ለጠላት እንዳለ ያመላክታል። አውቃለሁ ጥቂቶች ያለውን ገመና ለመመዝገብ ሞክረዋል። ግን ሙሉነት የለውም። የፈረሰው ድልድይ፤ የሞተውና የቆሰለው ሰው፤ የተፈናቀሉት ወገኖቻችን፤ የተቃጠለው ቤት፤ የወደመው የመንግስትና የግል ንብረት ሙሉ በሙሉ በቪዲዪ ስፍራውንና ቀኑን ባመላከተ መልኩ ተመዝግቦ መያዝ ነበረበት። ያ ግን በተጠና መልኩ አልሆነም። ዛሬም ትላንትም አማራ እየሞተ ነው። በወለጋ ኦነግ ሸኔና አጋሮቹ በሰሜን ወያኔ ሃርነት ትግራይ እያረደው ይገኛል። ግን ይህን ጉዳይ ለመቀልበስ ሰውን ማስተማር፤ ማስታጠቅ፤ ማስተባበር፤ አንድ ለሌላው የሚደርስበትን መንገድ ማመቻቸት ሲቻል የሞተን ቀብሮ የራስ ሞትን መጠበቅ ጅልነት ነው። ወያኔና የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች አማራን ከማጥፋት አላማቸው የሚገታቸው እነርሱም ሞትን ሲቀምሱ ብቻ ነው። እንተ እንዳልከው የአማራ ህዝብ የዶ/ር አብይ አፍዝ አደንዝዝ አልያዘውም። ያደነዘዙት እንመራሃለን እናውቅልሃለን አማራን እንወክላለን የሚሉ የቀድሞ የወያኔ ተለጣፊ ባለስልጣኖችና ካድሬዎች እንጂ።
  ወያኔ ከራሱ ክልል ወጥቶ ሌላውን ህዝብ እንዲያተራምስ የሆነው ጠንካራ መረጃ ባለመኖሩ ነው። የሰውና የሌላም የመረጃ ሰንሰለት ቢኖር ኑሮ ከመምጣታቸው በፊት ሊደረጉ የሚገቡ ዝግጅቶች ወይም የሲቪሉን ህዝብ ማሸሽ በተቻለ ነበር። ባጭሩ የችግሩ ምንጭ እኛንም ይጨምራል እንጂ መንግስት ብቻውን አይደለም። መንግስት ማለት ህዝብ ነው። ህዝብ ማለት መንግስት ነው። ግን አሁን በዘር፤ በቋንቋና በክልል በተሰመረቸው የድህረ ወያኔ ሃገር ነገር ሁሉ አስረሽ ሚቸው ነው። እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ሰው ህግ አስከብራለሁ ብሎ እያቅራራ ተመልሶ የህልውና ዘመቻ ነው ብሎ የሚቀባጥረው? ለመሆኑ የምንሰራውን እናውቃለን? የእርድ ከበት እንደ ጎርፍ የሚላክለት ሰራዊት እንዴት ነው ሥጋ እየበላ የሚዋጋው? ሰው ለእንስሳትም እንኳን አያስብም እንዴ? ለምን ቆሎና ዳቦ ቆሎ ወይም ከወያኔ ከማረኩት ብስኩት እየበሉ አይዋጉም? ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ በሆነበት የጦር ቀጠና የምን እርድ ነው። ይህ ሁሉ የዲሲፒሊን ማጣት ነው። ሥጋን እየበሉ ሥጋን የመግደል ዘይቤ። የእብዶች ጦርነት። ይልቅስ ከየስፍራው ለሰራዊቱ እየተባሉ የሚላኩት የቀንድ ከብቶች፤ በጎችና ፍየሎች ንብረታቸው ለወደመባቸው የአፋርና የአማራ ክልል ገበሬዎች፤ በጦርነቱ ለሞቱ የገበሬዎች ቤተሰብ መቋቋሚያ ቢሰጡ አራብተው ለግልና ለሃገርም ይጠቀሙበታል። የተበላ ነገር ፋይዳ ቢስ ነው። ሁሌ አምጡ!
  አሁን ወያኔ ተከቧል፤ እየተደመሰሰ ነው፤ ተቆርጦ የቀረውን እያጸዳን ነው የሚሉን አባባል ሰራዊቱ መቀሌ እያለ ይል የነበረውን የጉራና የእውነት ጭፍልቅ ወሬ መሆኑ ነው። ወያኔ ከክልሉ ወጥቶ በታንክና በከባድ መሳሪያ እየታገዘ ባፈረሳቸው ቦታዎች ሁሉ “እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም” በማለት እየጻፈ። የፈረሱ ቤቶችን ለመጸዳጃ እየተጠቀመ፤ ሴትና አረጋዊያንን እየደፈረ ሃገርን ሲያፈራርስና ደብረታቦር ድረስ አልፎ ተርፎም አፋር እስኪገባ ጮማ የሚቆረጥለት ጦር የት ነበረ? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። አሁን ከሱዳን ዳርፉር የኢትዪጵያ የሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ተመድንና ሱዳንን ወትውታ የተሳካላት አሜሪካ ኢትዪጵያን ለማፍረስ ከወያኔ ጋር አብራ ተሰልፋለች። ለምን እንዲወጡ ተደረገ ለሚለው መልሱ ሱዳን በቅርብ ከግብጽ ጋር የተቀናጀ ወረራ በኢትዮጵያ ላይ ትከፍታለች። ይህም በአሜሪካ በሚሰጣቸው መመሪያ ነው። አሜሪካኖች ሃገር አፍራሾች ናቸው። አሁን በአፍጋኒስታን ጭንቅ ውስጥ ያሉት አሜሪካኖች 20 ዓመት ሙሉ ተፋልመው አልሆን ሲላቸው እንደ ቬትናሙ ጥሎ መፈርጠጥ ሆኗል ስራቸው። ለዚህ ነው እነ ታይዋንና ሌሎችም አሜሪካ ከጎናችን አብረውን ይቆማሉ የሚሉ ሁሉ ሞኞች የሚሆኑት። መሳሪያ የሸጣሉ፤ ያስታጥቃሉ ግፋ በለው ይላሉ እነርሱ እስካልሞቱ ድረስ። ፍርዳቸውና ድርጊታቸው ሾተል ነው። ለምሳሌ በቅርቡ የኤርትራዊን ጄኔራል ማገዳቸውን በዚህና በዚያም ጥላሸት ቀብተው ነግረውናል። ግን ፍትህ ከሆነ የሳውድ አረቢያው መሪ ገዳይ ስኳድ ልኮ አሜሪካዊ ዜግነት ያለውን ጋዜጠኛ አፍኖ በመግደል ሰውነቱን ቆራርጦ የጣለው ጨካኝ እንዴት እንዲኖርና በነጻነት እንዲንቀሳቀስ ተፈቀደለት። መልሱ የሳውዲ የዘይት ክምር ለአሜሪካ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ስለሆነ ነው። ለዚህ ነው የአሜሪካ የውጭ ፓሊሲ ወልጋዳና ዘረኛ ነው የምለው። በሱዳን የስደተኛ ስፍራዎች የወያኔን ስልጡኖች የሚያሰለጥኑት ሱዳንና ግብጽ በአሜሪካ አይዞአችሁ እየተባሉ ነው። ለዚህም የወያኔ ሰዎች በሃገር ውጭና በሃገር ውስጥ ድጋፋቸው ከፍተኛ ነው። ሃገር ለማርፍረስ መሆኑ ነው።
  ዶ/ር አብይ ገና ትግራይ ውስጥ ሰራዊቱ እያለ በሰራዊቱ ላይ በትግራይ ህዝብ የደረሰበትን ግፍ በግልጽ ቢነግረን ኑሮ አሁን ያለንበት ሁኔታ ላይ አንደርስም ነበር። ውሃና ምግብ የጠየቁ ወታደሮች ለዚያውም በዋጋ መርዝ ተቀላቅሎ ተሰቶአቸው አልቀዋል፡ ብዙው ወታደር ለአሰሳ ሲወጣ በማዘዣ ጣቢያው ያሉ ጥቂት አመራር ሰጪ ወታደርች ተከበው እንደ ከብት ታርደዋል። የመኪና መስታውት፤ የመኪና ጎማ በማበላሽት ሰራዊቱ እንዳይንቀሳቀስ አሻጥር ተሰርቷል። ሌላም እዚህ ላይ መጻፍ የማይችሉ አጸያፊ ነገሮች በሰራዊቱና በሰራዊቱ ቤተሰቦች ላይ ተደርጓል። ህዝብ አናስቀይምም ገለ መሌ እየተባለ ነው ዛሬ ያለንበት የመከራ ዶፍ ላይ የቆምነው። እውነተኛ በሆነ መረጃ ህዝቡ እንዲያውቀው ተደርጎ ቢሆን ኑሮ አሁን ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ባልተባልን ነበር። አሁንም ወያኔ ሙሉ በሙሉ ካልጠፋ የኢትዮጵያ መከራ እንደ ክረምትና በጋ ተፈራራቂ እንጂ እልባት አያገኝም። ልመናው፤ ሃዘኔታው፤ ለሚያዝንልህና በስራህ ለሚያከብርህ ወገንህ እንጂ መርዝ ምግብህና መጠጥህ ላይ ጨምሮ ለሚሰጥህ መሆን የለበትም። የእብድ ፓለቲካ ሁሉጊዜ አሸነፍኩ እንጂ ተሸነፍኩ አይልም። ለዚምህ ነው የትግራይ ህዝብ ወያኔን እንደ ፈጣሪው የሚያመልከው። ባልታየና ባልተጨበጠ አለም የመናወዝ እይታ። አሁን ማን ይሙት ትግራይ ለራሷ ሃገር ሆና መኖር ትችላለች። አትችልም። በመከራና በችጋር ውስጥ አዎን ይኖራል። ግን ሰው የሚያምርበት አብሮ መኖርን ሲለምድ ነው። ስለሆነም መስፍን አረጋ የዶ/ር አብይን ገመናና ድክመት ከሌሎች ጉዳዮች ጋር አስነብቦናል። እኔ ግን በሃሳቡ አልስማማም። ወያኔ የዶ/ር አብይን አንገት እንደሚፈልግ ገና ከጅምሩ የታወቀ ነው። አሁንም እሱን ለማጥፋት የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም። ይህን ስል ዶ/ር አብይ ምጡቅ መሪ ምንም ስህተት የለበትም እያልኩ አይደለም። አሁን ሃገሪቷ ባለችበት ያጣብቂኝ ጊዜ ውስጥ ከዶ/ር አብይ የተሻለ ሰው የለም። እስከዚያው ዶ/ር አብይና መንግስታቸው ከጥፋታቸው እየተማሩ ዘርና ቋንቋን ተገን ሳያረጉ ለአንዲት ኢትዮጵያ እንደሚሰሩ ተስፋ አደርጋለሁ። ጊዜው የምንካሰስበት ሳይሆን አንድ የምንሆንበትና ጠላትን የምንመክትበት በመሆኑ ለዛሬው የመስፍን አረጋን ክስ ፍርድ ቤቱ በቀጠሮ አልፎታል። ፈገግታም የመኖር አንድ ምልክት ነው። በቃኝ!

  • ተሰፉ በሚገባ አስቀምጠውታል ትክክል ነው ወያኔ በሁሉም መስክ ነው አገራችንን ያራቆታት የዓብይ ድምፅ ማጥፋት ግን በዝህ ጊዜ ተገቢ አይደለም ???? thank you!!

 3. ጸሃፊው መስፍን አረጋ ከቀድሞው ከፍታው ወርዶ ወያኔ በቀደደለት ቦይ ሲፈስ እንደማየት አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ሃገር ከውጭና ክውስጥ በተወረረችበት በዚህ የጨለመ ግዜ እንዲህ አስጸያፊና ግዜውን ማየት የተሳነው ከፋፋይ ለወያኔ ለሱዳን ለግብጽ ለአውሮፓውያንና ላሜሪካ የወገነ ሃገር ሻጭ ባንዳና መሰሪ ጽሁፍ ክመስፍን አረጋ ባሁን ሰአት መስማት የእርግማን ሁሉ ጥግ ነው፡፡ አቢይ አህመድ በኢትዮጵያዊነቱ አይጠረጠርም፡፡ እስክዛሬም ጥርስ የተነከሰበት ሃገራዊ አንድነትን ብሎም የምስራቅ አፍሪቃ ቀጠናና የፓን አፍሪቃ አቀንቃኝ በመሆኑ ነው፡፡ የጠሉት ውያኔዎች ሃገር ከፋፋይ ቡችሎችና እነ መስፍን አረጋ ናቸው የተነሱበት፡፡ በዚህም ምክኛት በእስከዛሬው ባንጻራዊ ተአማኒ በተባለ ምርጫ 38 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለመስፍን የተታለሉ የመሰለውም አማሮች ድምጻቸውን ሰጥተው ለሚቀጥሉት 5 አመታት መርጠውታል፡፡ መስፍን አረጋ ወደድም ጠላ ህጋዊ የሃገሪቱ መሪ ይህ ባልዋለበት የምትወነጅለው ነው፡፡ አፍህን ደም ደም እያለውም ቢሆን ይህን እንደሃሞት የጎመዘዘ ጥላቻህን ሳይደፋህ ዋጥ አድርገህ ለሚቀጥለው 5 አመት ምርጫ ተዘጋጅ፡፡ አሁን ሃገራችን ባለችበት የጦርነት ግዜ ይህን መሰል ከፋፋይ ከልክ ያለፈ ጥላቻ ደግሞ ራስህንም እንዳይጎዳህ ጠንቀቅ በል፡፡ ሰውየው ከነመፈጠርህም ላያውቅ ይችላል ሃገርህን ግ ን በዚህ በከፋ ዘመን ይህን መርዛማ ለወያኔና ለኢትዮጵያ ጠላቶች የሚመች ከፋፋይ ንግግርህን ይዘህ እዚያው የስደት ሃገርህ ተቀመጥ፡፡ ኢትዮጵያን ካለችበት ችግር ለመታደግ አቅሙ ባይኖርህ ይህን መርዝ አትርጭባት፡፡ ኢትዮጵያ ጠላቶቿ ይውደሙ፡፡

 4. እዉነትን ሳይቀባባ የአብይ አህመድን ሙልጭልጭ ሰብእና እና ፀረ አማራነት የተነተነ ደፋር ተንታኝ ነው መስፍን አረጋ።

 5. ለመስፍን አረጋ በመሠረቱ ከላይ በአለም፤በተስፋ እና በዮሐንስ ተገቢ አስተያየት ተሰጥቶሃል አይምሮው ካለህ ያለምንም ማቅማማት ምክራቸውን ተቀብለህ ንስሃ ግባ። ሆኖም አግባብ ባይሆንም በበኩሌ በገጠሩ አርሶ አደሮች ወይፈናቸውን ለእርሻ ለመጠቀም ፍሬውን በመቀጥቀጥ በሬ ያደርጉታል። ፍሬው ከተቀጠቀጠ በኋላም በሬው ለአንድ ሰው ንበርትና አራሽ ሆኖ ሲኖር ጉልበት ሲደክምም በርካሽ ዋጋ ለፍሪዳ ይሸጣል።ውሎ እርሻ፤በባላት ቀን ዉሎው ከላሞች ጋር ነው። ስሜቱ በመቀጥቀጡ ምክንያት ማግሳቱንም ያቆማል ፤ጊደሯም ትወጋዋለች።በመሆኑም ግልጽ ደብዳቤ ለዶ/ር አቢይ ብለህ ከንቱ እና ደካማ ዝብጥርጥሩ የወጣ የጥላቻ ዘመቻ የጻፍከው ከጉብርህ ወይም ከእምብርትህ በታች ያለው ፍሪህን የህወሃት አባሎች ስለቀጠቀጡህ ስሜትህንም ስለአጠፉት ከሌላው ህብረተሰብ ጋርም እዳትውልም በመሆንህ እንደበሬው የነሱ አራሺነትህን እየነገርከን ነው ።አይምሮህም ጉልበትህም በመድከሙ አንተን እንኳን በርካሽ ዋጋ በሳንቲምም ሊሸጡህ ስለማይችሉ ተሎ ብልህ ለራስህ ንሥሃ ግባ። ከንቱ ቆዳ ለባሽ

 6. እንደዚህ እያላችሁ መርዛችሁን እየረጫችሁ አብይን የምንጠላው መስሏችሁ ከሆነ ህልም ነው እኛ ኢቲዮጵያውያን ለአብይ ብለን ሳይሆን ለሀገራችን ነው የምንሞተው ስታማስል ብታድር ያርብሃል እንጅ ሰሚ አታገኝም ፡፡

 7. ጊዜ – ሰውን ያደርጋል የውሻ ሚዜ !!
  እናንተ ግሞችና የሆዳሙ ብአደንና የመርዘኛው ኦሮሙማ አጎብዳጆች ናችሁ እንጅ መስፍን አረጋ እውነቱን ቁልጭ አድርጎ ዘርግፎታል፡፤ ሀቅ ሀቅ ነው፡፤ አይቀየር አይደለዝ አይበረዝ፡፤ አለም የተባልከው የመጀመሪያው አስትያየት ሰጭ፦ ለመሆኑ አሳምነው ጽጌን ያስገደለው ማን ሆነና ነው አብይን ነጻ ለማውጣት የምትውሸለሸለው? አዛኝ ቅቤ አንጓች አሉ፡፤
  ከላይ የለምጩን ባሰፈረው አስተያዬት እቅጩን አሳውቆናል፡፡ መስፍን አረጋ ፦ እድሜ ይስጥህ፡፤ ከክፉ ይጠብቅህ፡፡ በነገብርዬ ተርታ ተሰልፈህልና!!
  ጊዜ – ሰውን ያደርጋል የውሻ ሚዜ!!! እንዲሉ ሆነና አማራን ከቀኝም ከግራም ከባድ መከራ እየመጣበት መሆኑ ገና በጧት ታይቷቸው የነበሩትን እነ ጀኔራል አሳምነው ጽጌንና እነ ዶክተር አምባቸው መኮነንን በረቀቀ የፖለቲካ ቁማር ያስወገዳቸው አብይ አህመድ ገና ብዙ መከራና የሰቆቃ ህይወት ለአማራው እያዘጋጀለት እንደሆነ ፍንትው ብሎ ይታያል፡፡ አሁን ከወያኔ ጋር ባለው የዉጊያ አሰላለፍ፣ የመሳሪያና የመረጃ ስርጭትና ብሎም የአየር ሀይል አሰራር የሴራው ፍንጭ እየታየ ነው፡፤ እግዚአብሄር ያጥፋው፡፤ የሰራውን ደባ ወደራሱ ያድርግለት፡፡ ከአንግዲህ አማራው ያለው ብቸኛው አማራጭ በራሱ ተማምኖና አንድ ሆኖ ከስሩ “ሀ” ብሎ ጀምሮ ትግሉን በጎበዝ አለቃ እየተደራጀ መሳሪያን ከጠላቶቹ እየቀማ ተጋድሎውን ማሳደግ ብቻ ነው፡፡ ወላድ በድባብ ትሂድ እንጅ መንጋ የመለስ ዜናው አሁን ደግሞ የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ብአደኖችንም አንድ ሳያስቀር ከውስጡ መንግሎ በመጣልም በማስወገድም ራሱን አደራጅቶ ነጻነቱን ታሪኩን በትግሉ ያስመልሳል፡፤ የፖለቲካ ብስለት፣ የአላምማ አንዲነት ፣ያላሰለሰ ትግልና ብልሀት እጅግ በጣም ወስኝ ነው፡፡ አማራን ከተደገሰለት እልቂት የሚያድንና የኢትዮጵያንም አንድነትና ነጻ አገርነት የሚጠብቅ አምላክ ይርዳን!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.