የአሜሪካ ” ደሊላዊነት ” ዛሬም ቀጥሏል  – መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ 

አሜሪካ ለደሃ አገሮች ውበት ና ብልፅግና ደንታ የሌላት ናት ፡፡ ለራሱ አማላይ ውበት ተጨናቂ  ደሊላዊ ባህሪ ያለው መንግስት ያላት አገር ናት ። የደሊላን ማንነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታገኘዋለኽ  ( መፀሐፈ መሳፍንት ምዕራፍ 16ን አንብብ  ። ) ደሌላዋ አሜሪካ በተካነችበት ደሊላዊነት እንደ መፅሐፍ ቅዱሱ  ሳምሶን አዋዝታ የደሃ አገርን ፀጉር ላጭታ በጠላቶቿ እግር ብረት ማሳሰር ልማዷ ነው ። እገር ከታሰረ በኋላ ፈጣሪን የምትማጸነው  “ እባክህ አምላኬ አሥረው እያሰቃዩኝ ካሉት ጠላቶቼ ጋር አብረህ አጥፋኝ ። “ እያልክ ብቻ ነው  ። ለዘመናት አሥረው ከሚሳለቁብህም የሳምሶን ሞትን ብተመርጥ ማን ይፈርድብሃል  ? ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ፣ ዛሬ ና አሁን አንተ አርበኛው ጀግናው ኢትዮጵያዊ ፣ ለአገርህ ክብርና ህልውና ለመሰዋት ዝግጁ በመሆን ኢትዮጵያን ሊቀብራት ያሰቡትን  ባንዳዎች ጊዜ ሳሰጣቸው ከመቅበር ውጪ አማራጭ የለህም ፡፡

ዛሬ ና አሁን ፣  የአሜሪካ መንግስት ” በደሊላዊነት ”  በአፍጋኒሥታን ሠላማዊ መሪ ና ህዝብ   ላይ  የፈፀመው ሸፍጥ፣ ለአንተ ለአርበኛው ኢትዮጵያዊ ትልቅ ትምህርት ሰጥቶሃል ፡፡   የሸር ሥራዋና ፉገራዋ በሙሉ፣  የሚተገበረውና  የሚከወነው በደሊላዊነት መሆኑን ምንጊዜም አትርሳ ፡፡  ደግሞም ፣ በሲአይኤ አማካኝነት  በየደሃ አገሩ  አያሌ ብዝበዛ አመቻማቾች ነፍ ደሊላዊያን አሜሪካ እንዳሏት አትዘንጋ ፡፡

ደሊላዊያኑ ፤  በዶላር  በማማለል ህሊናን የሚያሸጡ ከመሆናቸውም በላይ፤  ደካሞችን በባትሪ እየፈለጉ፣  የብዝበዣቸው አጋር በማድረግ ይታወቃሉ ፡፡ በሙስና የተጨማለቁ ኢትዮጵያዊያንን አሜሪካዊ ዜግነት  እንዲያገኙ በማድረገ ሀብት ማሸሽም የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡  አገርን በዝብዘው  የሚያሥበዘብዙ ።  በልዩ ጥቅማ ጥቅም ህሊናቸውን ሽጠው የአገርን ቅርስና ክብር  እንዲጠፋ በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ …   ውጫቸው ሲታይ መላክ የሚመሥሉ … ውሥጣቸው ግን እንደ ዳቢሎሥ ጨካኝ የሆነ ፤  ለአሜሪካ ከበርቴዎች ዘረፋ መንገድ ጠራጊ ወኪሎችን በሥፋት የጥሬ ሀብት ጥቅም በሚያገኙበት ለመበልጸግ በሚታትር አገር ውስጥ  ሁሉ በማሰማራትም የታወቁ ናቸው።

አሜሪካ በገዘፈ ሀብቷ የተብለጨለጩ ፣ አማላይ የገንዘብ አቅም  ያላቸውን ደሊላዎች በመላው ደሃ አገር አሰማርታለች።  እነዚህም  ፍቅር ሳይኖራቸው ፣ አፍቅረናል ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት የሚያወናብዱ ፣ የሚያጭበረብሩና በአዞ እንባ አንቢነታቸው ይታወቃሉ፡፡  እንደ ደሊላ የሆነ መልክ ያላቸውም ናቸው።  ( በሰው አፍቃሪነት ፣ በፍትህና ርዕት ወዳድነት የተሽሞነሞነ ቃላትን የሚያዘንቡ ሐሳዊ መሲህ የሆኑ ህቡ ወኪሎችም አሏቸው፡፡ )  የሚፈልጉትን ካሳኩ በኋላ አራት እግርህን ብላ በማለት ወደሀገራቸው እብስ ሲሉ ነው የምታውቃቸው፡፡ … የአሜሪካንን ቱጃሮች ጥቅም ብቻ የሚያሥጠብቁ  ሆኖም ይህንን ዓላማቸውን በሰብአዊ መብት፣  በዴሞክራሲ ና በነፃነት ሥም ሸፍነው በሥውር የሚንቀሳቀሱ ስለመሆናቸው እስከማዕዜኑ አታውቅም ።

አሜሪካ በአማላይ ደሊላዎቿ  እያዋዛች፣ ጎዳህ ድረስ ሰተት ብላ በመግባት የምትፈልገውን ካገኘች በኋላ ለብዝበዛዋ የማይመች እንቅፋት ከገጠማት ወይም ደግሞ የብዝበዛ ተልኮዋን ከፈፀመች ከመቅሥፈት  እንደምተሸበለለ የቅርብ ጌዜ ታሪኳ ይመሰክራል።  ለብዝበዛ የቆመጠ ዓይኗ ላይ  በሩን ከርችሞ አገሬን አላስበዘብዝም ባለ መንግስት ላይ፣ በበዝባዥ ከበርቴዎቾ ሚዲያ አማካኝነት በቅጥፈት ወሬ ብዛት ዓለምን በማደናገር በዓለም ህዝብ ፊት ያ የደሃ አገር መንግስት ስሙ በመጥፎ እንዲነሳ ከማድረጓም በላይ እኔ የዓለም ፖሊስ ነኝ ብላ በሀሰት ትርክቷ ተደግፋ ልታጠፋው ትነሳለች።  በበዛ ጡሩንባ የዓለምን ህዝብ በውሸት ፕሮፖጋንዳ ስላደናገረችም የሚቃወማት እንብዛም አይኖርም።  (ሲኤንኤን ፣ ሮይተር፣  በቢሲ ወዘተ።  ሥለ አገርህ የእርስ በእርስ ጦርነት ሲያወሩ የአገርኽ መንግሥትን እንደሌለ ቆጥረው፣ አገር ለማፍረሥ ከሸፈተው  በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሥም በመንቀሳቀሥ የዘረኝነት አረምን ለመትከል  ከሚተጋው ጭራቅ ከሆነ ቡድን ጋር ወግነው እንደሆነ፣ ስትገነዘብ፣ እውነቱን በግልጽ ትረዳለህ ።)

እንደ  እባብ ብልህ እንደ እርግብ የዋኋ  ያልሆነችው ደሊላዊቷ  አሜሪካ

ደግሞም፣ ደሊላዊቷ  አሜሪካ ፣ ማሽንክ ናት ። እባብ ፡፡ በዓለም ላይ ባሉ ባላደጉ አገራት ሁሉ  ተበዝባዢ መንግሥት እንዲኖር ሥለምትፈልግ ነገረ ሥራዋ ሁሉ እንደ እባብ ካብ ለካብ ነው።  ከብ ለካብ እየሄደች ታጠምዳለች። ደሊላነቷን ሳታሥነቃ ። በእርሷ የበላይነት ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ባንኮች   በላይ በላዩ ብድር እንዲያበድሯቸውም በማድረግ ፣ መክፈል በማይችሉት ዕዳ እንዲዘፈቁ ታደርጋለች። ደሃ ና አቅመ ቢስ መንግሥት በመፍጠርም ፣ የእርሷ ፈቃድ ፈፃሚ  ታደርጋቸዋለች ።  አንገቱን የደፋ ግን ደግሞ ለራሱ ና ለጥቅም ሸሪኮቹ ብልፅግና ብቻ የሚሰራ የደሃ አገር  መንግሥት በየትኛውም ደሃ አገር እንዲኖር አትፈልግም ።

ለምሳሌ ለአፍሪካ አገሮች የምታደርገው ድገፍ በልፅገው ከዳቦ ልመና የሚያወጣቸው ሳይሆን ፤ ለእርዳታ ና ዕድሜ ለአሜሪካ የሚያሰኝ የፉገራ ዕርዳታ ነው።  የምታበድረውም ብድር ለመበልፀግ የማያሥችል ፣ የበለጠ የእርሷ ጥገኛ የሚያደርግ ነው ። በረጂ ድርጅቶቾም አማካኝነት እንደ ፈጣሪ እንድትታይ እየጣረች ፣ በጎን ደግሞ ለብዝበዛዋ ያልተመቻቸላትን መንግሥት ከሥልጣን ለማውረድ ተቃዋሚዎችን ከሥንዴ ጋር ቀላቅላ በላከቻቸው የሲአይኤ ቅጥረኞች ማደራጀት፣ ማሠልጠንና ተጥቅ ሰጥታ ማሰማራት የተለመደ ስራዋ ነው።  የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፣ ድሆች በልተው እንዲያድሩ፣ ” ሴፍቲ ኔት ” በማለት የደሃ አገርን ህዝብ በማደናገር ደሊላዊ ፍቅሯን ሁሌም ታሳያለች ፡፡ ህዝብ በምጽዋት ጠባቂነት እና በአሜሪካን አምላኪነት የማድረግ ስልቷ ይኸው የዓልሚ ምግብ እና የሥንዴ እርዳታ ነው ፡።  የብድሯ ባርያ የሆነ መንግሥት በመፍጠርም ተገዢዋ ታደርገዋለች ።

ወደጄ ፣ አሜሪካ የደሃ አገራት መንግሥታት የእርሷን ፈቃድ ፈፃሚ ፣ ታዛዢ ሎሌ እንዲሆኑ እንጂ  በአገር ፍቅር ሥሜት የጋሉ ፣ ብዝበዛን ተፀያፊ፣ የልማት ና ብልጽግና  አርበኞች እንዲሆኑ ከቶም አትፈቅድም ።

አሜሪካም ሆነች የቀድሞ  የአፍሪካ ቅኝ ገዢዎቻችን ፤ አገራቸውን ለማበልፀግ ቆርጠው የተነሱ አራት ዐይና መሪዎች በአፍሪካ ከተፈጠሩ ቶሎ ብለው ያጠፏቸዋል።… ለእነሱ ብዝበዛ የሚመቹ ፣ የራሳቸውን ህዝብ እርስ በእርስ በማጋጨት የሚታወቁ ፣ ዘረኛ ና አምባገነን መንግሥታትን የለሥማቸው ሥም በመስጠት ያቆላጵላጥሷቸዋል። በዚህም መንገድ ፣ አባገነኖቹ የአፍሪካ መንግስታት፣ በግብዝነት በመመጻደቅ ፤ የድህነት ሸምቀቆውን  በህዝባቸው ላይ የበለጠ  እንዲያጠብቁ ያተጓቸዋል ፡፡ አገራቸውን ተመፅዋች  በማድረግ መንግስት ወደ አሻቸው የሚጋልቡት ገራም ፈረስ እነዲሆን ያደርጉታል ።

( ትግራይን እና አገዛዙን ተመልከት ። የዳቦ ጥያቄ ያልተመለሰለትን ህዝብ ነው በሆዱ ሰበብ ለጥፋት አላማው ፣ ወያኔ  እየጋለበው ያለው ።   የሚልሰው ና የሚቀምሰው የሌለው ና ሥለዓለም ፖለቲካ አንዳችም ዕውቀት ወይም ግንዛቤ ስለሌለውም በእጦቱ የተነሳ ከሴታኑ ወያኔ ጋር ህዝብ ቢሰለፍ አይገርምም ፡፡ በችጋር የሚሰቃይ ህዝብ ምንጊዜም ዳቦ እሰጥሃለሁ ካለው ጎን ይሰለፋል  ። ምናልባት ጥያቂ የሚጀምረው በህይወት ሰንብቶ ፣ የዕውቀት ጮራ ሲያገኘው ና ከዳቦ ችግር ሲላቀቅ ብቻ ነው ። በአገርም ሁኔታ ብታየው ይኸው ነው ። ደሃ አቅመ ቢሥ ነው ። …)

 

የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ አንዳንድ የበለፀጉ የዓለም አገራት በዓለም ላይ ያሉ ደሃ አገራት በሙሉ በአምሥት ዓመታትት   ከድህነት እንዲላቀቁ ለማድረግ የሚችል አቅም አላቸው።  ይኑራቸው እንጂ እጅግ ሲበዛ ስግብግቦች ና አስመሳይ ኃይማኖተኞች በመሆናቸው አይናቸው የዛሬ 200 ዓመት ከተጠናወታቸው የጥሬ ሀብት  ብዝበዛ ሥላልተነቀለ የሚታያቸው የአፍሪካ እንቁ ፣አልማዝ ና መአድናት ብቻ ነው። እናም እያንዳንዱ ባለፀጋ አገር የደሃ አገራትን የአምሥት አመት በጀት የሚሆን ብር ለወታደራዊ በጀት  እያወጣ እርስ በእርሱ ትከሻ ለትከሻ ይገፋፋል  ። ( ለምርምር ሥራ ፣ ለጦር መሣሪያ ና ለሎጀሥቲክ ቢሊዮን ዶላር በሀብታሞቹ አገራት ይበተናል …) ከዚህ የጥፋት ወጪ ግማሹን እንኳን ቀነሰው  ለአፍሪካ ብልፅግና ብድር ቢያውሉት ና በህበረት ተቀናጅተው በመሥራት ደሃ አገራትን ለማበልፀግ  ቅን ልቡና  ቢኖራቸው ኖሮ ውብ የሆነች ዓለምን ለመፍጠርና ችጋርን እና ድህነትን ከአለም ያጠፉ ነበር ።

በዚህ ረገድ የበለፀጉት አገራት ሲገመገሙ ፣ በህሊና አንፃር የቀጨጩ ና እልም ያሉ ማይማን ሆነው ይገኛሉ ፡፡ ። ምክንያቱም ዓለምን ተባብሮ በማልማት ፣ ሰው ሁሉ እየተዟዟረ የሚጎበኛት ፣ በምድር አጭር ጊዜ ቆይታው የበዛ ስቃይ የማያይባት ዓለምን መፍጠር ሲችሉ  ፣ እነሱ ጠግበው ሲያጋሱ ፣ እነሱ በፈጠሩት ግጭት ና ጦርነት በሶርያ ፣ በየመን ፣ በአፍጋኒሥታን ፣ በኢትዮጵያ በእርስ በእርስ  ጦርነት ሰበብ በተፈጠረ ሥደት  ሰው በርሃብ አለንጋ እየተጠበሰ እያየን እነሱን አወቂዎች ና ኃይማኖተኞች ናቸው ለማለት አንችልም ፡፡

( አሜሪካ አፍጋኒሥታን የገባችው ታሊባን ከምር  የአልቃይዳ መጠለያ ምሽግ ነው ብላ  አሸባሪነትን በግንባር  ከምር ለመዋጋት ብቻ ነበርን ? የኦፕዬም ያልተቆረጠ ዘረፋን ፈልጋ እንደሆነስ ?  የመድሃኒት ካምፖኒዎቿን ፍላጎት ከሚገባው በላይ አላረካችምን ? ታሊባን ተመልሶ የአፍጋን መንግሥት እንዲሆን ሥትፈቅድ ዘላቂ ጥቅሞን የሚያሥጠብቅላት ሥውር እጃ ሳታሥቀምጥ ዝም ብላ የወጣች ይመሥላችኋልን ? ጆን ባይደን አሜሪካ በየደሃ ና በአንዳች ውድ ሀብት በበለፀጉ አገራት ውሥጥ  ጣልቃ የምትገባው  ለፅድቅ ሳይሆን የግል ጥቅሟን ለማሥጠበቅ ( ለብዝበዛ ) መሆኑንን እኮ  ነግረውናል ። )

የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ ፣ አንዳአንድ የበለፀጉት አገራት መንግሥታት ህሊና ቢሶች በመሆናቸው ሰው ሆነው ሳለ ፣ ለሰው የማያዝኑ ህሊና ቢሶች መሆናቸውን የሌሎቹን አገሮች ትተን በአገሬ በኢትዮጵያ የሚፈፅሙትን ሤጣናዊ ተግባር ማሥተዋሉ ብቻ በቂ ነው ። በተለይ አሜሪካ ይፋ የሆነ ጣልቃ ገብነትን የመረጠችውና በደሌላዊ የሴራ ፖለቲካ እነ ሳማንታ ፓወርን በመሳሰሉ የጥፋት ሴራ መሪዎች አማካኝነት የሤጣን ተግባር እየፈፀመች ያለችው ፤ ኢትዮጵያ ውሥጥ በአሸባሪው ትህነግ በኩል ስታከናውነው የነበረ  እጅግ ትርፋማ የሆነ ብዝበዛ ሥለተቋረጠባት ብቻና ብቻ  ነው  ። ይህንን ለመገንዘብ በአሜሪካ ና በአውሮፓ አሥፖልት ላይ በጥጋብ የሚከባለሉትን የመሣፍንቶቹን የትህነግ ልጆች መመልከት ብቻ በቂ ይሆናል ።  እነዚህ ጥጋበኞ ፣ በጣት የሚቆጠሩ የትህነግ ዓባለት ፤ አያሌ ቢሊዮን ዶላር በአሜሪካ ና በስዊዝ ባንክ እንዳከማቹ ይታወቃል ። ዛሬም ይኸው የደም ብር እየተቆነጠረ በመውጣት ለጥፋት ዓላማ በአገር ውሥጥ ይበተናል ።

በዚህ የደም ብርም “ሴት ለሚፈልገው ሴት ፤ ሥጋ ለማፈልግ ሥጋ ይገዛበታል ። ” የጦር ና የፖለቲካ አሻጥርም ይፈፀምበታል ። በግንባር በጦሩ ላይ ፤ በማህል አገር በጠቅላዩ ላይ ይሴርበታል ።…

ትላንት ታላቁ ና ጀግናው  የኢትዮጵያ ሠራዊት ጠመንጃውን ከዱላ በታች ቆጥሮ አንገቱን ደፍቶ ከሰሜኑ የአገራችን ክፍል ወደማህል አገር ና  ወደቀየው የገባው ፤ ጥቂት የማይባለውም  በበርሃ በውሃ ጥምና በርሃብ ክልትው ብሎ የቀረው ፤  አብዛኛው ወደሱዳን ና የመን  ተሰዶ በመግባት በሥተኋላ ወደአገሩ ተመልሶ ተመፅዎች የሆነው ፤ በሴት ና በሥጋ በተታለሉ ወታደራዊ ና ሲቪል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች እጅና እግሩ ታሥሮ ለእርድ በመቅረቡ ነው ። ደሊላዊነት ትላንትም ገዝፎ እንደታየ አትርሳ !

ይህንን እውነት ዛሬ ለማውሳት የፈለኩት ፣ በዓሉ ግርማ ” በኦሮማይ ” መፅሐፉ ጠቁሞን ያለፈው ፣ የሚያሥቆጭ ፣ ለሆድና ለሴት ተገዝቶ አገርን የመሸጥ አፀያፊ ተግባር  ዛሬም እንዳይደገም በማሰብ እንደሆነ  አትዮጵያን አፍቃሪ የሆናችሁ ሁሉ እንድትገነዘቡልኝ እወዳለሁ።

የአገራችንን የዛሬ ችግር ለመፍታት የሚያሥፈልገን፣ የተጋነነ እና የተደጋገመ ( በየሚዲያው የሚቀርቡ ሰዎች ራሳቸው ድግግሞሽ ናቸወ፡፡  በአገር ላይ ሰው እንደጠፋ ሁሉ ይኽ መሆኑ በረሱ አሳዛኝ ነው ። )  የሚዲያ ዲሥኩር አይደለም።  ዛሩ የሚስፈልገን   ለኢትዮጵያ አገሩ ክብር ና ነፃነት ሲል በልበ ሙሉነት ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት የሚተናነቅ ዜጋ ነው።  የዚህም ጀግና ገድል በኢቲቪ ፤ በፋና ፤ በዋልታ ካልተዘገበ በየትኛው የግል ሚዲያ እንዲዘገብ እንፈልጋለን   ?

ከኢትዮጵያዊያን ባህሪ አንዱ በጀግንነት ግለት ወደፊት ተራምዶ ጠላትን መግቢያ መውጫ አሳጥቶ ፣ ትንፋሽ እንዳያገኝ በማድረግ ጦርነትን በአጭር ጊዜ መጨረሥ እንጂ በተራዘመ ጦርነት መሠላቸት አይደለም ። እናም በሴት ፣ እና በዶላር የሚገዙ የጦር ና የፖለቲካ ሹማምንቶች እንዳይኖሩን የደህንነት ሥራችን ከምንጊዜም በላይ ጠንካራ መሆን አለበት ። ያልተገባ ና የተንዛዛ የመከላከያ ሚኒሥቴር ቢሮክራሲ ና አዛኝ ቅቤ አንጎች የሆነ የጠቅላይ ሚኒሥቴሩ አማካሪ ካለ ፣ ከሥፍራው ገለል መደረግ ይኖርበታል ።  ዛሬ አሜሪካ በሲአይኤ በኩል ሚዲያዎቿን በሙሉ አሥተባብራ ኢትዮጵያን ለማሽመድመድ እና ለአሸባሪው ትህነግ ቀኝ እጆን በመዘርጋት ከመቃብሩ ለማውጣት የምትፈልገው አሻንጉሊት መንግሥት በኢትዮጵያ ለመፍጠር በማሰብ ነው ፡፡ ይኽ አስተሳሰብ እጅግ ደካማ እና ኢትዮጵያዊያንን ከማያወቅ ጭንቅላት የመነጨ ነው ፡፡  በመሆኑም እኛ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን፣  አሸባሪውን ና  ጭራቁን ወያኔ  ከትግራይ ምድር ለማጥፋት የምናደርገውን ትንቅንቅ ፣ በአንድ ልብ ሆነን አገራችንን ለማዳን የምናደርገውን ጦርነት በአጭር ቀናት ለመፈፀም ቆርጠን መነሳት ይጠበቅብናል ።

አስታውሱ ፤   የአሜሪካው ሲአይኤ ዛሬም በሴት ና በዶላር  ( በሥጋ )  የኢትዮጵያን ከፍተኛ የጦር ና የፖለቲካ ባለሥልጣናት በማጥመድ በደሊላዊ ሴራ . በቀናት ውሥጥ አገር እንዲሸጡ የማድረግ ብቃት አለው። ከኢትዮጵያ የጦር ና የፖለቲካ  ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሥንቶቹ ከሱስ ነፃ እንደሆኑ እና ለገዛ ህሊናቸው ታማኝ እንደሆኑ ጠይቁ። ለማንኛውም አሜሪካዊያኑ በጠቅላይ ሚኒሥቴር አብይ አህመድ የገዘፈ አእምሮ ና አገር ወዳድነት  የተቋረጠባቸውን በትህነግ አማካኝነት የሚያገኙት ከሆነ ይህንን በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዓመታዊ   ጥቅም በማንኛውም መንገድ ለማግኘት ሥለሚሹ፣ የውጪ ቅጥር ተዋጊዎችን ና ነፍሰ ገዳዮችን ሳይቀር ከወያኔ ጋር ከማሰለፍ ወደኋላ አይሉም፡፡  እናም የኢትዮጵያ ደህንነት መሥሪያ ቤት ፣ ከሌሎች ወዳጅ አገር የደህንነት ዓባላት ጋር ተቀናጅቶ በዘመነ ደህንነት በከፍተኛ ባለሥልጣነት እና የጦር አዛዦች ላይ ሃያራት ሰዓት የክትትል ና የቁጥጥር ሥራ መስራት እንደሚጠበቅበት በማሳሰብ ጽሑፌን ብቋጭስ  ። …

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ  ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች ! !

ጤና ይስጥለኝ ፡፡