የህወሃት አሸባሪ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪዎችን ምንነቱ ያልታወቀ መርፌ ወግቷል August 23, 2021 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email 236391101 3010149952560797 3086562156685106336 n የህወሃት አሸባሪ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ነዋሪዎችን ምንነቱ ያልታወቀ መርፌ ሲወጋ ማየቱን አንድ የአይን እማኝ ገለጸ። በሀብሩ ወረዳ ቀበሌ 020 የሚኖረው ወጣት መሀመድ አንሷር እንዳለው የህወሃት አሸባሪ ቡድን በአካባቢው ሰርጎ ከገባ በኋላ የተለያዩ የግልና የህዝብ ንብረቶችን ዘርፏል። በየደረሱባቸው አካባቢዎች ሁሉ ዘርፎ የሚፈልገውን ያክል ከጫነ በኋላ ሌላውን በማቃጠል ሲያወድም ተመለክተናል ብሏል። ከዚህ ባለፈም “የኮቪድ 19 መከላከያ ነው” በሚል አሸባሪው ቡድን የተለያዩ ሰዎችን መርፌ ሲወጋ ተመልክቻለሁ ብሏል መሀመድ። አሸባሪ ቡድኑ ሰዎችን የሚወጋው መርፌ እስካሁን ምን እንደሆነና ለምን ዓላማ እንደሆነ ባይታወቅም “መርፌ የተወጋ እርዳታ ያገኛል” በሚል በርካታ ሰዎችን ወግቷል ነው ያለው። በተመሳሳይ በአፋር ክልል መርፌ ተወግቶ የእርዳታ አህል ያገኘ ጓደኛዬ አለ ሲልም መሃመድ ተናግሯል። የአሸባሪው ህወሃት ዘራፊዎች በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ቤት ሲያቃጥሉ ንጹሃንን ሲገድሉ ማየቱንም ተናግሯል። የአሸባሪው ቡድን ዘራፊዎች ለሰው ልጅ ምንም አይነት ርህራሄ የሌላቸው ጨካኞች መሆናቸውን በሚፈፅሟቸው ግዲያዎች ተመልክተናል ብሏል መሀመድ። በተለያዩ አካባቢዎች የአርሶ አደሮችን ቤት በማቃጠልም በጭካኔ ንብረቶችን ሲያወድሙ ተመልክቻለሁ ሲል እማኝነቱን ገልጿል። የአርሶ አደሮችን የቤት እንስሳቶች እየዘረፉ በማሸሽና ከባድ በደል በመፈፀም ላይ ይገኛሉም ነው ያለው። ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች የጥሞና ጊዜ ለመስጠት መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ቢያደርግም የህወሃት አሸባሪ ቡድን ሰርጎ ገቦች በአማራ እና አፋር ክልሎች ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስና ውድመት እያስከተሉ ይገኛሉ። ነሐሴ 17/2013(ኢዜአ — Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story የወሎን ኦፕሬሽን እየመራ ህውሀትን ላሊበላ እንድትገባ ያደረገው አቶ በረከት ስምኦን ነው Next Story ግልጽ ደብዳቤ በዐብይ አሕመድ ላይ ተስፋችሁ ላልተሟጠጠ አማሮች – መስፍን አረጋ