ፍጅቱ እና እልቂቱ የማያልቅልህ ዐማራ – ሙላት በላይ

ነሀሴ13 ቀን 2013 ዓ.ም

የዐማራዉ ህዝብ በተለይም ምሁሩ ዐማራን እየገጠመዉ የአለዉን ችግር ለመፍታት በቅድሚያ የችግሩን ምንጨ እና ጥልቀት ማወቅአለበት፡፡ የዐማራዉ ጠላት ማን ነዉ?  የጥላቻዉ መክንያት ምንድን ነዉ?  የድርጊቱ አስፈጻሚ ማን ነዉ? አፈጻጸሙ እንዴት ነዉ? ግቡስ ምንድን ነዉ? ብሎ በመጠየቅ ትክክለኛዉን መልስ በማግኘት መ ሥስራትን ይጠይቃል ፡፡

የዐማራዉ ጠላት ማን ነዉ?  ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተሰለፈዉ ሁሉ የዐማራ ጠላት ነዉ፡፡ከዚህ እዉነታ  ስንነሳ ግዙፉ እና ሥር የሰደዱ የዐማራ ጠላት አሜሪካ ና ምእራብ አዉሮፓ ሀገሮች ናቸዉ፡፡ምክንያቱ ደግሞ

1.እኤአ በ1868 ዓ.ም የሰዊዝ ቦይ መከፈትን  ተከትሎ ምእራብ አዉሮፓዊያን በ1884 ዓ.ም አፍሪካን በቅኝግዛት ለመቀራመት የአሳለፉት ዉሳኔ እና  የጀመሩት ወረራ በአድዋ ጦርነት ድልመመታት ምክንያት አለመሳካቱ ዐቢይ ምክንያቱ ሁኖ ይጠቀሳል ፡፡

2.በሀገራችን መልካ ምድራዊ አቀማመጥ ምክንያት የኃያላን ሀገሮች የንግድ መራኮቻ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቀይባህርን ፣ ሜዲትራኒያን ባህርን እና ዓባይን ከምንጨ ለመቆጣጠር ነዉ፡፡   የድርጊቱ አፈጻጸም በግብጽ እና በጣሊያን በኩል በጦርነት ወረራ በዚህ አልሰካላቸዉ ሲል በብሄረሰብ  ከፋፍሎ ሌሎችን ብሄረስቦች በዐማራዉ ላይ በጥላቻ ማሰለፍ እና እርስ በርስ  በማፋጀት በ እርዳት እና በህግ አስከባሪነት አሳበዉ እራሳቸዉን ማስገባት ነዉ፡፡ ፈጻሚዎች ኢትዮጵያ በአካሄደቻቸዉ ጦርነቶች ሁሉ በባንዳነት ያገለገሉ ባንዳዎች እና የባንዳ ዝርያዎች ናቸዉ፡፡ግባቸዉም በቅድሚያ ተከላካዩን ዐማራ አጥፍቶ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነዉ፡፡

አሜሪካኖች በዐለም ላይ የሚሰሩት ስራሁሉ ከራሳቸዉ ጥቅም ማስከበር ጋር ብቻ ነዉ  ለዚህም እንዲያመቻቸዉ የዉጭ ግንኙነት ፖሊሲዎቻቸዉ 1/ የአሜሪካንን ዜጎች ደህንነት ማስጠበቅ፡፡  2/  ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን መግንባት እና ማጠናከር፡፡ 3/ የሰባዊ መብቶችን መጠበቅ እና  ማስፋፋት፡፡  4/ የኢኮኖሚ እድገት እና ልማትን ማሳደግ እና ማስፋፋት፡፡ አካባቢያዊ ሰላምን እና ደህንነትን ማረጋገጥ የሚሉ ናቸዉ ፡፡ ይህን ፖሊሲያቸዉን ለማስፈጸም  እንደ ማስገደጃ የሚጠቀሙባቸዉ  በአሜሪካ ሥር  የተቋቋሙት   ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣የገንዘብ ተቋማት ድርጅቶች እና የዜና ወኪሎች  ናቸዉ፡፡

አሜሪካ የራሳዋን ፖሊሲ ለማስፈጸም በሶስተኛ ዓለም ሀገራት የራሰዋን ጉዳይ አስፈጻሚ የአሻንጉሊት መንግሥት ማስቀመጥ የማያቋርጥ ሥራዋ ነዉ፡፡ ለነሱ የማያገለግለዉን መሪ አምባ ገነን በማለት በዜና ወኪሎቻቸዉ ያዋክቡታል ተከታትለዉም ያስወግዱታል በአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ማለት ለአሜሪካ መንግሥት የማይመችማለት መሆኑ ነዉ፡፡አሜሪካ የምትከተላቸዉ ፖሊሲዎች ጣልቃገብነትን እና ነጥሎ ማጥቃትን ነዉ፡፡ በጣልቃ ገብነት ፖሊሲዋ ከ160 በላይ ሃገሮችን እንዳፈረሰች በታሪክ የተመዘገበ ሲሆን በግድያ ሙከራም እዉነተኛነቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም በፊደል ካስትሮ ከ600 በላይ የግድያሙከራ እንዳደረገች  ይነገርላታል፡፡የአሜሪካ የዉጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች አፈጻጸም አዉነተኛነት የሚለካዉ ለአሜሪካ በሚሰጠዉ ጥቅም ብቻ ነዉ፡፡ከዚህ ዉጭ እዉነተኝነትም ተቀባይነትም የለዉም ፡፡ለዚህ ነዉ ትህነግ ከ18 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን በጦርነት አሰልፎ ዐማራን እናአፋር ክልሎችን ህዝብ ሲጨፈጭፍ፣ ሲያሳድድ ፣ቤት ንብረት ሲዘርፈ፣ ሲተርፈዉም ሲያቃጥል የሰባዊ መብት ጠባቂ የተባለዉ አፉን ለጉሞ ዝም ያለዉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢ.ሕ.አ.ግ/ የተሰጠ መግለጫ

ምእራባዊያን አዉሮፓ ሀገሮች ዓላማቸዉ ለህዝቡ እድገት እና ብልጽግና የማያስብ ለነሱ ታዛዥ አሻንጉሊት መነግሥት መስርተዉ  ሀገር እየአደኸዩ ጥቂት ቤተሳብ ማበልጸግ እና ህዘቡ በምእራቡ  እርዳታ በመተማመን በራሱ እንደአይተማመን ማድረግ ነዉ፡፡ አማራ ቋሚ እና ጠንካራ ጠላቶቹን ከአወቀ መስራት የአለበትም ቋሚ እና ጠንካራ ሥራ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ብርቱ ባላንጋራ ብርቱ ያደርጋል እና፡፡ የአሜሪካኖች አሻንጉሊት መንግስት መሪ መለስ ዜናዊ በዐማራ ላይ የፈጸመዉን  ቀሳዊ እና መንፈሳዊ ጉዳት በመዘርዘር ሰለማያልቅ በጥቅሉ መለስ በዐማራዉ ላይ በዓለም ላይ በሚገኙ ፍጥረታት የሚፈጸሙ የግድያ እና የሥቃይ ዓይነቶችን በሙሉ በዐማራ ላይ ፈጽሞበታል ብሎ ማጠቃለሉ በማጠናከር ይገልጸዋል ብየ አምናለሁ ፡፡

ስለዚህ ዐማራዉን ከደረሰበት ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ጉዳት ለማዳን  የመለስን እና ቡድኑን  ሥራ ግልባጭ መስራትን ይጠይቃል፡፡ኢትዮጵያን ከጥፋት የሚጠብቃት ዐማራ ነዉ ብሎ ከአለቆቹ በተሰጠዉ ትምህርት አምኖ በእዉቀት ሳይሆን በእምነት የሚሰራዉ የዐማራ የቅርብ ጠላት የአሜሪካን እና የምእራብ አዉሮፓ ቅጥረኞች እና የባንዳ ዝርያዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ በቅድሚያ ዐማራን ማጥፋት ነዉ ብለዉ በዐማራዉ ላይ የዘመቱትን እስከ መጨረሻዉ እስከ ዘር ማንዘራቸዉ ለማጥፋት ዐማራዉ እራሱን በድርጅት አጠናክሮ እና በአንድ መስመር ተሰልፎ ዐማራን መነሻ ኢትዮጵያን መድረሻ በማድረግ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን በማሰባሰብ ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ትህነግን ከኢትዮጵያ ምድር የመሸኘትን ሳይሆን ጨርሶ  የማጥፋትን ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል ፡፡

የዐማራዉ  ችግር የኢትዮጵያ ችግር ፣ የኢትዮጵያ ችግር ደግሞ የዐማራዉ እና  የሌሎች ኢትዮጵያዊያን አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የቆሙ ነገዶችም ችግር ነዉ፡፡ በመሆኑም ዐማራነት እናኢትዮጵያዊነት አንዱ ካለአንዱ መኖር የማይችል የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸዉን አምኖ ለእድነታቸዉ ደህንነት በኢትዮጵያዊነት መታገል ያስፈልጋል ፡፡ ለዚህም ነዉ ብሄረሰቦች ለወልቃይት ዘመቻ እየተሟሟቱ የሚገኙት፡፡ የዐማራ ድርጅቶች መስራት የአለባቸዉ በክልል ለተወሰነዉ ዐማራ ደህንነት እናመብት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ በኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዐማራ ጭምር መሆኑን አዉቆ እና አሳዉቆ መሆን አለበት፡፡

ዐማራዉ ትህነግን ከኢትዮጵያ በአጭርጊዜ ነቅሎ ለመጣል የምትችለዉ   ሰዉን በአነጋገሩ፣ በአለባበሱ፣ በስያሜዉ፣ በእዉቀቱ፣ በማእረጉ  በድህነቱ፣ በሀብቱ፣ በበሽተኛነቱ፣ በለማኝነቱ፣፣ በእብድነቱ አምኖ በይሉኝታ፣ በርህራሄ፣ በእምነት ከመስራት ወጥተህ ማንንም ትልቅ ትንሽ ሳትል እየተከታተልክ በመጠየቅ በመፈተሸ ማንነቱን አዉቀህ በእዉቀት መሥራት ስትችል ብቻ ነዉ፡፡ ለአለህበት ዘመቻ በአጭር ጊዜ ዉጤታማ  ለመሆን የምትችለዉ፡፡ከአልሆነ ጊዜ ይወስዳል ፣ያሰለቻል፣ ያዘናጋል ምክንያቱም የትህነግን አባለት በሙሉ መለስ ያሰለጠናቸዉ ያልመነኮሰዉን መነኮስኩ ብሎ፣ያልቀሰሰዉን ቀሰስኩ ብሎ፣ ያላበደዉን አበድኩብሎ፣ ያላጣዉን አጣሁ ብሎ፣ በልመና አሰማርቶ ዐማራን በየአለበት እያሳደደ እየገደለ የዘርማጥፋት ስራን ያሰራ ስለነበረ ነዉ፡፡ለዚህም መረጃ የሚሆነዉ የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማድ እንዲሉ የትግራይህዝብ መሬት የተሸለ ቤት እና ንብረት እየአላቸዉ በልመና የተሰማሩ እጅግ በጣም ብዙ ትግሬዎች መኖራቸዉን  የትግራይ ክልል መስተዳድር ማህበራዊ ዘርፍ በጥናት አረጋግጦ  መሬታቸዉንም እንደሚቀሙ  ህግ ማዉጣቱን ነዉ ዶክተር ሰለሞን እቁባይ የሚያረዳን

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጎንደር - ክፍል ሦስት (ሥርጉተ ሥላሴ)

የዲሞክራሲ መነሻ መሰረቱ ህገመንግስቱ ነዉ፡፡ ህገመንግሥት ደግሞ  የህጎችሁሉ ምንጭ ነዉ ፡፡በመሆኑም  አሁን አዳዲስ ህገች እየወጡ እንደሆነ እየተገለጸ ነዉ ታዲያ ዐማራዉ ባልተሳተፈበት በሀገር በአጥፊዎች በወጣዉ ህገመንግስት የሚወጡ ህጎች ለዐማራዉ የሚኖራቸዉ ፋይዳ ምን?ሊሆን እንደሚችል የዐማራ ምሁራን እና ህዝብ ከወዲሁ ሊያስብበት ይገባል፡፡ ግብ ጽ አብዮት ከአካሄደ በኋላ በሌላ አምባገነን እጅ የወደቀዉ ቅድሚያ ባለመዘጋጀቱ ሲሆን ቱነዚያ አስቀድመዉ በመዘጋጀታቸዉ የተሳካ ሽግግር አድርገዋል ፡፡ አሁን በሀገራችን የሚታየዉ ለዉጥ የኢትዮጵያ መንግሥት አገር አቀፍ አባል ለመሆን ሲሆን  ሌላዉ ደግሞ የጎሳ አካባቢ አቀፍ አባል ለመሆን እንደሆነ የሥራ ሂደቱ ይናገራል፡፡ለዚህም የአዲሰ አበባን መዋቅር የሰዉ ሃይል አመዳደብ  መገምገምቢቂ መረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ሥልጣን የህዝብ ነዉብሎ የሚያምን መንግሥት ዉክልናን መንፈግ ለጊዜዉ ነዉ እንጂ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ ነዉ የሚሆነዉ፡፡

ዐማራዉ፡፡ ዲሞክራሲ የሚመጣዉ በህዝብ አስገዳጅነት መሆኑን አዉቆ  ለህዝብ በማሳወቅ ነገ የዛሬ ዉሳኔአችን ዉጤት እንደሆነ አምነን ነጋችን ለማሳመር በንቃት በርትተን መስራት አለብን፡፡ ህዝባዊ ቁጣ ከእለት ወደ እለት ተባብሶ የሰዉ ልጅ ትግስት ያልቃል በማለት ኦሪት ዘጽአት 23.6 እና ቅዱስ ቁርአንም ምእራፍ 3  አሊኤምራን ክፍል 3 ቁጥር 71 ተቅሶ ጋዜጠኛ ሙሉነህ አያሌዉ የህዳሴ አብዮት በሚለዉ መጽሃፉ በገጽ243 የተጠቀሰዉን አስታዉሶ መስራቱ ለህዝብም ለመንግሥትም ይጠቅማል ብየ አምናለሁ፡፡

ዐማራዉ ሁሉም ህዝብ የኛ የሚለዉ ህገመንግስት እና መሪ ለኖረን ይገባል በሚል እምነት የጋራ መነሻ እና መድረሻ ንድፈ ሃሳብ ፈጥሮ የጋራ Sሥርዓት  መፍጠር ለሁሉም የሚበጅ መሆኑን አምኖ ይሰራል ፡፡የዐማራዉ ሥነ ልቦና የሚገለጸዉ በአገራዊ ልብ ወለዶች በግል ታሪኮች በስነ ቃሎች እና ተረቶች ዉሥጥ ነዉ፡፡ ዐማራዉ እኔም እኛም የሚል ስነልቦና ያለዉ ሲሆን የኛ የሚለዉን ስነ ልቦና በአብዛኛዉ የተላበሰ ነዉ፡፡ ቢሆንም መጨፍለቅ እና በደቦ መወሰን አይስማማዉም ፡፡ ይህ ደግሞ እራሱን  ከማወቅ እና እራስን ከመግዛት የሚመጣነዉ፡፡ በዐማራ ድሃ እና ሀብታም አንድነትም ልዩነትም አላቸዉ በአንድነታቸዉ ድሃ በማንነቱ ከሃብታም አያንስም ሁለቱም በኩሩነታቸዉ አንድ ናቸዉ፡፡ ድህነቱን አይቶ ዝቅ የሚያደርገዉን አይቀበልም፡፡ዐማራዉ በቋንቋዉ ብዙ ነገሮችን ወካይ ናቸዉ ለምሳሌ በማተቤ አትምጣብኝ ሲል በአመነበት ሁሉ ሟች መሆኑን ለማሳወቅ ነዉ፡፡

አማራዉ በአባት እርስት እና በሚስት የለም ዋዛ በሚለዉ ስነልቦናዉ ላይ መለስ እና ቡድኑ ያሳደረዉን ስብራት እንዴት ያየዋል አሁንስ ምን እየተሰራ እንደሆነ እንዴት? ያዉቀዋል ፡፡አይፈሩም ይጠረጥሯል በሚል ይትባህልህ እየተመራህ የሚነገሩትን፣ የሚሰሩትን፣ የሚታዩትን፣ እየገመገሙ እናእየአጠኑ እንደ አስፈላጊነቱ መልስ ለመስጠት የዐማራዉን ዝግጁነት ይፈልጋል፡፡ለምሳሌ በባህርዳር ከተማ  የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ የስሜን እና የምእራብ  ክልሎች ጉርብትና፣ የርሳነ መስተዳድር እና አፈጉባኤዎች  በሚል ስያሜዎች በተደረገዉ ስብሰባ ላይ   በዶክተር ሙሉ ነጋ እና በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተነሱ ሃሳቦችመልክታቸዉ ምን እንደሆነ አማራዉ ሊያስብበት እንደሚገባ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የበድር አመራሮችን አስመልክቶ የወጣ መግለጫ - ከፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን

በዶ/ርሙ?ሉ ነጋ የተነሳዉ ሃሳብ እናንተ ዐማራዎች በኢትዮጵያ ዉስጥ የምትኖሩ ናችሁ እና እንደ ኢትዮጵያ ነዉ ማሰብ የአለባችሁ፡፡አለ፡፡‹ እናሳ ምን እናድርግ? የዐማራዉ ጥያቄ

በአቶ ሺመልስ አብዲሳ  የቀረበዉ ሃሳብ ዐማራ ክልል የክልላዊ ፍላጎቱን ለመጠበቅ ድርቅ ባለቁጥር ክልል ዉጭ የአሉ ዐማሮችን ጥቃትን ይፈጥራል፡፡አለ፡፡ እናሳ ምን ይሻላል?የዐማራዉ ጥያቄ   እነዚህ እና መሰል ሃሳቦችን ለአማርኛ ቋንቋ ባለቤት ለሆነዉ ዐማራ ወዴት እየአመሩ እንደሆነ እና የስብሰባዉም ዓላማ እና ግብ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ የሚሳነዉ ዐማራ አለ አልልለም፡፡

ዐማራዉ የፌደራል መንግስቱን እየአመኑ ከመስራት ይልቅ በራስ መተማመንን አጠንክሮ የራስን ችግር በራስ ለመፍታት እንደሚችል አምኖ ህግን ጠብቆ እና አስከብሮ የዐማራዉን ክልል እና ደህንነት አስከብሮ፣ ህዝቡን እንደየችሎታዉ እና  እንደአቅሙ አደራጅቶ በሁለገብ ልማት በማሰለፍ እየሰሩ ማሰራት ከመሪዎች ይጠበቃል፡፡  በሁለሜና ቸዉ በሙስና የተዘፈቁትን  በማጣራትአስወግዶ የመንግሥት መዋቅርን ከሙስና በጸዱ ሰዎች በመተካት የኢኮኖሚ ልማትን እናፖለቲካዊ ሁኔታዎችን እየተከታተለ የየድርሻዉን ጠንክሮ መስራት ከእየአንዳንዱ ዐማራ የሚጠበቅ ግዴታም  ኃላፊነት ነዉ፡፡

የዐማራ ምሁራን እና ህዝባዊ ድርጅቶች በአጠቃላይ የዐማራ ህዝብ ሥር የሰደዱ ጠላቶቻችን አሜሪካ እና ምእራብ አዉሮፓ መሆናቸዉን ጠንቅቀን አዉቀናል በሚሰሩት የጥፋት ስራቸዉም አረጋግጠናል ፡፡ስለዚህ  ኢትዮጵያን በነገድ ለመከፋፈል ለማጥፋት የተሰለፉ አገር አጥፊዎች  ከነዚህ ሀገሮች ጋር መገናኘት ለልማት ሳይሆን ለጥፋት መሆኑን ያለጥርጥር አምነህ በርትተህ ልትታገላቸዉ ግድ ይላል፡፡ለምሳሌ ኦነግ እና ኦፌኮ ሀምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም  ኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ የሽግግር መንግስት አዋጅ በሚል ስያሜ አዉጥቶ  ህጋዊ የህዝብ መንግስት በህዝብ ይሁንታ ሲደረግ እናበምርጫ እስኪመሰረት ድረስ ለ3 ዓመታት ተቋቁሟል በሚል ማወጁ፤ በማስከተልም ዶ/ር መራራ ጉዴና ወደአሜሪካ መሄዱ፣ብዙም ሳይቆይ ኦነግ ሸኔ እና ትህነግ አንድነት መፍጠራቸዉ ሁሉንም አሰባሳቢዉ አሜሪካ መሆኑ ትህነግ በጦርቱ ሲጠቃ  ትህነግ የኦነግን የበላይነት ተቀብሎ በዚሁ መከረኛ ዐማራ ላይ የሚዘመት ላለመሆኑ ዐማራ ምን ዋስትና ይኖረዋል ፡፡ ስለዚህ ዐማራ ወዲያማዶ ሁኖ ክፉሰዉ ተጣራ ወዲህ ማዶ ሆኖ ክፉሰዉ ወይ አለዉ ጎበዝ ተጠንቀቁ ይህ ነገር ለኛ ነዉ የሚለዉን የቋንቋ ይተባህልህን በመጠቀም  ማንኛዉንም እንቅስቃሴ በመከታተል እና በማጥናት የዉጭሀገር እና የዉስጥሀገር ልጆችህነ በማስተሳሰር በራስሀ ልጆች በራስህ ዘዴ ብቻ ትህነግን አጥፍተህ የዐማራዉን ህልዉና ጠብቀህ ኢትዮጵያን ለማዳን ብቁ መሆንህን አምነህ እና አጠንክረህ ልትታገል ግዴታ ወድቆብሃል ፡፡

ሙላት በላይ

1 Comment

  1. በጎንደርና በአፋር ወያኔ በገባባቸው ቦታዎች በሰውና በንብረት ላይ የፈጸመውን በደል ለተመለከተ መፈጠርን ያስጠላል። ምንም አይነት የሰው ስብ ዕና የሌላቸው አውሬዎች መሆናቸውን ተኩሰው ከገደሏቸው እንስ ሳትን ጭምር ማየት ይዘገንናል። ላሞች፤ ፈረሶች፤ የጭነት በቅሎዎችና አህዪች፤ ፍየልና በጎች ውሻዎች ስይቀሩ በጥይት ተበሳስተው ከብቶች ሲለቅሙበት በነበሩበት ቦታ ወድቀው ወድቀው ማየት እግዚኦ ያስብላል። አሜሪካና አውሮፓ ለምን ይህን ቡድን የሙጥኝ እንዳሉ ጭራሽ አይረዳኝም። ከደረሰኝ መረጃ ጥቂቱን ላካፍላችሁ።
    ማይጸብሪ – በድንገት ገብተው ከተማውን ከከበቡ በህዋላ ምንም አንነካችሁም በማለት ወጣቶችን ለስብሰባ ጠርተው በማሰለፍ ነበር የረሸኗቸው። ይህ የተመለከቱ የከተማዋ ኗሪዎች በድንጋጤ በያሉበት ነፍሳቸውን ለማዳን ሲሮጡ የተወሰኑ ሴቶችን በመያዝ አይዞአችሁ አንነካችሁም ምግብ ታበስሉልናላችሁ በማለት ያስቀሯቸዋል። ወዲያ ከተማው ባዶ መሆኑ ሲያውቁ የሚያቃጥሉትን አቃጥለው፤ የሚዘርፉትን ጭነው እንጀራ ጋጋሪዎች ብለው ያስቀሯቸውን ሴቶችም ረሽነው ከገቡት ወደ 100 የሚሆኑት ወያኔዎች ሌላ ሃይል ድጋፍ ለመስጠት ትንሽ ሃይል በማይጸብሪ ከተማ በመተው ይንቀሳቀሳሉ። ድርጊታቸው ልባቸውን ያቃጠለው ከተሜዎችና የገጠር ሰዎች ተሰባስበው በመክበብ ውጊያ ከፍተው ገለውና ሞተው ከተማውን ሲያዪት ከላይ ያልኩት ነገር መሆኑ ከወደቁት የሰውና የከብት የንበረት ውድመት ይረዳሉ።
    አፋር ግንባር – እያወቁ ተኩስ በመክፈት ተጠልለው የነበሩ ሴቶችና ህጻናትን ሲገድሉ ለምን እንዲህ እናረጋለን ብሎ ከመካከላቸው የጠየቀ አንድ አሁን ምርኮኛ የሆነ የመቀሌ ወጣት አይ ዝም ብል የተነገረን ያገኛችሁትን ሃብትና ንበረት፤ እንስ ሳት ሰው ድልድይ ሁሉ ማውደም መጫን የሚችለውን ጭኖ ወደ ትግራይ ማጓጓዝ ነው። ስለሆነም እንደዚህ ያለ ጥያቄ መጠየቅ ያስመታል ይለዋል የሃይል መሪው። ልጅ ብልጥ ስለነበር ተሽሎኩልኮ በመሄድ ለአፋር ሃይል እንጅን ሰጠ። መረጃ ከዚያ የመነጨ ነው።
    ንፋስ መውጫ ከተማ – ዙሪያው ሁሉ ፈራርሷል። ባንኩ፤ የግልና የመንግስት መ/ቤት ሌሎችም ሁሉ ተዘርፈዋል። የሚገርመው የመብራትና የስልክ መገናኛ ምሰሶዎችንና ገመዶችን ሳይቀር ነው የቆራረጡት ያፈራረሱት። በዝርፊያው የሚጫነው ወደ ትግራይ ተጭኗል። የሚገደለው ተገድሏል። በከተማዋ አቅራቢያ ባለ ሜዳ ላይ እንስ ሳት በጥይት ተበሳስተው አሸልበዋል። በዚያች ከተማ የሆነውን ያየ ሰው የሰው ልጅ እንዲህ ያለ ጭካኔ በወገኑ ላይ ይፈጽማል ብሎ መገመት ይከብደዋል ይላል ግንባር ያለ ሰው ባጫወተኝ መረጃ መሰረት።
    ውጊያው በወያኔ ከአፋርና ከአማራ ክልል መውጣት ብቻ መቆም የለበትም። ወያኔን መቀሌ ድረስ ገብቶ መቀጥቀጥ ነው። እነዚህ ሰዎች በተገኙበት መገደል ያለባቸው አሸባሪዎች ናቸው። አንድ ነገር ግን ይገርመኛል። ሰው በአፉ ከሚለፈልፈው መረጃ ይልቅ ወያኔ ያደረገውን በደል በፊልምና በፎቶ ማስቀረቱ የበለጠ ለመረጃነት ጠቃሚ ነበር። ግን ዝም ብሎ መለፍለፍ የቃል ክምር ብቻ የሆነ ጋዜጠኛ ለምንም አይጠቅምም። መረጃ ጊዜ ሳያልፍበት፤ ሰውን በማናገር የሞተን የፈረሰን፤ የቆሰለን ወዘተ ዶኮሜንት አድርጎ ለህዝብና ለዓለም ማሳየት ነው። በአፍራ ከ 200 በላይ ሰዎች በወያኔ ተገድለዋል። በምን የተነሳና በቪዲዪና በአይን ምስርክሮች ድምጽ የተደገፈ መረጃ ያልቀረበው? ለመቅበር እንደምንቸኩለው መረጃ ለመሰብሰብም መቸኮላ አስፈላጊ ነው። የወያኔ በደል ሰማይ ከደረሰ ዘመናት ያለፈ ቢሆንም የአሁን ግን እጅግ ዘግናኝና ከሰው ባህሪ ውጭ የሆነ የአራዊት ተግባር ነው። ለነገሩ ሲፈጠሩ ጀምሮ በሰው ደም የተቃመሱ እብዶች መሆናቸው የታውቀ ቢሆንም እንዴት ከመቀሌ ውጭ ወጥተው በአፋርና አማራ ከተሞች የመከራ ዝናብ እንዲያዘንቡ እንደተፈቀደላቸው ምንም አይገባኝም። የፌዴራል መንግስት፤ የክልል መንግስት፤ የውጭ ሃገር እርዳታ ይደርስልናል ብሎ ከማሰብ ይልቅ ዛሬም ቢሆን ወደፊት ሴት ወንድ ልጅና ሽማግሌ ሳይል ተደራጅቶና ታጥቆ እነዚህ ሰው ጠላሽ አረመኔዎች መፋለም ይገባል። ወያኔ እያለ ኢትዮጵያ ሰላም አትሆንም። ያው ጌታቸው እንዳለው ኢትዮጵያን ሲኦል ሊያወርዷት አይደል የሚፈልጉት። በውጭ ሃገር የትግራይ ፌስቲቫል እየተባለ ሲዘፈንና ሲጨፈር ማየት ይሰቀጥጣል። በምድሪቱ የሚደርሰውን መከራ ሰው ሆኖ በሰውኛ እይታ ለተመለከተ ግፍ ያለ ገደብ ይፈሳል። በዘር ለተቃመሰው ጠባብ ብሄርተኛ ደግሞ ካለራሱ ዘር ሌላው ሰው ስለማይመስለው የሚያስበው በዚሁ ካርቶን ጭንቅላቱ ነው። የሚያስጨፍር ሳይኖር መጨፈር። ወይም እንደ ወያኔው የሙት ቁልፍ ደጋፊ ስታሊን ” መለስ ሲሞት የኢትዮጵያን ቁልፍ ይዞ ሞተ” ለዚያ ነው ዛሬ እንዲህ ያለ ጉድ የመጣው ይለናል። ውሻ በበላበት ይጮሃል ነው እንጂ መለስ ሲያንቀላፋ የተጎዳው ወያኔ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለችም። አረመኔው ወያኔ ጅራቱን እያወዛወዘ ሰላም የሚለውን የቤት ውሻ ተኩሶ ገድሎ የሚፎክር የጨካኞች ስብስብ ነው። በኢትዪጵያ ምድር ሁለቱን የጣሊያን ወረራ ጨምሮ እንደ ትግራይ በቀሉ ወያኔ ያለ የጨካኞች መንጋ በምድሪቱ ተፈጥሮ አያውቅም። ከሰው ስብ ዕና የወጡ አውሬዎች ናቸው። ይህን ቡድን ለመደገፍ ነው የትግራይ ፌስቲቫል፤ ሙዚቃ በሱዳን፤ እና በአረብ ሃገራት ክፋትን በመዝራት እውነተኛ ኢትዮጵያዊያን እንዲጠሉና ከሃገር እንዲባረሩ የሚያደርጉት። ሴራቸው ባህር ተሻጋሪ ነው። የዝርፊያና የግድያ መረባቸው የተወሳሰበ ነው። ኢትዪጵያን እወዳለሁ፤ ለሃገሬ ቁሜአለሁ፤ ዘርና ቋንቋ አይገድበኝም የሚል ወገን ሁሉ ከእነዚህ የመከራ ዝናቦች መራቅ ይኖርበታል። ከፍለውና አስከፍለው፤ መርተውና አስመርተው በተለያዪ መንገዶች እልፍ የሃገራችን ልጆች በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ አስገድለዋል። አሁንም ለበለጠ ክፋት ተዘጋጅተዋል። በተለይ ለአማራ ህዝብ ያላቸው ጥላቻ ይህ ነው አይባልም። ጥላቻቸው ትላንትና ዛሬ የጀመረ ሳይሆን 50 ዓመት በተጠጋ የፓለቲካ እድሜአቸው የትግራይን ህዝብና የውጭ ሃይሎችን የአማራ ጥላቻ ግተዋቸዋል። ቆፍጠን። ነቃ፤ ማለት ተገቢ ነው። ወያኔና ደጋፊዎቻቸው አማራን ለማጥፋትና ለማጥላላት አይቦዝኑም። አማራው ራሱን ከመከላከል የበለጠ ሌላ የሚያድነው ምድራዊ ሃይል የለም። ወያኔ ያፈረሰውን ቤ/ክርስቲያን፤ መስጊድ፤ ት/ቤቶች፤ የህክምና ተቋማት ተመልከት። ይህ ሆን ተብሎ የተሰራ ድርጊት ነው። ጀግና አይፎክርም። ገደልኩ ብሎ አያቅራራም። ዝም ጭጭ ብሎ ሁሉ በመረጃ እየያዙ ጠላትን ማንኮላሸት ነው። ከወያኔ ጋር እርቅ አርጌ እኖራለሁ የሚል አማራ ደንቆሮና የእነርሱ አገልጋይ ብቻ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share