አሜሪካ በኤርትራ ጦር አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች

240002404 386153702898026 6598256408767732482 nአሜሪካ የኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል ፈጽሟል ባለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት በጦሩ ዋና አዛዥ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች።

ማዕቀቡ በኤርትራ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ የተጣለ ነው፡፡
ማዕቀቡን የተጣለው በአሜሪካ የፌዴራል ግምጃ ቤት (ትሬዠሪ) በኩል ሲሆን አዛዡ በአሜሪካ ያላቸው ሀብት እንዲታገድ እንደተወሰነ ግምጃ ቤቱ በድረገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
አሜሪካ በጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ የሚመራው የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሟል፤ ሴቶችን ደፍሯል እንዲሁም ወጣቶችን እና ንጹሀን ዜጎችን ቤት ለቤት በመግባት ገድሏል ስትል ከሳለች።
የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ካደረገ በኋላም ተመልሶ ወደ ትግራይ ክልል ገብቷል የሚለው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ጦሩ በአስቸኳይ ወደ ኤርትራ እንዲመለስ ጠይቋል።
ውሳኔው አሜሪካ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ላላት ቁርጠኝነት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችልም ነው ግምጃ ቤቱ ያስታወቀው።
አሁንም ጦርነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው የሚለው የህ ተቋም በቀጠለው ግጭት ምክንያት እርዳታ የሰብአዊ መብት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ማድረስ ባለመቻሉ ሁሉም አካላት ግጭቱን እንዲያስቆሙ ጠይቋል።
ኤርትራ ማዕቀቡን በተመለከተ እስካሁን የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡
FBC
ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረገው ዘረፋ መቀጠሉና 3 ወገኖቻችን መቁሰላቸው... በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የፓርቲ ፖለቲካ ሳይሆን ሕዝባዊ ትግል እንደሚያስፈልግ መገለጹ... ገዢው ፓርቲ አንዳርጋቸው ጽጌን ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ማዋሉን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መቃወማቸው.. ኢትዮጵያ ዛሬም በአቶ መለስ የሙት መንፈስ እንደምትመራ የአገዛዙ ሚዲያ ዘገባ ማመልከቱ ና ሌሎችም

1 Comment

  1. የጆርጅ ፍሎይድን ገዳይ ባግባቡ ያልዳኘ አገር ስለሌላው የማውራት ሞራል አለው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share