ህብረት ለአገራችን ኢትዮጵያ የህልውና ዘመቻ ህብረት – ዘመቻ ህልውና

5655555

አገራችን ኢትዮጵያንና ዜጎቿን ለሶስት አስር ዓመታት ያህል ለከፍተኛ ዕልቂትና ውስብስብ ችግር የዳረገው ህወሀት በረዥም እልህ አስጨራሽና ሀገር አቀፍ ትግል ከመንበረ ስልጣኑ ቢወገድም፤ ኢትዮጵያውያን ለሰላምና አገርን ለማረጋጋት ሲባል የቸሩትን ይቅርታ እንደ ፍርሀት በማየት ከጥቅምት ፳፻፲፫ ጀምሮ ጦርነት በማወጅ በትግራይ አጎራባች ዐማራና አፋር ኢትዮጵያውያን እየተካሄደ ያለውን ከፍተኛ ዕልቂት፣ ውድመትና ቀውስ እናወግዛለን።

ይህን በድንገት የተሰነዘረበትን ዘግናኝ ጥቃት መከላከያ ሰራዊታችን፤ የዐማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ ተቋቁሞ ድልን ተቀዳጅቶ በስኬታማ የህግ ማስከበር ዘመቻ ህወሃት መቀሌ ከመሰረተው የሽብር ማዕከል ወደ ቆላ ተምቤን እንዲሰደድና እንዲፈረጥጥ ተገድዶ ኣንጻራዊ ሰላም ባካባቢው ቢሰፍንም የተላላኪያቸውና ሰራ ኣስፈጻሚያቸው ህወሃት የበላይነት መወገድ የተከፉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከባድ ተፅዕኖ በማሳደርና ጣልቃ በመግባት፤ መሽጎ የነበረው ነቀርሳ ዛሬ እስከ ጉና ተራራና ወረታ ድረስ እንዲስፋፋና ከፍተኛ ዕልቂትና ውድመት እንዲፈጽም ኣስችለውታል። በዚህም ምክንያት በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለዚህ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳና ግብረ አበሮቹ የማያዳግምና ግልፅ የሆነ መልስ በመሰጠት ላይ ናቸው።  በዘረኝነት አስተሳሰብ አገር ወዳድነቱን አጥፍተነዋል ያሉት ወጣት በኔ ትውልድ አገር አትፈርስም፤ ሉዓላዊነቷም አይደፈርም ” በማለት ከዳር እሰከ መሀል፤ ከምሰራቅ እሰከ ምዕራብ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ የህልውና ዘመቻውን ጥሪ ተቀብሎ በመዝመት፤ ለህወሀት ድፍረትና እኩይ ኣላማ ተገቢውን መልስ በመስጠት ወረራውን እየመከተ ይገኛል። ወጣቱ ዘማች ህዝባዊ ሀይል ከአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት፣ ከየአካባቢው ከዘመቱት ልዩ ሀይል አባላትና ዘመኑ አምጦ ከወለዳቸው አርበኞች ጋር በመሆን ህይወቱን፣ አጥንቱንና ደሙን እየገበረ መሆኑን ተረድተናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጥጋበኞቹ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሱማሊኛ ሙዚቃ በሸራተን ሲደንሱ የሚያሳይ ቪድዮ

እኛም፤ በምዕራብ አውስትራሊያ ኗሪ የሆን አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን 21 August 2021 ኣስቸኳይ ህዝባዊ ስብሰባ በማድረግ እየተከፈለ ላለው ታላቅና አገር አቀፍ መስዋዕትነት በደጀንነት ለማገዝ፤ አሰፈላጊውንና አቅማችን የሚፈቅደውን የሞራል፣ የገንዘብና የዲፕሎማሲ ኣስተዋጽዖ ለማድረግና ቀጣይና ጠንካራ የሆነ ድርጅታዊ መዋቅር በመፍጠር የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነውን ህወሃት ላንዴና ለመጨረሻ ከምድረገፅ ጠፍቶ የሃገራችን ሉዓላዊነት የሚከበርበትን የህልውና ዘመቻ ለመሳተፍ በመግባ ባት ተፈናቃዮችና ቁስለኞች የሚረዱበት ወደ ሰላሳ ሽህ ኣውስትራሊያን ዶላር $30,000.00 AUD ቃል ገብተናል። ገንዘቡም በዘመቻ ህልውና ህብረት ኮሚቴ በመሰብሰብ ላይ ይገኛል። ውጤቱንም በቅርብ እናሳውቃለን።

 

Contact – የህልውና ዘመቻ ህብረት ነሀሴ ፳፻፲፫ ማርእሸት መሸሻ ሊቀ መንበር mareshetmeshesha@gmail.com +61459462377

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share