ማኅበረሰቡ ከሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የመከላከያ ሚኒስቴር አሳሰ

getenet

አማራ ክልል ሰርጎ የገባው የአሸባሪው ህወሀት ታጣቂ ከአማራ ሚሊሻና ልዩ ሀይል አቅም በታች መሆኑን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። አሸባሪው ህወሃት እስካልጠፋ ድረስ “ወደፊትም የሀሰት ወሬና ማወናበድ አይጠፋም ህዝቡ ከዚህ ውዥምብር መውጣት አለበትም” ተብሏል።
የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሰራዊት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
አሸባሪው ህወሓት በራያ በኩል በጉባ ላፍቶና ሀብር ወረዳዎች በአካባቢው ህዝብ የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እየጣለ መፈርጠጡን ገልጸዋል።
የአማራ ሚሊሻ የማረካቸውን የህወሃት ሰርጎ ገቦች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረከበ መሆኑን ጠቁመው፤ የማረኩትን የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ራሳቸውን እንዲያጠናክሩበት መደረጉን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የደረሰበትን ኪሳራ መቋቋም አቅቶት የፈረጠጠው የአሸባሪው ሀይል ወደ ጋሸና፣ ተኩለሽና ቁልመስክ በመሸሽ በለመደው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን እያወናበደ መሆኑን ገልጸዋል።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን እስካልጠፋ ድረስ የሀሰት ወሬና ማወናበድ ስለማይጠፋ ህብረተሰቡ ህጋዊ ከሆነ የመንግሰት አካል የሚሰጠውን መረጃ ብቻ በመከተል ከውዥንብሩ መውጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በተከዜ በኩል በከፈተው ጥቃት ከፍተኛ ኪሳራ ስለደረሰበት ካሁን በፊት እንዳደረገው አስከሬን በሲኖ ትራክ ጭኖ መሄድ አልቻለም።
ከዚህም ባለፈ ምንም ዓይነት የውጊያ ስልት የማያውቁ ንጹሃንን በግድ ወደ ትግል በማስገባት ተከዜ ላይ የውሃ ሲሳይ ሆነው እንዲቀሩ ማድረጉን ጠቁመው፤ በውጊያ የሞቱትን መቅበር ስላልቻለ አስክሬናቸውን ተከዜ ወንዝ ላይ እንደጨመረ ተናግረዋል።
ይህ እኩይ ድርጊቱ አልበቃው ብሎ በለመደው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በተሳሳተ መረጃ “አለም አቀፉን ማህበረሰብ ጭምር ማወናበድ ጀምሯል” ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉዑሽ -ከአዲስ አበባ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ዛሬ ልደታቸው ነው

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share