ቀደም ባለዉ ጊዜ አሳምነዉ ጽጌ በባህር ዳር መፈንቅለ መንግስት አቅዶ ለአዲስ አበባዉ ኦፕሬሺን መሳፍንት ጥጋቡን መድቦ የአማራ ግዛትን መፈንቅለ ክልል እራሱ በመምራት የአማራ አመራሮችን መግደሉን በብሄራዊ መገናኛ ተነገረን። እንዲህ ለመያዝ ለመጨበጥ መላ ቅጡ የጠፋ ነገር ከተነገረን በሗላ መሳፍንት ጥጋቡ ሳእረ መኮንንን ገድሏል ተብሎ ኮለኔል ጽጌ አለማየሁ በልቅሶም በማስመሰልም የመሰረተችዉን ጥልፍልፍ በመጠቀም የመሳፍንት ጥጋቡ አንገት እንደ መጥምቁ ዮሀንስ ተቆርጦ እንዲሰጣት አጥብቃ ስትወተወት ከቆየች በሗላ ሞቱ ቀርቶ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበት ወደ ወህኒ ተወረወረ። አንባቢ ጠንቅቆ እንደሚያዉቀዉ መሳፍንት ጥጋቡ አልገደልኩም ንጹህ ነኝ እያለ እየወተወተ በኢትዮጵያ የፍርድ ተቋም መግደሉ ተወስኖበት እስር ቤት ወርዷል። እንዲህ አይነቱ ነገር የተለመደ ለመሆኑ ሰሞኑን አንድ እናት የሚወዷትን የእንጀራ ልጃቸዉን ገድለዋል ተብለዉ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ከተፈረደባቸዉ በሗላ አራት አመት ከታሰሩ በሗላ ሟች የተባለችዉ ትዳር መስርታ ልጅ ወልዳ አለሁ ብላ ብትመጣም መኖሯም ከተረጋገጠ በሗላ ተጨማሪ 4 ወር ጠጥተዉ ያለ ምንም ካሳና ይቅርታ መለቀቃቸዉ ተሰምቷል።
ያሳዝናል በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያን ወታደር ያረደ ለዳግም ጥፋት ወደ በረሀ ገብቶ መከላከያዉ ህይወት ሰዉቶ ለፍርድ ይቀርባል ብሎ የያዘዉ አብረሀም ገ/መድህን የተባለ የትግሬ ዘፋኝ የትግራይ አመራር አንድም ቀን ሳያስረዉ በተያዘበት እለት ወደ ቤቱ ፌሺታ አድርጎ በክብር ሸኚቶታል። አገኘሁ ተሻገር ይህን ነገር ይሰማ አይስማ ማወቅ አይቻልም ስለሱና ስለ ድርጅቱ ቀደም ሲል ምልከታችንን ስላጋራን ለመሳፍንት ጥጋቡ ስስ ልብ ይኖረዋል ብለን በፍጹም አናስብም ።
የዉስጥና የዉጭ የዜና ምንጮች በተለያየ ሚዲያ ላይ እንዳመላከቱት ሳእረ መኮንን አንድም ሚስቱ አንድም ከገዛይ አበራ ጋር በተደረገዉ የተኩስ ልዉዉጥ መሞቱ ይታመናል። ሳእረ፤ ሳሞራ፤አዜብ መስፍን፤ አርከበ እቁባይ የከተማ ኑሮ ለምደዉ ወደ መቀሌ ቢጠሩ ሞኝህን ፈልግ በማለታቸዉ በዚህ ቂም ተይዞባቸዉ ሰብሀት ነጋ ጥርስ ነክሶባቸዉ ቀን ሲቆጠርላቸዉ እንደነበር ግልጽ ነበር። ያም ማለት ልባቸዉ ከህወአት አልራቀም።
ሳእረ መኮንን ከኤርትራ ጋር ሰላም ሰፍኖ ትግሬዎችም በአልጀርስ ኢትዮጵያን ያለ ተደራዳሪ አስቀርተዉ ፍርድ ቤቱም የትግሬን ግዛት ለኤርትራ ሰጥቶ በዚህም ዉሳኔ ስዩም መስፍን፤መለሰ ዜናዊ፤ሳሞራ የኑስ አጨብጭበዉ ካስረከቡ በሗላ ሰላም ሰፍኖ እያለ የ10 ሚሊዮን ዶላር የመከላከያ መሳሪያ ወደ ትግሬ መላኩ ምን አስቦ እንደሆነ መገመት የሚከብድ አይሆንም። ዛሬ በህይወት ቢኖር ሰልፉ ከማን ጋር እንደሚሆን ግልጽ ነዉ።ሳእረ መኮንን፤ጽጌ አለማየሁ፤ሳሞራ የኑስ፤አረጋዊ በርሄ፤አርከበ እቁባይ የኢትዮጵያን ወጣት የፈጁ ፤የክፉ ተምሳሌዎች፤ የኢትዮጵያና የአንድነቷ ጠላቶች መሆናቸዉን ወገን ላፍታም መርሳት አይገባዉም። ታዲያ ወንድሞቻችንን ፈጅተዉ ለኢትዮጵያ ለዋልነዉ ዉለታ እያሉ ሲያላግጡ ማየት ህዝባችንን ምን ያህል እንደናቁት በግልጽ ያሳያል።
በእንጻሩ መሳፍንት ጥጋቡ አንድ ደካማ እናቱ እያለቀሱ ጥሎዋቸዉ ሀገሩን ለማገልገል ወደ መደበኛዉ ጦር በሀገር ፍቅር ስሜት የተቀላቀለ ወጣት ነበር። ከላይ የተጠቀሱት የሀገር ገዳዮች በተዘረፈ ገንዘብ እስከ ወንጀላቸዉ ተንደላቅቀዉ ሲኖሩ ለመሳፍንት ጥጋቡ እንዲህ የተዛባ ፍርድ በፍጹም ተገቢ አልነበረም። ለመሳፍንት የተጓደለዉ ፍርድ ለሁላችንም የተጓደለ ነዉ። ዛሬ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አንድነትን ስላጠፉ ሳሞራ የኑስ፤አረጋዊ በርሄ፤ጽጌ አለማየሁ፤አዜብ መስፍን ከቤተ መንግስት ባልተናነሰ ቤት በታክስ ከፋዩ ገንዘብ ወይም በሰረቁት ሀብት ሲኖሩና ልዩ ጥቅም ሲያገኙ የመሳፍንት ጥጋቡ እናት ልጃቸዉ ዉሀ እንዳያቃብላቸዉ አለሁ እንዳይላቸዉ የወደቀ ቤታቸዉን እንዳያቃናላቸዉ ጠዋሪ አጥተዉ እልም ባለ ገጠር ዉስጥ በቤተ ክርስቲያን እየተመጸወቱ ይገኛሉ። በዚህ ሳያበቃ መሳፍንት ጥጋቡም ምስጢር ሊያወጣ ይችላል ተብሎ በሳእረ ገዳዮች ተመትቶ በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ መገኘቱን የጎበኙት መስክረዋል። ለሀገሩ በማገልገሉም የወደፊት ኑሮዉን በመከራ እንዲገፋዉ ተደርጓል። የሞተለሺ ቀርቶ የገደለሺ በላ ይሏል ይህ ነዉ።
መሳፍንት ጥጋቡ የኢትዮጵያ ወታደር እንጂ የክልል ወታደር አይደለም ከላይ እንዳመላከትነዉ ኮለኔል ጽጌ ያላቸዉን ኔት ዎርክ በመጠቀም በጥይት መትተዉ አስመትተዉ ይባስ ብለዉ ፍርድ አዛብተዉበት ወደ እስር አስወርዉረዉታል ፈጣሪ ፍርዱን እስኪሰጥ፡፡ የትግሬ ፋሺስቶች ነገ እንደሚፈቱ ቅንጣት ያህል ጥርጥር አይኖርም ወደ ፍርድ ቤት ከቀረቡም በስልጣን ዘመናቸዉ በሰረቁት ገንዘብና በፈጠሩት ጥልፍልፍ ካንበሳ መንጋጋ ፈልቅቆ የሚያወጣቸዉን ስርአት አዘጋጅተዋል። ከዚህ ሁሉ ነጻ የሆነዉና በእናቱ የገዳም ጸሎት ፍትህን የሚጠብቀዉ መሳፍንት ጥጋቡ ብቻ ይሆናል። ዛሬ ላይ ብንከዳም በተለያየ ጊዜ ለበቀለ ገርባ፤ለእስክንድር ነጋ፤ለአንዱአለም አራጌ……ጩኸናል። ሰዉ ሰብአዊ ክብር ሲነፈገዉ ሲበደል ሰብአዊ የሆነ ፍጡር ሁሉ አብሮት ሊቆም ይገባል። ያደረጋችሁትን ምስኪን ዜጋ ባስቸኳይ ለቅቃችሁ እንቅልፍ እንድተተኙ በሰብአዊነት ስም እንጠይቃለን። አጣዬን፤ ሻሸመኔን በቁሟ ያጠፉና በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች የወገንን ደም ያፈሰሱ ዛሬ በማእረግና በሀብት ሲብነሸነሹ እንደ መሳፍንት ጥጋቡን የመሳሰለ ተከላካይ የሌላቸዉ ወገኖች ግፍ ሲፈጸምባቸዉ ማየት በእጅጉ ያሳዝናል። ትላንት ኢንጂነር ስመኘዉ በጠራራ ጸሀይ ሲደፋ ዘይኑ ጀማል እያላገጠ መግለጫ ከመስጠቱም በላይ ጠ/ሚኒስተሩም ምንም ደንታ ሳይሰጣቸዉ እንደማይሆን ሁኖ ታልፏል። የቃዬል ደም ወደ አምላክ እንደጮኸ የኢንጅነር ስመኘዉም ደም ወደ አምላኩ ይጮኸል በዚህ ጉዳይ የተሳተፉትንም እረፍት ይነሳል።፡በእርግጥ አገሩ የደም መሬት ሁኗል ግፍንም ተለማምደነዋል። እንደ መሳፍንት ጥጋቡ ህይወታቸዉን ላገራቸዉ የሰጡ ታላላቅ ዜጎች ሲወድቁ ዝም ብሎ መመልከት የጥሩ ዜጋ ስነ ምግባር ባለመሆኑ ግፍን የመቃወም ለተበደለ የመቆምን ባህል አዳብረን ወገን የሌላቸዉን ዜጎች መታደግ የኢትዮጵያዊነት ከፍታ በመሆኑ ወገን ከተበዳዮች ጎን ይቁም በማለት ይህችን ጽሁፍ ወደ አንባቢ ልኬያለሁ። በዚህ አጋጣሚ እስክንድር ነጋ፤ ታዲዮስ ታንቱ፤ በወለጋ የታገቱት ወጣቶች ጉዳይ ከህዝብ አእምሮ እንዳይደበዝዙ በማለት ጽሁፌን እቋጫለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር [email protected]