በዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ መሰረት በማይካድራ 740 በላይ ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈው የተገደሉበት ዛሬ 90ኛ ቀኑ ነው። በዚች ከተማ በአብዛኛው የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ የተጀመረው ጥቃት እስከ ሌሊት ድረስ ቀጥሎ እንደነበር የዓይን እማኞችን ጠቅሰው የሰብዓዊ መብት ድርጅቶቹ ቀደም ብለው ባወጧቸው ሪፖርቶች ይፋ አድርገዋል። የዚህን ሪፖርት ጫፍ ተከትሎ ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ወደ 950 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ማይካድራ የተጓዘው የአሜሪካ ድምፅ የሐዋሳ ዘጋቢ ዮናታን ዘብዲዮስ ተከታዩን የቪዲዮ ዘገባ አሰናድቷል። /VOA