የዘር ማጥፋት (Genocide) ዋነኛው መሳሪያ ዝምታና ወንጀሉን በስሙ አለመጥራት ነው!

                                            የአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም       ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ዩ.ኬ

በአማራ ማህበር ዩናይትድ ኪንግደም እና ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በጋራ የተዘጋጀ በዙም የተቃውሞ ሰልፍ አማራ ላይ የሚፈፀመውን መንግሥታዊ ጭፍጨፋ እንዲቆም የተሰጠ የአቋም መግለጫ።

የዘር ማጥፋት (Genocide) ዋነኛው መሳሪያ ዝምታና ወንጀሉን በስሙ አለመጥራት ነው!

  • በአገራችን ኢትዮጵያ የሚፈፀመው ዘር ተኮር ጥቃት በጠ/ም አብይ አህመድ አሊ መንግስት የተደገፈው የአማራን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፤ ማፈናቀል እና ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲቆም እና በዚህ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ ወንጀለኛ የኦሮሞ አክራሪዎች እና የብልፅግና ፓርቲ የመንግሥት መዋቅር አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።
  • በኦሮምያ ወለጋ ሆሮጉዱሩ፤ ቤኒሻንጉል መተከል፤ ጉራፈርዳ፤ ማይካድራ እንዲሁም በመከላከያ አባላት ላይ የተፈፀመው በዘር ለይቶ ጭፍጨፋ (Genocide) ወንጀል የተሳተፉ የኦነግና ትህነግ አክራሪ የፖለቲካ አደረጃጀቶች እና ግለሰቦች በሽብርተኛ መዝገብ ውስጥ እንዲገቡና ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታገዱ፤ በሰሩትም ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ እንጠይቃለን።
  • ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ከተፈለገ የአማራ ህዝብ ያልተወከለበት የኦነግና ትህነግ አማራ ጠል የሆነው ህገመንግሥት እንዲሰረዝና፥ በዚህም ህገመንግስት መሰረት የተቋቋመው ህዝብ አጫራሽ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ተወግዶ ህዝብ የተወያየበትና ያመነበት ህገመንግስት እና አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲመሰረት እንጠይቃለን።
  • የአማራ ተወካይ በሆነው አብን ላይ የሚደረገው ማወከብና ማሸማቀቅ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የአብይ አህመድ ተረኛው የኦሮሙማ መንግስት (የብልፅግና ፓርቲ)፤ አማራ ጠል የሆነው አክራሪው የኦነግ እና በኦነግ መንፈስ የተደራጁት የኦሮሞ ፓርቲዎች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን።

 

  • ወልቃይት እና ራያ:- በግፍ የተነጠቀውን ማንነቱን በአማራ ህዝብ መራር ትግል ከተመለሱ በኋላ በአማራ ክልል መተዳደራቸውን እየደገፍን፤ ለዘለቄታው ዋስትና በፌደሬሽን ምክር ቤቱ ተወስኖ በቋሚነት በአማራ ክልል የጎንደርና የወሎ መስተዳደር ሥር ወደነበሩበት እንዲካተቱ እንጠይቃለን።

 

  • በመተከል ዞን የሚደረገው የማያቋርጥ የአማራ ህዝብን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፤ ማፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም እና የቤኒሻንጉል ክልል ፈርሶ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግስት እና የአማራ ክልል መንግሥት በጊዚያዊነት እንዲተዳደር ፥

ለዘለቄታው ደግሞ የመተከል ዞን ወደ ቀድሞው አስተዳደር ወደ ጎጃም ክፍለ ሐገር (አማራ ክልል) እንዲመለስ እንጠይቃለን።

  • በሸዋ-ደራ የአማራ ርስት ላይ በሀሰት ትርክት እና አግላይ መንግስታዊ የፖለቲካ ቅዠት ምክንያት የንፁሃን አማሮች ደም እየፈሰሰ ይገኛል። ለዚህም የአማራ ብልፅግና ፓርቲ መቶ ፐርሰንት (100%) ተጠያቂ ነው።

 

  • አማራ ከሚባለው ክልል ውጭ የሚገኘው አማራ ሕገ መንግስታዊ የፖለቲካ ውክልና እንዲኖረው እና በአገሩ ሙሉ መብት ኖሮት እንዲሳተፍ ፣ ሁሉም ዜጋ ከሕግ በታች ሆኖ እኩል በሚተዳደርበት ሕገ መንግሥት እንዲኖር፤ በአማራው ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት አደጋን ለማስቆም በየትኛውም ክልል ያለው አማራ እራሱን መከላከል እንዲችል እንዲደራጅና ታጥቀው እራሳቸውንና አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ መንግስት እንዲወስን እንጠይቃል።

 

  • የአማራ ተወላጆች ላይ በማንነታቸው የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በ21ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረ ትውልድ የማይረሳው የታሪክ ጠባሳ ነው። በኦሮሚያ ክልል መከላከያን ከአካባቢው በማስወጣትና አሸባሪው ኦነግን አስገብቶ

ሰላማዊ ሕዝብን ማስፈጀት፣ በሴራ ዘር ማፅዳት እና በግሪደር ሰው እንደቆሻሻ መድፋት የት ያደርሰን ይሆን? ከፌደራል መንግስት እስከ ክልል መዋቅር የተንሰራፋው ወንጀልና ቸልተኝነት ሕዝብን አስተዳድራለሁ ከሚል መንግሥት አይጠበቅም። ስለዚህ ለጠፋው ሕይወት ሁሉ ተጠያቂው የአብይ አህመድ መንግስት ነው። ይህንንም መንግስት አምኖ ጉዳት የደረሰባቸው እና የተፈናቀሉ አማሮችን በአስቸኳይ መልሶ እንዲያቋቁማቸውና ካሳ እንዲከፍል፤ እንዲሁም አለምአቀፍ አጣሪ ቡድን ወደቦታው ገብቶ እንዲያጣራና ወንጀለኞችን ለሕግ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን።

  • በትህነግ እና በኦነግ አመራር ሆነው በአማሮች ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲፈፅሙ የኖሩ፤ የአማራን ዘር ማጥፋት ፈፃሚና አስፈፃሚዎች በጠ/ሚር አማካሪነት ስም ተሸፍነው በአርባጉጉ ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በበደኖ፣ በወተር ፣ በአሶሳ፣ በወልቃይት ጠገዴ፣ ራያ፤ ወለጋ፤ በሸዋ-ደራ ፣ መተከልና እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክፍል በሚኖሩ አማሮች ላይ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.