የማህበራዊ ገጾች አብዮት – ፈ.ፉ.

**************************
ጉድ እኮ ነው ይህ ዘመን ይህ ወቅት፣
ወሬዎች እንደ ማዕበል የሚናኙበት፣
እንደ ውሃ ሙላት የሚፈሱበት፡፡
ስንዴው ከእንክርዳዱ ተመስቃቅሎ፣
ልብ አማልሎ ስሜት ሰቅሎ፣
የሚነገር የሚተረክ የቀን ውሎ፡፡
ተቆጣጣሪ ተው ባይ የሌለበት፣
የማህበራዊ ገጽ አብዮት፣
ቅጥ የለሽ፣ ልቅ ጽህፈተ-አንደበት፣
ፌዝ ቁም ነገር የተቀላቀለበት፡፡

ዜና «ሰብሮ» አሉባልታ ገንብቶ፤
የራሱን መስኮተ-ዩ ቱብ ከፍቶ፤
ይመግባል ወሬ ፈትፍቶ፡፡

ምስል ፈብርኮ ወይ ለውጦ፣
እንዲስማማ ከሌላ አውድ መርጦ
ይለቃል ውሸትን እውነትን ገልብጦ፡፡
መፈተሽ ነው ተጠንቅቆ በብልሃት፣
እንዳይለወጥ ሚዛናዊ አስተያየት፣
እንዳይዛባ ፍርድና አመለካከት፡፡
——–
ፈ.ፉ. (10 Jan 2021)

ተጨማሪ ያንብቡ:  አድዋ ተናገር !! ( አሥራደው ከፈረንሳይ )

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share