ለመተከሉ ጭፍጨፋ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቀጥተኛ ተጠያቂ ናቸው! – ያሬድ ኃይለማርያም

/
ለመተከሉ እልቂት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የክልል እና የፌደራሉ ባለሥልጣናት ተጠያቂዎች ናቸው። ሽመልስ አብዲሳን ካባ ያለበሰች አገር ገና ብዙ የመተከል፣ ብዙ የሻሸመኔ፣ በዙ የማይካድራ፣ ብዙ የወለጋ አይነት እልቂቶችን ልታስተናግድ ትሽላለች።
ዛሬ በመተከል የሆነው ትላንት በቡራዩ፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በማይካድራ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከተከሰቱት ዘር ተኮር ጭፍጨፋዎች የተለየ አይደለም። ደጋግሜ እንዳልኩት በሁሉም ጥቃቶች ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፤ በተለይም ጥቃቶቹ የተፈጸሙባቸው አካባቢዎች ላይ ያሉ የመንግስት ባለሥልጣናት አንድም ጥቃቶቹን ባለማስቆም እንዲሁም ለዜጎች በቂ ጥበቃ ባለማድረግ ቀጥተኛ ተጠያቂዎች ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሕግ ተጠያቄ ሊሆኑ በሚገባቸውን ሹማምንት ተከበው መቀጠላቸው በአገሪቱ ውስጥ ከሕግ ተጠያቂነት የማምለጥ ባህል እየደነደነ መምጣቱን ብቻ ሳይሆ የሚያሳየው ጠቅላዩ ከሕዝብ ደህንነት ይልቅ ለራሳቸው ሥልጣን ቅድሚያ የሚሰጡ ሰው መሆናቸውንም ጭምር ነው። ለግፉአን እንቆማለን የምትሉ እና ለሰዎችም መብት እንቆረቆራለን የምትሉ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን እና የመብት አቀንቃኖች ኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው እየተፈጸመ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፍራ እና የመንግስትን ከልክ ያለፈ ዳተኝነት በግልጽ ቋንቋ በማውገዝ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የመጠየቅ ሞራላዊ ግዴታ አለባችሁ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  በቂሊንጦ ግንቦት 7 ነው ተብሎ የታሰረው ወጣት 10 ጥፍሮቹን ነቅለው ብልቱ ላይ የላስቲክ ውሃ አንጠልጥለው እንዳሰቃዩት ተጋለጠ

1 Comment

  1. እረ እየተስዋል፤፤
    እንግዲያማ የጁንታው ጉዳይ አስፈጻሚዎችስ ቢሆኑ (አለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጨምሮ) የሚፈልጉት ይህንኑ አንተው የምትለውን አይደል? አቢይ ሄግ ላይ ወይም ብቻ የሆነ ቦታ ፤ ወይም እንደ አልባሽር አሬስት ዋረንት ተቆርጦበት ብቻ አለ አይደል? ……”አቢይ ተጠያቂ ነው” ስትል ከዚህ ዉጭ ሌላ ምን አፈጻጸም አለው ታዲያ? ለተፈጻሚነቱም ተግተህ መስራት አልብህ፤ አውርተህ ብቻ መተው የለብህም፤ አንተ ምን አለብህ? ሁለት ሃገር ይኖርህም ይሆናል፡፤
    ዶ/ር አቢይ ሽመልስ አብዲሳን ወይም ሌላ የክልል ከፍተኛ ባለስልጣን በፈለገው ጊዜ ማንሳት ይችላል ብለህ ስታስብ ነው ትልቁ የትንታኔ ችግርህ የሚጀምረው፡፤ “ይችላል” ብለህ ታስብና ድርጊቱ ሳይፈጸም ሲቀር ትንታኔህ ወደ “አቢይ አውቆ ነው፤ በግድያው እጁ አለበት” ወደሚል ድምዳሜ ይወስድሃል፤፤
    በነገራችን ላይ የሰባኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅት መሪ ተሁኖ እንደዚህ በግልጽ በግለሰብ ደረጃ አቋምን ማንጽባረቅ እንደሚቻል አላውቅም ነበር፤ ለድንቁርናዬ ይቅርታ፡ ስለሆነም ማነች “ቡሽል” ነው የምትባለዋን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰባዊ መብት ሃላፊ ዝቅ ብዬ “ማሪኝ” ብያለሁ፤፡
    ችግር የለም አላልኩም ጓዶች፤ በጣም ችግር አለ! ችግሩ ከጭፍጨፋውም በላይ ነው፡፤ የዘር ጭፍጨፋው is the symptom NOT the cause. Neither it is the intended goal! Think my friend, ይልቅ የፕሮፈሰሩን አደራ እንዳትበላ፤፤ ለነገሩ የማትችለውን አደራ ነው ያሸከሙህ፡፤

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share