ከወያኔ በከፋ የኦሮሞ ኦነግ/አፒዲ አደገኞች ናቸው ብዬ ነበር – ሰርፀ ደስታ

ዛሬ ያለፍቃዴ ነው ይሄን የጻፍኩት፡፡ ብዙ ነገር ያሳዝነኛል፡፡ ዝም ብዬ ነገሮችን እንድታስቡ ለመጠቆም ያህል ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰቴር ተብዬው ግን ከአራጆች ጋር በትላንትናው እለት ቁጭ ብለው ሲያወሩ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ አራጆችም ሲደነፉ ነበር፡፡

እስከዛሬ በወያኔ እየተሳበበ ብዙ አረመኔያዊ ግፎች ተዘለዋል፡፡ ሌላው ይቅርና በወለጋ በወያኔ ላይ ጦርነቱ ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት በፊት በመቶዎች ለስብሰባ ተብለው ተጨፍጭፈዋል፣ ተማሪዎች ከደነቢ ዶሎ ዩኒቨርሲት ተወስደው እሰካሁንም የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡ አይታወቅም የምንለው መታረዳቸውን የነገረን ስላሌለ እንጂ አረመኔው በሽመልስ አብዲሳ የሚመራው ኦፒዲ/ኦነግ እዳረዳቸው ግልጽ ነው፡፡ ከቡራዩ ጀምሮ የሆኖትን እንኳን ብናታውስ፡፡ በግልጽ በአደባባይ በይፋ የክልል መሪ ነኝ ብሎ በሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ የጥላቻና ዘረኝነት ድንፋታ እየደነፋ ያየንው ሽመልስ አብዲሳ ከብዙ በዙሪያው ካሉ ጋር ትልቅ እድል አግኝቶ ብዙ ሲሰራ ነበር፡፡ አዝናለሁ፡፡

የኦሮሞ የአሸባሪ ሰንሰለት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትልቅ ሥራ እንደሚሰራ ብዙ ጊዜ ብንናገረም ከወያኔ አሸባሪ ጋር እየተምታታ  ሰዎች ሊገለጥላቸው የቻለ አይመሰልኝም፡፡ ከወያኔ የከፋ አረመኔ ለ50 ዓመት በጥላቻ፣ ዘረኝነትና የበታችነት ስሜት የተመረዘ አደገኛ የአሸባሪ ቡድን ዛሬ ወያኔን ተክቶ ስልጣን ከመያዙም በላይ ይሄው ወያኔ ሞታም አንዳች ሳያጎድል የአረመኔነቱን ሥራ ቀጥሎበታል፡፡

የመተከል አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ቀጥሏል፡፡ አብይ አህመድ ትላንት በአረጆች ታጅቦ አራጆች እየደነፉ አይተናል፡፡ ዛሬ የሄነውንም አይተናል፡፡ የመከላከያው ታማጆር ሹም የተባለውም በቦታው ነበር፡፡ አዝናለሁ መከላከያው ያማን ነው የሚለውን ከዚህ በፊት አንስቼ ነበር፡፡ የመከላከያው ሥራ የታማጆር ሹሙን ጨምሮ አብይን መጠበቅ እንጂ ከአገርና ሕዝብ ጋር በተያያዘ አንዲት የሠራትን አስታውሱኝ፡፡ ሰሞንን በወያኔ ላይ የወሰደው ካላችሁ ራሱ መከላከያውና የአብይ ሥልጣንም አደጋ ላይ ስለወደቀ እንደሆነ ልብ ይበሉ፡፡ እግረ መንገዱ የወያኔ አረመኔ ቡድን መጥፊያ መሆኑ ለኢትዮጵያውያን ስኬት ቢሆንም መከላከያው የሰራው ለኢትዮጵያ በሚል የሚያሰኝ እርግጠኛ እውነቶችነ ማንበብ አልቻልንም፡፡ ይልቁንም መከላከያው ቅድሚያ ሥራው ከሆኑትና ሕዝባዊነትም አገራዊም የሚያሰኘው ብዙ ዛሬ ላይ ሊሰራቸው የሚችሉ ሥራዎች ነበሩት፡፡ የዜጎች ደግንነትን መጠበቅ ዳርድንበርን መጠበቅ፡፡ ሁለቱንም ሲያደርግ እያየንው አደለም፡፡ ድንበር በሱዳን ወታደሮች ተደፍሮ እዛም እየተዋጋ ያለው ተራው ገበሬ ነው፡፡ መከላከያው ይሄን ሊጠብቅ አልቻለም፡፡ ዜጎች በየቦታው ሲታረዱ  ሕዝብን እየታደገ እንዳልሆነ በመተከሉ ተደጋጋሚ አረመኔያዊ ጥቃት ማይት ብቻ በቂ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:   ጃዌው ጠ/ሚንስተር (አስቻለው ከበደ አበበ)

የሚገርመው የዜጎች በአረመኔዎች መታረድ ደግሞ በዋናነት እየተቀናጀ ያለው ሥልጣን ላይ ባሉት መሆኑ በግልጽ እየታወቀ በኦሮሞነታቸውና በአረማራ ጠልነታቸው ብቻ ከለላ እየተደረገላቸው እንዳሉ እናያለን፡፡ እደግመዋለሁ ሽመለስ አብዲሳ የተባለ ግለሰብ በይፋ በተደጋጋሚ ሲነግረን የነበረው የኦሮሞ ኦፒዲ/ኦነግ አረመኔ ቡድን በወያኔ እግር እንደተተካ ማስተዋል ብንችል መልክም በሆነ፡፡ እንግዲህ ዛሬ ግልፅ ነው፡፡ የኦሮሞ ባለሥልጣናት ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ሁኔታ (በጣም ጥቂት ሊኖሩ ከቻሉ) ዋና መስፈርታቸው በቅድሚያ አማራ ጠል መሆን የኦነግንና ወያኔን አረመኔያዊ ክህሎትን የተጠመቁ መሆን ነው፡፡ ለነገሩ ነፍጠኛ እያለ ካልደነፋ የሚሰማውም የለም፡፡

የጉሙዝና ሲዳማ አረመኔ ወሮበሎችን በመጠቀም ወያኔ ኦሮሞን አንደተጠቀመችበት ዛሬ የኦሮሞው ኦፒዲ/ኦነግ በአገር ላይ ትልቅ አደጋ ሆኖ እያየዋለን፡፡ በዚህ ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሆነውን ሁሉ እናስታውሳለን፡፡ በዘረፋው በኩል አዲስ አበባን ማሰብ ብቻ በቂ ነው፡፡ ወሮበላ እየነገሰ አገር ሠላም አትሆንም፡፡ በእኔ እምነት የሚከተሉት የኦሮሞ መርዘኞች ዋና ናቸው፡፡

እነሽመልስ አብዲሳ በግልጽ እያወጁ ሲያርዱ ኢያየህ፣ እነ ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳዩን እየዘወሩ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሥራ አስኪያጆች እየተመራ፣ አብይ አህመድ ከፊት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ  አሉ በተባሉ ቦታዎች ሁሉ የኦሮሞን ወሮበሎች እየመደበ፡፡ ሌሎችም አይናችን የሚያቸው እውነቶችን ሳንቀበል ስለ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ሕዝብ ሠላም ማሰብ ዘበት ነው፡፡  ሆኖም ይሄ ጎዳይ ከቀን ወደ ቀን እየተገለጠ መሄዱና ሁሉም የወያኔ እጣፈንታ እንደሚደርሰው ተስፋ አለኝ፡፡ ምን አልባትም እንዲህ ከመጠን በላይ እያንቀዠቀዣቸው ያለው ይሄው ሊሆን ግድ ስለሆን ይመስላል፡፡ ተመከሩ ተማሩ ብንልም እየሰሙ አደለም፡፡  የመንግስት መዋቅሮች ከኦፒዲ/ኦነጋውያን ተይዘው ሠላም የለም፡፡ አዝናለሁ!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጲያ፣ ሃይማኖት እና ብሄር ካለፈው እና ከአሁኑ ታሪካችን ተምረን ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንታገል

የአማራው መሪ ነኝ የምትለው አገኘሁ የተባለ ሰው በአንድ ንግግሩ ደጋግሞ የተዋጋንው ለርስት አደለም እያለ ሲያወራ ሰምቼዋለሁ፡፡ ለፍትህ ነው ይልሀል፡፡ ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም፡፡ እርግጥ ነው መሬት ለማስመለስ ወደጦርነት አልተገባም፡፡ እርስታቸውን በግፍ የተቀሙ ርስታቸውን መልሰዋል፡፡ ለማንም ወሮበላ እንዲህ ያለ ያአቋም ልፍስፍስነት በመያዝ ነው በየጊዜው እድል እየተሰጣቸው ያለው፡፡ አንዱ ኦሮሞ ጓደኛ (የታመመ) ስለጦርነቱ ድል ሳይሆን ከምንም በላይ ያሳሰበኝ የአማራ የሁመራንና ራያን መሬት መመለስ ነው አለኝ፡፡ ጓደኛዬ ነው፡፡ እኔ አመክንዮዋዊ እንደሆንኩ አሳምሮ ያውቀኛለና እቅጩን ነገርኩት፡፡ እኔ እነዛን ቦታዎች በአካል አውቃቸዋለሁ፡፡ መሬቶቹ እንዴት እነደሄዱና ቀጥሎም የመሬቶቹ ባለቤት የነበሩትን ከቦታው የማጽዳት አረመኔያዊ ድርጊት ይደረግ እንደነበርም አውቀለሁና፡፡ በነገራችን ላይ አብዛኛው መሬት የተያዘው በወያኔ ባለሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ነው፡፡ በራያ አላማጣ ፃድቀንና ቤተሰቡ የያዘው መሬት መጠን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ሁመራም ያው ነው፡፡  የአማራ መሪ ነኝ የሚለው ምን እንደሚያስለፈልፈው ባይገባኝም ደጋግሞ አርስቱን አንፈልገውም አይነት ይላል፡፡ ቀጥሎም እንደውም በሕግ የሚታይ ይሆናል ያለበትንም አድምጫለሁ፡፡ በይትኛው ሕግ ሊለን እንደፈለግ እንጃለት፡፡ በየትኛው ምድራዊ ሕግ ነው አራጅህ ያስተዳድርህ የሚባለው፡፡ሲጀምሩ በሕግ ቦታዎቹ አልሄዱም፡፡ ከዚህ በከፋ ግን ከዚህ በኋላ ከተከዜ ማዶ በመጣ ትግሬ እነዚያ ቦታዎች ሊተዳደሩ አይችሉም፡፡ የማይካድራውን ስለተነገረ እኮ ነው፡፡ ብዙ ማይካድራዎች በእነዛ ቦታዎች ተፈጽመዋል፡፡ ሰሚ ሳይኖር፡፡ የዛሬው የትግራይ ክልል ነኝ የሚለው እነዚህ ቦታዎች ይገቡኛል ለማለት ምን አይነት ሞራላዊ ብቃት ይኖረው ይሆንስ? ስለዚህ የአማራው አገኘሁ ዝም ማለት ያባት ነው፡፡ እያወራህ ያለህው የጌቶችህን ቁጣ ለማቀዝቀዝ ከሆነ አዝናለሁ፡፡ ከምንም በላይ መሬቱን ሲነጠቅ ፍትህ ሁሉ ተነጥቋል፡፡ ይሄ ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ የተፈጸመበት ከገዛ መሬቱ ለማጥፋት ነው፡፡  ማንም አልመለሰለትም በሰማይ ሆኖ ግፍን ሁሉ የሚሰፈር ቅዱሱና ኃያሉ እግዚአብሔር እንጂ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ እውነተኛ ልጇን አጣች

ፌደራሊዝምና ወሮበሎችን በደንብ እዩ፡፡ ኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ያስፈልጋት አያስፈልጋት የወሮበሎች ወሳኔ ሳይሆን ስለኢትዮጵያ ማሰብ የሚችሉ ዜጎቿ  ሊወስኑ በተገባ፡፡ ፌደራሊዝም ነው የተባለው ዛሬ እነ ሽመልስ አብዲሳና ተባባሪዎቻቸው እንደፈለጋቸው ሕዝብ የሚያሳርዱበት በግልጽ ክልሎችን በዘር ድርሻ የከፋፈለ  ሕገ ንግስት ብለው አውጥተው ነው፡፡ እንጂማ በቤኒሻንጉል ክልል በተባለው የጉሙዝ ብዛት ስንት ነው? ሲቀጥል መተከል ለምን ቤኒሻንጉል  ውስጥ ተካተተ፡፡ ሕዝቡ አማራና አገው ሆኖ፡፡  ሌሎች የክልሉ ዞኖችም ከጉምዝ ይልቅ ጉሙዝ ያልሆነው ይበዛል፡፡ እና በምን መስፈርት ነው ጉሙዝ ጥቂት ሌሎች አናሳዎች ብቻ ክልሉን የሚመሩት፡፡ ዛሬ እርግጥ ነው የኦሮሞ አራጆች ክልሉን በከፊል እየመሩት ነው፡፡  በዘር የተከፋፈል ክልል ብቻም ሳይሆን በሕግ ዜጎች በሌላ ክልል እንደዜጋ የመኖር መብታቸው በሕግ ታግዶ በምን መስፈርት ነው ሠላም የሚገኘው?

ቅዱስ እግዚአብሔር የንፁሀንን ደም ይበቀል! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

1 Comment

  1. ግሩም ትንታኔ ነው።
    የ አማራ ህዝብ መብቱን ማስከበር የሚገባው በ እራሱ መስዋዕትነት ብቻ ነው፤ ያለአንዳች ጥርጣሬ። መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ለ ማምጣት ታትሮ ሲሠራ አልታየም። ብቃት ይሁን ወይም አለመፈለግ በ ዕርግጠኝነት ለ መደምደም ያስቸግራል። አዝማሚያው ግን ተባባሪነት ይመስላል። ለ ኦሮሞ መስፋፋት ጥርጊያ ለ መክፈት።
    ስለዚህ አማራ ተት፣እናክሮ እራሱን ከ መበላት ማዳን አለበት። ከ አውሬዎች መሃል ሰብአዊ መሆን አይቻልም። ሊገድል የሚመጣን መግደል የመኖር ህልውና ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share