ከሁሉም ክፋትና ጥፋት ጀርባ ሕወሐት አለ!! (አሁንም ልብ ያለው ልብ ይበል!) – አንድነት ይበልጣል

አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ – ጥቅምት 17 / 2013

የሰሞኑ ፈተናዎቻችን ምንና ምን ናቸው?

 • በአማራ ወገናችን ላይ እየደረሰ ያለውና በዓባይ ግድባችን ላይ የሚቃጣው ጥቃት ምንና ምን ናቸው?
 • አንበጣ በወገኖቻችን ላይ እያደረሰው ያለው አደጋና በዓባይ ላይ የተቃጣው ጥቃትስ ምንና ምን ናቸው?
 • የሕዝብ መናፈሻዎች፣ የሐገር ውስጥና የውጭ ቱሪዝም መዳረሻዎች ግንባታና የጣና እምቦጭና የጎርፍ አደጋዎችስ ምንና ምን ናቸው? …

በወያኔና በፈረሶቹ እንዲሁም መንግሥት ውስጥ በሸመቁ ቀልባሾች ሤራ፣ በአማራ ወገኖቻችን ላይ ያነጣጠረውና አላባራ ያለው ጥቃት የሁላችንም ሕመምና ሐፍረት ነው፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቆም አለበት! የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን በአባይ ግድብ (በዕድገትና ህልውናችን) ላይ የደቀኑብን አደጋም እንደዚሁ ትልቅ ፈተናችን ነው፤ ያለ አንዳች ማመንታት መመከት አለበት! አንበጣም ሌላው የጋራ ፈተናችን ነው፤ በፍጥነት በቁጥጥር ሥር ልናውለው ይገባል! ወፍ፣ ጎርፍ ወዘተ ሁሉ የሰሞኑ ፈተናዎቻችን ናቸው፤ ፈጣን መፍትሔ ይሻሉ፡፡

እነዚህ ሁሉ ፈተናዎቻችንም ሆኑ እነርሱን ለመሻገር የምንከፍላቸው መስዋዕትነቶች እርስ በርስ የሚፎካከሩ ሣይሆኑ የማይነጣጠሉ ፈተናና ጥረቶች ናቸው፡፡ “አንዱን ምረጡ፤ ወይ አማራን ብቻ ወይ አባይን ብቻ ወይ እህላችንን ብቻ ወይ ጣናን ብቻ እንታደግ” (Either Or) የሚባልላቸው አይደሉም:: “ሉዓላዊነት ገደል ይግባ! አማራን ብቻ እንታደግ ወይም የአማራ ዘር ይጥፋ! ግድቡን ብቻ እንታደግ ወይም የሕዝብ መናፈሻና የቱሪስት መዳረሻ አንፈልግም፣ የጣናን እምቦጭ ብቻ እናጥፋ ወዘተ” አይባልም፡፡ አንድነታችንን አጠናክረን፣ ግድ የሚለውን መስዋዕትነት እየከፈልን፣ ሁሉንም ፈተናዎቻችንን በአንድ ላይና ጊዜ መሻገር አለብን፤ እንችላለንም!! የአማራ ወገናችንንም፣ የአባይ ግድባችንንም፣ ገበሬዎቻችንንም / አርብቶአደሮቻችንም / ሕዝባችንንም … በአንድ ላይና በአንድነት እንታደግ!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  መስከረም ሁለት – ኢትዮጵያ ትቅደም! - ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ከሁሉም ክፋትና ጥፋት ጀርባ ሕወሐት አለ!!

 • ወያኔ ከመጣ ጀምሮ አማራ ወገኖቻችን ላይ በተገኙበት ሲካሄድባቸው ከቆየው የዘር ማጥፋትና ለይቶ ጥቃት፣ በቅርቡ በሻሸመኔ፣ በቤኒሻንጉልና አሁንም በጉራፈርዳ ከተካሄደው ጭፍጨፋ ጀርባ በእርግጠኛነት ሕወሐት አለ፤
 • አሁንም እየዋጠ እንደሚያለቅሰው አዞ፣ በፌስቡክና በመግለጫ፣ ከቅርብም ከሩቅም ሆነው ለአማራ ወገናችን የውሸት እንባ ከሚያፈሱት ጀርባ ሕወሐት አለ፤ (አወቁም አላወቁ)፤
 • ነገም ሆነ ሰሞኑን ሊደረግ በተጠራው የአብን ¨የተቃውሞ¨ ሰልፍ ጀርባ ወያኔ መኖሩ አይቀርም፤ በተቃውሞ ሰልፉ የወጣቶችን ዓላማና ቁጣ በመንጠቅና መሥመር በማሳት ወደ ሕገወጥ የኃይል እርምጃና ፍጥጫ እንዲያመራ ያደርጋሉ፤ ወያኔና የወያኔ ፈረሶች በዚህ ሠልፍ ላይ ተጨማሪ ደም እንዲፈስና በዚህም ሌላ ዙር የብጥብጥ አጀንዳ ለመፍጠር መሞከራቸው አይቀሬ ነው፡፡
 • መንግሥታዊው የለውጥ ኃይልና የጸጥታ አካሉ፣ የሕዝብን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ተቃውሞ የማሰማት መብት እንደሚያከብር፣ ተቃውሞው በቁጣ የታጀበ ቢሆን እንኳ፣ እና ኃይል ቢኖርበትም በልኩ ለመታገሥና ሕጉ የሚፈቅደውን ተመጣጣኝ ኃይል ብቻ ለመጠቀም ፍላጎትና ዝግጅት ሊኖረው እንደሚችል አልጠራጠርም፤
 • ትልቁ ፈተና ግን በተቃውሞው ላይ ከሚሳፈረው የወያኔ ቀልባሽ ኃይል ጋር ተናቦ የሚሠራና ምላሽ የሚሰጥ መሠሪ አካል በመንግሥት/በጸጥታ ኃይሉ ውስጥም ሊኖር እንደሚችል ከሐጫሉ ህልፈት በኋላ በሻሸመኔ ወዘተ፣ በቅርቡ ደግሞ በቤኒሻንጉልና በጉራፈርዳ ጭፍጨፋ ጊዜ አይተናል፡፡ ስለዚህ በመንግሥትና በጸጥታ አካል ውስጥ ያደፈጡ የወያኔና የተረኞች ፈረሶች በፊናቸው ¨ነገር በደላላ¨ እየፈለጉ ደም ሊያፈሱ ይችላሉ፤ ለሕዝብ ቁጣና ሆን ተብሎም ለሚሰነዘሩ ትንኮሳዎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል አውቆ በመጠቀም ለሌላ ዙር ብጥብጥ በር ሊከፍቱ እንደሚችሉ እገምታለሁ፤

ሁሉንም (ወያኔንም መንግሥትንም) በበላው ዕዳ ልክ እንጠይቀው!

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእንቆቅልሽ ኖሮ በእንቆሽልሽ ያረፈው ድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ

በዚህ ውስብስብ የኃይሎች አሰላለፍ ውስጥ ዜጎች፣ ልዩ ልዩ ተዋናዮችንና ሚናቸውን በቅጡ ለይተን በተደረገብን፣ በተደረገልንና ባልተደረገልን ልክ አቋም ልንወስድ ይገባናል፤ አቋም ብቻ አይደለም፣ ማንንም እንደተሳትፎው አይነትና መጠን በግልጽና በሕብረት እንቃወመው እና/ ወይም እንደግፈው፡፡ ለምሳሌ የሰሞኑን ሁኔታ ብቻ ብናይ እንኳ፣ የአማራ ወገኖቻችንን የሚያስጨፈጭፈውና የሚጨፈጭፉት ወያኔና ፈረሶቹ ናቸው (መንግሥት ውስጥ በተሰገሰጉት ቀልባሾች እየተረዱ)፡፡ ልዩ ልዩ መብቶቻችንን የሚጥሱት እነዚህ ናቸው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ አላባራ ያለውን ጭፍጨፋ መከላከል፣ ማስቆምና የሕግ የበላይነትን ማስከበር ያልቻሉት የክልል መስተዳድሮችና ፌዴራል መንግሥት ናቸው፡፡ ይህን አውድ ለብቻው እንየው፣ ወያኔና ፈረሶቹ መብቶቻችንን የሚጥሱ (Violators) ሲሆኑ መንግስት ደግሞ መብቶቻችንን ማስከበር (Protection) ያልቻለ ክፍል ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱንም በየጥፋታቸው ዓይነትና ልክ ልንቃወምና ልንታገላቸው ይገባል፡፡

አለበለዚያ በየፌስቡኩ፣ በየሜዲያውና አሁን ደግሞ በየሰልፉ የዋና ጨፍጫፊዎቹን፣ የወያኔና የፈረሶቹን ጥፋት አይቶ እንዳላየ የምንሆነው በምን መስፈሪያና ልኬት ነው? ለነዚህ ጨካኝ አረመኔዎችስ የሚያዝነውን ልብ ከየት ነው ያመጣነው? በአንጻሩ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ሙሉ ለሙሉ ማስከበር ገና እንዳልቻለ እየታየ ነው፤ ታዲያ የወያኔን ዕዳ ለወያኔ የመንግሥትን ዕዳ ለመንግሥት ማሸከምስ ያቃተን ለምንድን ነው? የለውጡን ቡድን ባልበላው ዕዳ ሁሉ እያዋከብን ስናዝለው በሚፈጠረው ክፍተት ወያኔና ፈረሶቹ ሊገቡበት እንደሚችሉና የዚህንስ መዘዝ መገመት ከባድ ነገር ነው እንዴ? የለውጡን ቡድን ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲያመቻች እንደገፍ፣ እናስገድደው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለአንዳች ተጽዕኖ የፈለገውን መርጦ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንጀምር … ይኸው ነው!

 

የኔ ጥያቄዎች

ከዚህ ትዝብቴና ግምገማዬ ተነስቼ እንደ አንድ ዜጋ የሚከተሉትን ምክር አዘል ጥያቄዎች እጠይቃለሁ፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ዋርካ ምድር ነካ ንገሩት ለዋንዛ ፍቅር ለባለጌ ይመሥለዋል ዋዛ " መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ሀ) በወያኔ ተንኮልና ሤራ ላይ ከ29/45 ዓመታት በኋላም ያልባነነ ብዙ የሕዝብ ወገን አለ፤ መቼና ከዚህ በላይስ ምን ስንሆን ነው የምንባንነውና ¨በቃ¨ የምንለው?

ለ) መንግሥትስ በዚህ ዘርፈ ብዙና የማያባራ የወያኔ ሐገር አፍራሽ አሻጥር ላይ (ከስጋቱና ሊደርስ ከሚችለው ጉዳት ጋር (ሪስክ)) በሚገባ የታቀደ፣ የተናበበ፣ ቆራጥ፣ ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ የሚወስደውና ወያኔን የምንገላገለው መቼ ነው?

 • በአማራና በመላው ሕዝብ ህልውና፣ በሐገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ እየተፈጸመ ያለው አደጋ ምን ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው በመንግሥት ውስጥ ያለው የለውጥ ኃይል፣ የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን እርምጃ (Last Resort) የሚወስደው?

ሐ) ከመንግሥት ውጭ ያሉና በመንግሥት ውስጥ የተሰገሰጉ ቀልባሾች፣ ሥልጣን ናፋቂዎችና ተረኞች አንድ አእምሮ፣ አንድ ልብ፣ አንድ አፍ፣ አንድ ኪስና አንድ እጅ ሆነው እያተራመሱን ይገኛሉ፤ ታዲያ ከመንግሥት ውጭ ያለው የለውጥ ኃይል በመንግሥት ውስጥ ካለው የለውጥ ሐይል ጋር የጋራ በሆኑ ዓላማዎች ዙሪያ ተባብሮና ሕዝቡን በየፊናው አስተባብሮ ለመሥራትና የቀልባሾችን ጥፋት ለማምከን የሚያሽኮረምመው ነገር ምንድነው?

በዕውነቱ ምናልባት ገና በደንብ ያልገባኝ ነገር ካለ የሚያስረዳኝ ወገን-ዘመድ ቢኖር ብዬ ነው መጠየቄ፡፡ መወያየት መልካም …

በሁሉም ፈጣሪ ይርዳን!!

 

3 Comments

 1. አንድነት፤
  በጣም በጣም መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ 100% በህሳብህ እስማማለሁ፡፡ ጥያቄዎችህንም እጋራለሁ፡፡ ለጥያቄዎችህ መልስ ለመስጠት ግን መንግስትም የሚከብደው ይመስለኛል፤፤ የሆነ ሆኖ ቅድሚያ የሚስጠው ቁልፍ ጉዳይ ወያኔን ከነግሳንግሱ (በመንግስት መዋቅር ውስጥ በየክልሉ ያሉ) መዋቅሩን በጣጥሶ ከጨዋታው ውጭ ማድረግ ነው፡፡ ሌላው እዳው ገብስ ነው፡፡
  የአቢይ መንግስት ይህ እንዲሆን ይፈልጋል ወይ? “እንዴታ” ነው የምለው! ምክንያቱም የፖለቲካ ዋጋው ከፍ እያለበት ነው፡፡ ታዲያ ለምን አያደርገውም? ለመሆኑ ምንስ ነው ማድረግ ያለበት? ብትለኝ ለማለት የምችለው ምንም ያድርግ ምን ብቻ የሚያደርጋችው ነገሮች “surgical precision” ይጠይቃሉ ነው፡፡ በዚያ ላይ በአጭር ጊዜ (swiftly!) መልስ የሚሰጥ እርምጃም አለ ብዬ አላስብም፡፡ “ተንታኝ” የተባለውም ሁሉ “እርምጃ ይወሰድ” ይላል እንጂ “ምን ዓይነት እርምጃ?” ስትለው መልስ የለውም፡፡ Because we have a hostage situation here!
  We shall prevail!

 2. ሻዕቢያ እና ኤርትራውያኖች ስደተኞች አሉበት ከየአማራን ህዝብ በጅምላ ከሚያጠፉ ጀርባ !!!

 3. የወያኔን ማንነት የማያዉቅ የለም።ችግሩ ያለው ወያኔ ያሳደገቻቸው የባሰ ክፋት ይዘው ስለ መጡ ነው። በአግላይነትም በዘረፋውም ወያኔን አስከንድተዋል። ሆደ ሰፊነታቸውም ለህወሃት ለኦነግ እና ለቅርንጫፎቻቸው ነው።ሌላውማ በቢሮዉም መሰብሰብ አይችልም። ምክንያት እየተፈለገ ይታሰራል ፍርድ ቤት ቢፈታውም አይፈታም።የአዲስ አበባ ህዝብም ባይተዋር ተደርጎ በጠራራ ፀሐይ የደከመበትን ቤቱን ይነጠቃል። ግፉ ብዙ ነው።።ይህ ሁሉ ሆኖ እኛ የምንሠራዉን አትዩ ።ህወሃትን እዩ ይሉናል። ተረኞች ባይብሱብን የህወሃት ዕዳዉ ገብስ ነበር ።እነ ሽመልስ ነገሩን አቅደው እየሠሩ እንደሆነ ነግረውናል።ይህ የሽመልስ የግሉ ነው የሚሉትን ይተዉት ።በተግባር ስላየነዉ።ታድያ እየተካሄደ ያለው ለዉጥ ወይስ ጠ/ሚንስትሩ እንዳሉት ለዉጥ እያስመሰለ ዝሆኑ ድብቅ ዓላማዉን ለማሳካት እየሰባበረ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share