በጀርመን የገባውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ያለው ቴከኒካዊና ተቋማዊ ልምድና አስተያየት – ክፍል 9

ለተከበራቹህ ወገኖች                                                                           

የኮሮና ልምድ ከጀርመን – 2ኛ ማዕበል ሎክዳውን  28.10.2020

ሁኔታዎች በቅፅበት በመቀያየራቸው ከአለፈው በመቀጠል ስለ ኮቪድ-19  ወረርሽኙ 2ኛ ማዕበል የተወሰነውን ሎክዳውን የያዘውን ክፍል ዘጠኝን አቀርባለሁ።

በ8ኛው ገለፃ ከሶስት ቀናት ላይ እንዳስቀመጥኩት ፅሁፍን ሳልጨረስ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተቀያየሩ ነበር። በዚህም የተነሳ በዛሬው ዕለት አዲስ ውሳኔ በመወሰዱ ይህንን ልምድ ለማካፈል እሞክራለሁ።

በዛሬው ዕለት ቻንስለር አንጌላ ሜርክል ከፌዴራል መንግስታት ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር በመመካከር  ጀርመን በኮሮና ላይ የተፈራውን ሎክ ዳውን ጥለዋል። በየ15 ቀኑ የእርምጃ ውጤት ይፈተሻል። በህዳር መዘጋት የተነሳ ለሚደርሰው ክስረት ለአንስተኛ ኩባንያዎች 75% የወር ገቢያቸውን፣ ለትላልቅ 70% የወር ገቢያቸውን ለመደጎም ታቅዷል። ለዚህም የሚሆን 10 ቢልዮን ዩሮ ተይዟል።

የሮበርት ኮህ ኢንስቲትዩት እንደዘገበው በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ  15ሺ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተያዙ ሲሆን እና ይህም በተመሳሳይ የናሙና ምርመራ መጠን ከአንድ ሳምንት በፊት ከነበረው ከእጥፍ በላይ ሲሆን፣ በጽኑ ህሙማን ማገገሚያ ውስጥ ያሉት ቁጥርም በ10 ቀናት ውስጥ እጥፍ ሆኗል.። ከዚህ በመነሳት ይህ እርምጃ በአስቀድሞ መከላከያ እቅድ መሰረት ተወስኗል። የእርምጃዎቹ ዓላማ በታህሳስ ለገና በዓል ሰው ዘና በሎ ለመገናኘት እና እንደተለመደው ለማክበር በማሰብ ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው ህዳርን በከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ እና እቀባ በማድረግ በመገደብ ታህሣሥን ለማዳን ነው። አንድ ሚሊዮን ሰዎችን የያዛውን የኢቨንት ኢኮኖሚውን የሚጎዳም ነው። ከ10 ሰራተኞች 9ኙን እስካሁን ጎድቷል።  ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እርምጃዎችን በመቃወም በግል፣ በጋራ ወይም በድርጅት ስም ለጀርመን ፍርድ ቤቶች ክስ በማቅረብ ከዚህ በፊት እንደሚደርገው ለማስቆም እንቅስቃሴም ተጀምሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ማረጋገጥ የምትችልባቸው 10 መንገዶች

  1. የጅምላ ሻጮች እና ቸርቻሪዎች ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ

የኮሮና ኢንፌክሽኖች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ ቢኖርም በጅምላ እና በችርቻሮ በህዳር ክፍት ሆኖ ይቆያል። ሆኖም በሱቆች ውስጥ በአስር ካሬ ሜትር ከአንድ በላይ ደንበኛ  መቆየት አይፈቀድላቸውም ።

  1. ትምህርት ቤቶች እና መዋለ ህፃናት ክፍት ሆነው ይቆያሉ

የኮሮና ቁጥሮች በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምሩም ትምህርት ቤቶች እና መዋለ ህፃናት በህዳር ውስጥ ክፍት እንደሆኑ ይቆያሉ።

  1. የምግብ አቅርቦቶችን

ምግብ ቤቶች ከጥቅምት 23 (2 November 2020) ጀምሮ ለተቀረው አንድ ወር ዝግ ናችው። ይህ ወደ  ቤት በትዕዛዝ ተወስደው የሚሄዱ ምግቦችን የሚያቀርቡትን አያካትትም።

  1. የህዝብ ግንኙነቶች/ርቀትን በከፍተኛ ሁኔታ መገደብ

በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች በጋራ መቆየት የሚፈቀድላቸው ሁለት የቤተሰብ አባላት ቢበዛ አሥር ሰዎች ባሉበት ብቻ ነው። ይህ አስገዳጅ ነው፣  የእነዚህ የግንኙነት ገደቦች ጥሰቶች ላይ ከፍተኛ ቅጣት ይጣላል።

  1. ስፖርት

ፕሮፊሽናል ስፖርት በተለይም የቡንደስ ሊጋ ያለ ተመልካቾች ብቻ በህዳር ውስጥ ይደርጋል።

የጤና ተኮር ስፖርት እና በአማተር ስፖርት ዝግ ነው። የተናጠል ስፖርት ለምሳሌ ሩጫን እገዳው አይመለከተውም።

  1. የመዝናኛ ተቋማት

መዝናኛን የሚያገለግሉ ተቋማት በኖቬምበር ውስጥ በአጠቃላይ በመላው ጀርመን ዝግ ናቸው፡፡ ሲኒማ ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች ፣ ኦፔራዎች እና የኮንሰርት አዳራሾች፣ ቱሪስቶች በሆቴሎች መቆየት እስከ ህዳር 21 (30 November) መጨረሻ ድረስ ዝግ ናቸው።

  1. የመዋቢያ ስቱዲዮዎችን እና የመታሻ ቤቶች

እንደ የመዋቢያ ስቱዲዮዎች ፣ የመታሻ ቤቶች ወይም የንቅሳት ስቱዲዮዎች ዝግ ናቸው። የፀጉር ማስተካከያ ሳሎኖች ግን የንፅህና አጠባበቅ መስፈርቶችን በማሟላት ክፍት ናቸው፡፡ እንደ ፊዚዮቴራፒ ያሉ ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች ክፍት ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ልትወልድ ሆስፒታል የገባችዋን እናት በህክምና ስህተት ገድለዋል የተባሉት ዶክተር ተከሰሱ

ከመልካም የጤንነት ሰላምታ ጋር
ፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share