የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ( አብን ) የጠራው ሰልፍ በመንግስት መከልከሉ የብልፅግናን ከልክ ያለፈ አንምባገነናዊነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ( አብን ) የጠራው ሰልፍ በመንግስት መከልከሉ የብልፅግናን ከልክ ያለፈ አንምባገነናዊነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ገለፀ።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ማንኛውም ዜጋ ሀሣቡን በነፃነት የመግለፅ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብቱ ሊከበርለት ይገባል ብሎ ያምናል።
“ማንኛውም ሰው ያለ ማንም ጣልቃገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው። ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በስነጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውም ዓይነት መረጃ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጫ ነፃነቶችን ያካትታል።”
ሲል የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 2ን ጠቅሷል።
መኢአድ በተጨማሪም አንቀፅ 30 ንዑስ አንቀፅ 1″ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው” የሚል ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ እንዳለም አመልክቷል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ፣ በደቡብ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል እየተፈፀመ ያለውን ዘር የማጥፋት ተግባር የሚያወግዝ ሠልፍ በአማራ ክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ከተማ ዜጎች ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ያወሳው መኢአድ አንምባገነኑ የብልፅግና መንግስት ይህን ሠልፍ እንዳይካሔድ ከልክሏል ነው ያለው።
በሕገ መንግሥቱ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው ይህ መብት ፈቃጅና ከልካይ የሌለው መብት ሆኖ ሳለ መንግሥት እራሱን ፈቃጅ እና ከልካይ አድርጎ ይህን በሕገ መንግሥቱ የተደነገገ መብት መጣሱ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በአማራው ላይ እየደረሰ ላለው ዘር የማጥፋት ተግባር ተባባሪ እንደሆነ ይቆጠራል ሲልም መኢአድ በመግለጫው አስታውቋል።
ሰሞኑን ገዢው ፓርቲን በመደገፍ በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች በተከታታይ እየተደረጉ ባሉበት ሁኔታ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለሚመለከተው የመንግሥት አካል በግልፅ በደብዳቤ ያሳወቀውን ሰላማዊ ሰልፍ መንግሥት በሚዲያ ወጥቶ መከልከሉ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው ብሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የትግራይ ህዝብ የወያኔ ስርአት ተጠቃሚነው! (አንዷለም አስራት )

3 Comments

  1. እንበጣን ማን ሊያባርላችሁ ፈለጋችሁ ኖርዋል የአብን ደጋፌዎች ስትሰለፉ?

  2. ዘሃበሻ የሻምበል ለማ ጉያን ዜና እረፍት ቢያንስ እንደ ዜና ያልዘገበው ለምንድነው? ነው ሳላነብ አመለጠኝ፤ ውይስ እሳቸውም ኢትዮጵያዊነታችው ጥያቄ ዉስጥ ወድቋል ማለት ነው? ወይስ ሥራቸው አይመጥንም ነው? ወይስ ትውልዱ አያውቃቸውም ነው? “በዚያኛው” በኩል ያሉትም ጣል ጣል አድርገዋቸዋል፡፡
    ኢትዮጵያዊነት ከብሄር ማንነታችው ጋር ሳይጋጭባችው ኖረውት የሚያልፉ ሰዎች መጨረሻቸው እንዲህ መሆኑ ነው፤ ትክክለኛ አቋም ግን ከሁለት የሚያሳጣ አጣብቂኝ፤
    በመህል ለማለፍ የኢትዮጲያን የተወሳሰበ ታሪካዊ ሥሪት ጠንቅቆ ማወቅ፤ ትግስትና ጥበብ ይፈልጋል፡፡ አሁን አብይ እየሞከረው ያለው ማለት ነው፤
    ሌላኛው መንገድ ክሁለቱ ጫፍ (በኢትዮጵያ እና በብሄር ጽንፈኝነት መካከል) ሆኖ ጎራ ለይቶ ዲንጋይ ሲወራወሩ መኖር ነው፡ የሚገርመው እነዚህ ሁለት ጫፎች ዲንጋያችወን የሚወረውሩት አንዱ ወደ ሌላኛው ጫፍ ሳይሆን ሁለቱም ወደ መሃል ነው፤

    የሻምበልን ነፍስ ይማርልን!

  3. ታዲያ ሲከለከሉ ለምን ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኦቦ ሽመልስ አብዲስ እና ለኮ/ል አብይ አህመድ ጥያቂያቸውን አያስገቡም፡፡ ምንአልባት ችግሩ ደብዳቢያቸውን ለጥበቃ ክፍል ሃላፊው ለኮንስታብል ተመስገን ጥሩነህ ማቅረባችው ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም ያበሳጫል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share