“ላጉርስህ ሥትለው ልንከሥህ ካለህ ምን ትለዋለህ ??… “  መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

የኢትዮጵያ   መበልፀግ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ እጅግ አሥፈላጊ ነው።አገርም በራሷ ዜጎች ጥረት ና ግረት ነው የምትበለፅገው።እንዲሁ በቅሥፈት ከጠርሙሱ የወጣ ጂኒ አያበለፅጋትም።እንደ አላዲን ተረት…

አገር ታታሪ ና ጠንካራ የሥራ ዲሲፕሊን ባላቸው ዜጎቾ ነው የምትበለፅገው።አገር  ድካምን በማያውቁ  ዜጎቿ፣የለማቋረጥ በሚፈሥ ላብ፣በእውቀት ላይ በተመሠረተ ብርቱ ጥረት ልትበለፅግ ትችላለች።

አገር፣    ዜጎቿ ለነገው ትውልዳቸው ምቾት ሲሉ መዕሥዋት በመክፈል በእድገት ጎዳና  ሥትበለፅግ የሁሉም ዜጋ ህይወቱ ይቀየራል።ለምሳሌ፣በዓባይ ወንዛችን ላይ እየተገነባ ያለው የኃይል ማመንጫ ግድብ ሥኬት የመሰዋታችን ሥኬት ነው። ዜጎች ከድህነት ለመውጣት ያላቸውን ጉጉት በተግባር ያሳዩበት ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ አባይን ግንድ ይዞ ከመዞር የገታውና ማደሪያ የሰጠው ፣ሀገር ወዳድነት የታየበት እንቅሥቃሴ ነው።የለው ብቻ ሳይሆን የሌለው ና   የሌላት  እንኳ ያቺኑ ያላቸውን የዕለት ጉርስ ለህዳሴው ግድብ ሰጥተዋል።    “ለምን እየተቸገሩ ለአባይ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያላቸውን ሰጡ? “ብለን ብንጠይቅ ብዙሃኑንን ምንዱባን ከድህነት የሚያላቅቀው ይህ የሚታይ፣የሚዳሰስ ና በተጨባጭ የሚያዩት ፕሮጀክት መሆኑን ከልብ በማመናቸው እንደሆነ ተገንዝበው ነው።ዛሬ አባይ “አባይ!”እንዳልሆነም አሥመሥክሯል።አባ ይ “አባ’ይ ” ነው። ነገ ለትውልዱ እንጀራ አውጪ በመሆኑ ኘው ፣ከሊቅ እሥከ ደቂቅ በአንድ ድምፅ “ግድቡ የኔ ነው። “ በማለት ዓለምን ያሥገረመው።

ዛሬም ወደፊትም፣  እንደ አባይ፣ “አባ’ይ ” ከተገኘ ማለትም ሠርቶ የሚያሰራ፣የሚያበላ ፣ከተገኘ፣ሀገር ፣ በአጭር ጊዜ ውሥጥ ትበለፅጋለች።የአጠቃላይ ህዝቡም ኑሮ ይለወጣል።

ገበሬው፣ሠርቶ አደሩ፣ወቶአደሩ፣ነጋዴው፣ወዘተ አልጋውን፣ልብሱን ፣ቤቱን ና ምግቡን ይቀይራል።በጎና ጠቃሚ ባህሉ ይዳብራል።ጎጂ ና አጥፊ ባህሉ ይጠፋል።ከአካባቢው፣ከጎሳው፣ከቋንቋ ተናጋሪው ባሻገር አርቆ መመልከት ና ማሰብ ይጀምራል።በማሰቡም በተፈጥሮ አንድ የሆነ፣የሚወለድ የሚያድግ፣የሚጎለመሥ፣የሚያረጅና የሚሞት መሆኑንን ይገነዘባል። በከንቱ መኮፎሱ ይቀርና የዓለም አካል ተፈጥሯዊ ልዩነት የሌለው ሰው መሆኑን በቅጡ ያውቃል።ከአድማስ ባሻገር እንዳያልም፣እንዳይተጋ እና ለትውልዱ የነገ ምቾት በብርቱ እንዳይጥር ካደረገው እና አዚም ሆኖ ካደነዘዘው  የአእምሮ ደህነትም ይላቀቃል።

በመላው ኢትዮጵያ ድህነትና ያለማወቅ  እጅና እግሩን የሸበበውና  ቀፍድዶ የያዘው ሰው እልፍ እለአፍ ነው። የዘመናት “ ችግር ና ችጋር “  ዛሬም ከአገሬ ህዝብ ጫንቃ ላይ አልወረዱም።ይህ እውነት እያለ ነው፤ወያኔ/ኢህአዴግ የሚላሥ የሚቀመሥ ሥለማግኘቱ እርግጠኛ ያልሆነውን ብዙ አበሳን የተሸከመ ህዝብ፣  ጥጋበኞቹ በጥይት እሳት ሊያሥፈጁት ፣ጠግበው ውሥኪና ቮድካ እየጠጡ ይሚማማሉት።

በቮድካ ደንዝዘው፣   ሚሊሻ ና ልዩ ኃይል ለእነሱ ጥጋብ ሲሉ ከንቱ  የሆነ የውሻ ሞት እንዲሞት ምሽግ አድርገውት፣ “ግፋ በለው!!…” ይሉታል።በእውነቱ ለመናገር በድህነት ተቀፍድዶ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት አረንቋ ውሥጥ ያለን ህዝብ የጥይት እራት ለማድረግ መንቀልቀል በእጅጉ የሚያሳፍርና ህሊና አልባነትን ነው።

ዛሬም የተገንጣይነት ሥም የያዙ፣ለህዝብ ያልቆሙ።27 ዓመት ኢትዮጵያን በተጭበረበረ ምርጫ ሲያሥተዳድሩ የነበሩ፣የትግራይን ደሃ ወዛደር እና ገበሬ ከምፅዋት ተቀባይነት ፣ከሥንዴ “ራሺን” ያላላቀቁ።ትላንት በበረሃ ሳሉ የሚቀመጡባትን የየዋሁን ገበሬ የዲንጋይ መቀመጫ ዛሬ በባለ አምሥት ኮኮብ ሆቴል በውድ ሶፋ የቀየሩ ናቸው። ከምቾት ወዳድነታቸውም የተነሳ ራሳቸውን ፈጣሪ ያደረጉ፣ሞትን የረሱ ፣ህሊና ቢስ “ማቶዎች” መሆናቸው ድርጊታቸው ያሳብቃል።

እነዚህ ህሊና ቢሶች እያሉ ፣  እንዴት ነው በልፅግናን በአገራችን እውን የምናደርገው? በነገድ እና በቋንቋ ተጠራርቶ ፣በነፃ አውጪ ሥም ተደራጅቶ ፣ በመዝረፍ ነውን?ወይስ በአንዲት ሉአላዊ አገር የሚኖር “ሰው የሆነ ዜጋ ሁሉ ” እኩል መብትና ነፃነት ኖሮት በመላው ኢትዮጵያ ተዞዙሮ የመሥራት፣ሀብት የማፍራት፣ከወደደው ጋር ተጋብቶ ፣ተዛምዶ ና ተዋልዶ የመኖር መብቱ ተረጋግጦለት ያለ ሌብነት በወዙ እንዲከብር   ተገቢውን መንግሥታዊ ድጋፍ በማድረግ ነው?…

ሌብነት አልባ፣ በወዝ ፣በድካም፣በልፋት፣በጥረት እና በግረት የመበልፀግ  ጎዳናው ሁለተኛው አማራጭ ነው።ይህ በህሊናቸው ጥንካሬ የሚመኩ ዜጎች የብልፅግና መንገድ ነው።ይህ መንገድ ብቻ ነው ፣ ወደ ብልፅግና የሚወሥደን።ይህ መንገድ ወደ ብልፅግና እንደሚወሥደን እናውቃለን። አሻጋሪው የእውነተኛ ለውጥ መንግሥትም ተቋማትን በመገንባት ላይ መሆኑን በተጨባጭ እያየን ነው። “ቦሌ በአንድ ቀን አልተገነባም “በእርግጥ “ የፖለቲካ ጫዎታው” “ የማንችስተር “እና “የአርሴናል ” ጨዋታ እየመሰላቸው፣በሥራ፣በገብያ፣በመሸታ ቤት ፣በየካፊው …ሁሉ ተሰባስበው ፣በሥሜት በመናገር የራሳቸውን ማንነት በመዘንጋት የሚዘላብዱ አሉ።መዘላበድ መብታቸው ነው።ሆኖም ቆም ብለው በማሰብ ራሳቸውን ከተነጂነት ቢያላቅቁ ና እንደ ሰው ቢያስቡ እውነታውን ይረዳሉ።”ሀገር የምትመራው ፣በእውነት ላይ ተመሥርቶ፣ከግል ጥቅም እርቆ፣በመከባበር፣ በመደማመጥ እና ለመጪው ትውልድ ብልፅግና አርቆ በማሰብ እንጂ በቋንቋ፣በጎሳ እና በዘራፊ ቡድን ተደራጅቶ በህዝብ ሥም፣ህዝብን በእሳት እንዲማገድ እንደችቦ አቁሞ የምቾትና የድሎት ኑሮ መኖሪያ ምሽግ በማበጀት ባለፉት ሁለት ከመንፈቅ ዓመታት በአሻጋሪው   መንግሥት የተሰራውን ሀገርን ወደ ብልፅግና የሚያራምድ ሥራ በመናቅ አይደለም።

እርግጥ ነው፣አሻጋሪው መንግሥት የሰውን አእምሮ መቆጣጠር የሚችል ሁሉን አዋቂ ሁሉን ቻይ እግዜር እንዳያደለ እናውቃለን።   ደሞም    የዚች ሀገር ችግር ውሥብሥብ እና በሴራ ፖለቲካ የተተበተበ ነው። በመሆኑም የፖለቲካ ጌሙን ያላወቀ፣በትንሹም በትልቁም በማልቀሥ ና አንደ ሰው ላይ ጣት በመቀሰር የሚነዛው የቅጥፈት ወሬ በቀላሉ ሀገርና ህዝብን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። ይህንን በመገንዘብ በለውጡ መንግሥት ላይ፣ አፍ እንዳመጣ ከራሥ ፍላጎትና ጥቅል ከሆነ የመንጋ ሃሳብ ከመወገን፣ ብንታቀብ ሐውጡን እንዲፋጠን እናደርጋለንና ሰከን ብለን ራሳችንን በማየትና የተከመረብንን ኃጥያት በመገንዘብ ለንግግራችን፣ለፅሑፋችን፣ለከት ቢኖረው መልካም ነው።… “ ከበሮ ችሎታ ባለው ሰው እጅ ሲመታ ያምራል እችላለሁ ብለው ስዩዙት ግን ያደናግራል። ‘

ባለፉት ሁለት መንፈቅ ዓመታት ውሥጥ  የፍትህ ጠበቃ የሆኑት የህግ አሥፈፃሚ ተቋማት ገና ተገንብተው ባለማለቃቸው ፈተናው መብዛቱንም እንገነዘባለን።ይሁን እንጂ ውሥጥ ለውሥጥ ተቋማትን ከሌብነት የፀዱ፤ለእውነት የቆሙ፤በህግ የበላይነት የሚያምኑ ፣ ለሰው ፊት የማያደሉ እና ብቃት ያላቸው ፣ከበሮውን በወጉ የሚመቱ ለማድረግ በብርቱ እየተሠራ መሆኑን እንገነዘባለን።

ይህ የመንግሥት አካሄድ  በእጅጉ የሚደገፍ  እና “ይበል!” የሚያሰኝ ነው።እንዲህ ዓይነቱ በጥንቃቄ የሚከናወን ብቃት ያለውን ዜጋ  የህዝብ አገልጋይ ለማድረግ መንግሥት ፈራ ተባ እያለ ፣እንደ ዶ/ር በየነ ጴጥሮሥ ዓይነቱን የሠከነ ምሁር ፣በከፍተኛ ሥልጣን የህዝብ አገልጋይ ማድረጉ “ይበል !ይበል! አሰኝቷል።

ይህ ለሀገር ና ለህዝብ የሚበጅ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው።ሙያነክ የሚኒሥቴር መሥራ ቤቶች ሁሉ ከመሠል አቻዎቻቸው የላቁ ሆነው መገኘት ይኖርባቸዋል።ትላንት በጦር ሜዳ ደርግን የፖለቲካ ኮሚሳሪያቱና ካድሬዎቹ ናቸው፣የደርግን ሞት ያፋጠኑት።እናም ብልፅግና በአሮጌ አቁማዳ ውሥጥ አዲስ የወይን ጠጅ ለመጨመር የሚዳዳ ከሆነ  አዲዮስ!”(በዚህ ጉዳይ ላይ ቅን ሃሳቤን በቀጣይ ፅሑፌ አቀርባለሁ።)

አገር በየጊዜው በጉልበተኛ ፖለቲከኞች እንዳይናወጥ መንግስት  ጠንካራ መሠረት ያላቸው ተቋማትና ሹማምንት ያሥፈልጉታል። እነዚህ ተቋማት እንዲኖሩት ደግሞ ፣ ወደፊት በሚካሄደው የመንግሥት ምሥረታ ሀገር አቀፍ ምርጫ፣ በቅሥቀሣ ወቅት ፖለቲከኞችን በመሞገት ለአገር ብልፅግና የሚበጅ ሃሳብ   ምሁራኑ በማቅረብ ፤ ሞጋችነታቸው ጎልቶ መታየት ይኖርበታል።

ሟጋችነታቸው ዛሬ ና አሁን፣ በህወሓት /ኢህአዴግ የነፃ አውጪነት ግግምና ላይ  አለበት መሆን ይኖርበታል።በእውነቱ  ህወሃት /ኢህአዴግ ያአደራ እቃ ይመሥል የዛሬ 44 ዓመት ተቸክሎ ካለበት አልነቃነቅም ያለ “ገገማ”  ፖርቲ ነው።ይህ ከአለም እድገት ጋር መጎዝ የማይፈልግ፣ከህዝቡ ንቃት ጋር ሲወዳደር በእጅጉ ኋላ የቀረ ፓርቲ የሚኖረው በትላንትን ጀብዱ ነው።ትላንት ግን ዛሬ አይደለም።ትላንት በጦርነት ማሸነፍ ይቻላል። ዛሬ ግን በጦርነት ማሸነፍ የሚችልበት ሁኔታ፣ሥፍሬ ና የተመቻቸ ጊዜ እንዲሁም አቅም የለም።ልንገጠል ቢልም ህዝቡን ከሰማይ መና እያዘነበ አያበላውም።በእርዳታ ስንዴ በሚኖር ምንዱባን ህዝብ ላይ በቀቢፀ ተሥፋ ማላገጥ ካልሆነ በቀር ።እገነጠላለሁ።ብሎ ፉከራ።ይልቅሥ ወደቀልቡ ተመልሶ እንደህዝቡ እውነተኛ ፍላጎት ቢያድር ይሻለዋል።…    ለ27 ዓመት በትግራይ ህዝብ ሥም ሲነግድ የኖረው ፣ዛሬም   ነፃ አውጪ ነኝ በዩ ህውሃት እና ነፃ አውጪው ኦነግ ሸኔ፣ አንድ አይነት ናቸው።በዛሬዋ ዓለም ጦርነቱ “ግዛቴ ተገፍቷል።የእኔ ነበር።ለእኔ ይገባል።በማለት በተሥፋፊነት እንጂ በተገንጣይነት አይደለም። “ ይሁን እንጂ ህወሓት ም ሆነች ኦነግ ሸኔ አሻጋሪውን መንግሥት በሙሉ አቅሙ ሠርቶ ከዚህ የተሻለ የለውጥ ብርሃን እንዳያሳየን ፣በየጊዜው ጥላቸውን ሲያጠሉበት እና እዚህና እዜያ እሳት ሲለኩሱበት፣ነዳጅ ሲያርከፈክፉበት እንደነበረ እና ዛሬም እንገነጠላለን የሚል ማሥፈራርቾቻቸውን እንዳልተው እንገነዘባለን ለዚህም ኘው ገገሞች ናቸው የምንላቸው በአራድኛ።በዚህ ግግምናቸውም ፣ዛሬ እና አሁን  ሁለቱም ፍፃሚያቸውን በገዛ እጃቸው እያሰናዱ ነው።

ይሁን እንጂ መሪነን በማለት እንደቦክሰር ና ናፖሊዮን እነሱ ጮማ እየቆረጡ፣ውሥኪ እየተጎነጩ፣      ህዝብን ደግሞ በጎመን እየደለሉ  በቡድን ሥም ወይም በህዝብ ሥም መነገድ እሥከወዲያኛው ሲያከትም እና የህግ የበላይነት የሰፈነበት ፣ተጠያቂነት ያለበት፣ህግን የሚያከብር ዜጋ በመላ ሀገሪቱ  ሳይሸማቀቅ የሚኖርበት የፖለቲካ፣የኢኮኖማ እና የማህበራዊ ኑሮ መደላድል ሲፈጠር  የለውጥ ኃይሉ ፣በዘረፋ የከበሩትን የእጃቸውን እንዲያገኙ ማድረጉ አይቀርም።እነዚህን እንቅፋቶች በህግ አግባብ ከቀጣ በኋላ፣ እጅግ እፁብ ድንቅ የሆነ ዜጎችን ሁሉ የሚያኮራ ድህነትን ታሪክ የሚያደርግ ሥራ እንደሚሰራ ተሥፋ በማድረግ ነው፣ብዙሃኑ ምንዱባን ህዝብ ብልፀግናን የሚደግፈው።

ዛሬ፣ዘርፈው የከበሩ፣በምርጥ አልጋ የሚተኙ፣በውብ ቪላ ቤት የሚኖሩ፣የቧንቧ ውሃ ለጣት መታጠብያ እንኳን የማይጠቀሙ በህዝብ ሥም፣ በትግሬነት፣ በኦሮሞነት፣ በአማራነት፣ በወዘተኝነት ሥም፣ የሚነግዱ፣በቀን አንድ ጊዜ፣ ለመመገብ ያዳገተውን ወጣት እንዴት አድርገን፣ቢያንሥ የዘረፍነውን እና በየቀኑ ጮማ እየቆረጥን በውስኪ የምንታጠብበትን  በወገናችን ሥም የዘረፍነውን ሀብት በአገር ብልፅግና ላይ አውለን ሥራ እንፍጠርለት የማይሉ ግን ደግሞ ለእነሱ በከንቱ እንዲሰዋ በፍርፋሪያቸው ለመደለል የሚጥሩ ፤ሀገርን ሰላም ሲያሳጡ፤ዜጎችን ሲያሳርዱ፣ሲያፈናቅሉ፣ሲያሥርቡ ና እንዲታረዝ ሲያደርጉ ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ መዝለቃቸው ይታወሳል።

ዛሬ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት “ አሥራአንደኛ ሰዓት የሚባል ነገር ያለመኖሩን “ ለእነዚህ፣የፍቅር፣የሠላም፣የወንድማማችነት፣የእኩልነት፣የመተሳሰብ ና አብሮ የመኖር ጠላቶች በግልፅ በመንገር ማምረሩን በግልፅ ነግሯቸዋል።የትግራይ ህዝብ ግን ደግሞ የመላው ኢትዮጵያውያን ወንድምና እህት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጦል።   መንግሥት አሥረአንደኛው ሰዓት በማለፉ    እኩይ ድርጊታቸውን  እሥከወዲያኛው እንዲያከትም ቁርጠኝነቱን በተግባር እያሳየ ነው።

“ ሀ” ብሎ በመጀመር የበጀት ድጎማቸውን አግዷል። “ እንሆ የፍፃሜው ጦርነት ተጀምሯል።” ቅንነት ካልፈጠረባቸውና መሞታቸውን ከዘነጉ ከጥቂት ፣በንዋይ ፍቅር ካበዱ የዳቢሎስ አገልጋዮች ጋር ደም የማይፈሥበት ጦርነቱ  እየተካሄደ ነው።ድሉም  ምንጊዜም ቅን ለሆነቱ የፈጣሪ አገልጋዮች ይሆናል።ከጅምሩ በፍቅር ፣ በይቅርታ፣በምህረት እንጂ በሰይፍ ድል አድራጊነት ሥለማያምኑ ድል የለውጥ ኃይሉ እንደሚሆን አልጠራጠርም።…

 

ጤና ይሥጥልኝ

 

2 Comments

 1. If you think Tigray or TPLF will just sit back and watch Ethiopia prosper while Tigray does not get a piece of the pie I say you must be really fooled by TPLF. The electricity GERD produces will reach countries as far as Tanzania . Tigray is becoming the industrialization hub while Ethiopia is becoming a genocide civil war hub with foreign debt accumulating and GDP decreasing in Ethiopia there is no way Ethiopia will not sell electricity for cheap allover to whoever pays foreign currency before Ethiopia start to use the electricity for local consumption.Just like the land grab went on in Ethiopia during Meles time the electricity grab will go on. Local consumption of electricity in Ethiopia will not get prioritised because it will not bring foreign currency. So the way I see it, Tigray is better off to become an independent country to get the electricity it needs from Ethiopia. As Eritrea became the number one coffee exporter by taking coffee from Ethiopia , Tigray is preparing to be the number one industrialization hub by taking electricity from Ethiopia. Plus As you know Tigray TPLF controls the Ethiopian economy currently . Dual citizenship Ethiopian born foreign nationals are allowed to invest in Ethiopia. So I say TPLF and the Tigray people are better off than the rest of Ethiopians even after Tigray become independent. Ethiopians gave their money to build GERD while Tigrayans pocketed saved up their money ready to build factories utilizing the electricity the GERD produces.

  TPLF does not need to get fed by Abiy
  TPLF knows how to feed itself as it has done ate up all Ethiopia while the rest were getting their leftovers thrown to them.
  Actually the poor Ethiopians are the ones who are loosing their lives to protect GERD from
  Egypt , TPLF will not loose lives to protect GERD but TPLF is set to benefit by investing as Ethiopian born foreign nationals even if Tigray declares independent country.
  Eritrea will side with Tigray too because Tigray will use Eritreas port with the ethio eritrean train passing right through tigray .

 2. Logistically

  I WANT TO GIVE YOU CLARIFICATION ON THE NEW POLICY REGARDING THE ETHIOPIAN BORN FOREIGN NATIONALS INVESTMENT OPPORTUNITIES IN ETHIOPIA :

  Tigray born will not necessarily mean Ethiopian born if Tigray becomes an Independent country . If Tigray becomes independent then Tigrayan owned businesses will be confiscated by the Ethiopian government. Foreign citizens who are born in Tigray will not be able to invest as locals , they can only invest as foreign investors.

  Only Ethiopian born foreign citizens will be able to invest as local investors .

  “Ethiopia further opens up sectors to diaspora and foreign nationals ”
  https://www.ethiopoint.com/ethiopia-further-opens-up-sectors-to-diaspora-and-foreign-nationals/

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.