ጀዋር መሐመድ የኢትዮጵያ አቤሴሎም መሆኑን ገሃድ እያውጣ ነው – ዋቅወያ ነመራ

/

(ጀዋር ሙሐመድ “የግድቡ ጉዳይ፡ ለጊዜያው ፕሮፓጋንዳ ብሔራው ጥቅም እንዳይጎዳ” በሚል አርስት በጻፈው ጽሐፉ ላይ የተሰጠ አስተያይት
ዋቅወያ ነመራ

ብዙ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ስለአቤሰሎም ላያውቅ ስልሚችል መጀመሪያ ስለአቤሴሎም ትንሽ ልግለጽ።ታሪኩ ክመጽሐፍ ቅዱስ የተወደ ስለሆነ መጽሐፍ ቅዱስን  የማትወዱ ወይም በመጽሐፉ የማታምኑ ወገኖቼ በመጽሐፉ አለማመን ወይም መጽሐፉን አለመውድም ፍጹም መብታችው ነው። ስለሆነም  የዚህም ጽሑፍም  ዓላማ ስለአንድ አመለካክት ወይም ሃይማኖት እንዳልሆነ  እባካችው ተረዱልኝ። እኔ ግን ስለአቤሰሎም ታሪክ  ስለማውቃው  ጀዋር “የግድቡ ጉዳይ፡ ለጊዜያዊ ፕሮፓጋንዳ ብሔራዊ ጥቅም እንዳይጎዳ” ሲል የጻፈውን ሳነብ የአቤሴሎም ታሪክ ወደ አኢምሮዬ መጣ።

የአቤሴሎም  ታሪክም  ከሞላ ጎደል እንዲህ ነው።  በ1035 ዓመተ ዓለም (B. C.) ገደማ  እንደተወለደና ከ1005 እስከ 965 ዓምተ ዓለም (B. C.) ገደማ  እሥራኤን ንጉሥ ሆኖ እንደገዛ  የሚነገርለት  ንጉሥ ዳዊት የሚባል የእሥራኤል  ንጉሥ ነበር።ይህ ንጉሥ አቤሴሎም የሚባል ልጅ ነበረው። አቤሴሎምም መልከ መልካም፤ ተግባቢ፤ እንዲሁም ሰዎች እንዲከተሉት የማድረግም ችሎታ ነበረው።   ይህ የንጉሥ ልጅ አቤሴሎም አባቱን አጥላልቶና አሳጥቶ ራሱን ንጉስ ማድረግ ፈለገ። ጧት ጧትም ተነስቶ  በአደባባይ ቆሞ ንጉሱ ፍርድ ሊሰጣቸው ቀጠሮ ሰጧቸው ክንጉሱ ፍርድ ሊሰሙ ወደ ንጉሡ የሚመጡትን ሰዎች እየጠራ “ጉዳይህ እውነትና ቅን ነው” ግን ቅን ፍርድ “እፈርድ ዘንድ ፈራጅ አድርጎ ማን በሾመኝ”  እያለ “የእሥራኤን ሰዎች ልብ ሰረቀ” ይባላል።

ጀዋር መሐመድ የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ እድገት አስፈላጊነትና ስለግብፅ ሴራ የጻፈው በሙሉ ሊባል በሚቻል ደረጃ ትክክልና መልካም ነው። ይሁን እንጂ ጀዋር ስለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ ክቡር ዶክተር አቢይ አህመድ  የፃፈው ከእውነት የራቀና ተንኮል ያለበት ይመስላል። ለምሳሌ አሜሪካና የዓለም ባንክ አደራዳሪዎች እንዲሆኑ አቢይ እንዳደረገ ይጽፋል። ባለፈው ጊዜ አቢይ በሃይል የተናገውም አምባ ገነን ስለሆነና ከተፎካከሪች ጋር  ተከራክሮ ማሽነፍ ሃሣብ ስለሌውና በሃሣብም ተከራክሮ መሽነፍ ስለማችል ነው እንዲህ በሀይል የሚናገረው  ይላል። አቢይ ወደ ሥልጣን ሲመጣና የፖለቲካ ተፎክክሪዎችን ሲያሳትፍ ግብፅም አቋሟን አለሳልሳ ነበር ነግር ግን አሁን አቢይ በተፎካካሪዎች ላይ መፎከር ሲጀምር ግብፅም በኢቲዮጵያ ላይ ተነስታበታለች እና አቢይ ንገሩ ክመበላሽቱ በፊት ክተፎካካሪዎች ጋር ይደራደር ይላል።  የግድቡም ጉዳይ በኢትዮጵይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መመራት ሲገባው ውጭ ጉዳይን  ወዲያ አሽቀጥሮ አቢይ ከመስኖ ሚኒስትር ጋር እንደፈለገ እያደረገ ነው ይላል። ደግሞ አሜሪካ ኢትዮጵያን በእርዳታ  ገንዘብ እያንበሽበሽችው ያለው አቢይ  በህዳሴ ላይ እየተለሳለሰ ስለሆነ ይሆናል ይላል።  እውነቱ ግን ይህ ሁሉ እየተረገ ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ አልታየም ጀዋርም ዝም ብሎ  በቃል ከመክሰስ ያለፈ ምንም ማስረጃ አላቀረበም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትልቁ ችግር ያለው ከውድቀት ከአለመማር እንጅ ከመውደቁ ላይ አይደለም ! - ጠገናው ጎሹ

እስካሁን  ጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለአደረጋቸው፤ ስለተናገራውና ስለአበረታታቸው ሕዝቡም ከሚያውቃቸው እውነቶች  እስቲ አንደንዶቹን ብቻ ለምሳሌ ያህል መጥቀሱ እዚህ ተገቢ ይሆናል። ጀዋር እንደሚለው ዲሞኪራሲን  የሚያመጣ  ከሆን በወለጋ ውስጥ 18 ባንኮች ሲዘረፉና ሰላማዊ ሕዝብ በየቦታው በጥይት ሲደል እነኚህን ፀረ ዲሞኪራሲ ተግባርና ፈፃሚዎችንም ያወግዝ ነበር እርሱ ግን አላውግዘም። ጃዋር እንደሚለው በዲሞክራዊ የሚያምን ቢሆን ኖሮ  በምርጫ ተወዳድሮ አሽነፎ ነበር። ግለሰቡ አሁን እያደረግ ያለው በሕዝብ ምርጫ  ሳሆን የመንግሥትን እጅ ጠምዝዞ በድርድር ሥልጣን ላይ ልወጣ ነው። ጀዋር በዲሞኪራሲ የሚያምን ቢሆን ኖሮ በፓርቲው ስብሰባ ላይ ደጋፊዎቹ ኦሮሞ ያልሆነውን ወይም ያልሆቺውን ፍቱ፤ ኦሮሞ ያልሆነውን ቄስም  ከገዳማችሁ አስወጡ ብለው ጥሪ ሲያቀርቡ ያቆማል እንጂ አያጨበጭብም ወይም አያሽካካም ነበር። ጀዋር ዘረኝነትና ስሜትን መቀስን እንጂ በሕይቱ አንድም ቀን እንኳን ሀገርን ቀርቶ  መንደርም አስተደድሮ አያውቅም። ሥልጣንምም ቢይዝ ይህንን ምስኪን ድሃ ሕዝብ እንዴት ክድህንቱ እንደሚያወጣና  ዲሞክራሲንም እንዴት እንደሚያ ሰፍን ምንም እቅድ ለሕዝም አቅርቦ አያውቅም እንዲህ ዓይነትም እቅድ  የለውም። ሌላ ቀርቶ ጀዋር ሙሐመድ ኦፌኮን መቀላቀሉ ይፋ ከሆነ ወዲህ ፕሮሰር መራራ የቆየ አቋማቸውን እየለወጡና አክራሪ ጸንፈኛ እይሆኑ  ለመምጣቻው ብዙ ማስረጃዎች አሉ።  ታዲያ ጀዋር በሃሣብ መከራከር የሚፈልገው ምኑን ነው (ስሜትን፤ ፀረ ዲሞክራሲነትን ወይስ  ዘረኝነትን)?

የጠቅላይ  ሚኒስትር  ክቡር  ዶክትር  አቢይ መንግሥት ምንም ጥፋት አይሠራምና ጥፋትም የለበትም  የሚል ግምትም ሆነ እምነት የለኝም። ጥፋቶችና ጉድለቶች እንዳሉበትም በሚግባ እረዳለሁ። ሌላ  ቀርቶ  መንግሥቱ  ራሱ  ቢጠየቅ  ሁሉንም  በትክክል  እየሠራሁ  ነኝ  ምንም ጥፋት የለብኝም ጥፋት የሚባል ነገር  ሠርቼ  አለውቅም  የሚልም  ሆነ ከዚህ በፊትም ያለ  አይመስለኝም።   መንግሥት የሰዎች ስብስብ ነው፤ የሚሠራ ማንም ሰው መሳሳቱ አይቀሬ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ የዶክተር አቢይ መንግሥት ምንም ለውጥ አላመጣም ለኢትዮጵያ  ዲሞኪራሲም መሠረቱን እንዲጥል የሚረዳ ምንም እንዳለደረገ ም ተብሎ  ሲነገር ይታያል ፤ ይደመጣልም። ይህም ከእውነት የራቀ አባባልና አመለካክትም ነው። ሌላ ቀርቶ  አሁን መንግሥቱን የሚቃወሙቱ ሁሉም ሊባል በሚቻል ደረጃ  የዲሞራሲን መሠረት ክሁሉም ጋር በጋራ ለመጣል ሲባል በአቢይ መንግሥት ምህረት ተደርጎላቸው ከውጭ የገቡና  በአለፈው መንግሥት ይታደኑ የነበሩ  “ወንጀልኞ” የነበሩ ወይም በአቢይ መንግሥት ከእስር ቤት የተፈቱ  ወይም የአቢይ ሥልጣን ከያዘ በኋላ  የተፈጠሩ ወይም የተመሠረቱ  አለዚያም በአቢይ መንግሥት ዘመን  እንደፈለጉ ለመሆንና የፈለጉትን ለመናገርና ለመጻፍ ነፃነት የገኙ ናችው። ይህ ማለት መንግሥቱ ለተፈካካሪዎችና ለጋዜጠኞች በለውታቸው ስለሆነ  በሙያቸው  ሥራቸውን  አይሥሩ መንግሥትን ከመተቸና  ጎጂ ይሆነውን ሥራ ከማጋጥ ችው ይቆጠቡ ማለት ፈጽሞ አይደለም።  ነገር ግን መልካም የተደረገም የመንግሥት ሥራም ካል መተረክና ለሕዝብ ማድረስም የእነርሱ ሥራ  ነውና  አይዘንጉ ማላት ብቻ ነው። አንዳንዶቹማ ራሳቸው የታወቁ የትነግ መንግሥት ክፍተኛ ካድሬ ሆነው ያገለገሉ መሆናቸው እየታወቀ  ዛሬ የፖለቲክ ተንታኝ ራሳቸውን አድርገው ዶክተር አቢይን በትነግ መንግሥት ውስጥ አገልግለዋል ብለው ሲያወግዙ ይታያሉ።  አብዘኛዎቹ  የመንግሥቱ ተቺዎች ይህ መንግሥት በRevolution ሣሆን በReform መምጣቱን ከቁጥር ውስጥ ሳያስገቡ  ተነስተው ይህ ለምን እንዲህ አልሆነም ይህ ደግሞ ለምን እንዲህ ሆነ ሲሉ ይደመጣሉ። ኦነግ ወለጋን ሲያተራምስ፤ ጃዋር ሙሐመድ ሁሉም ቦታ ገብቶ ሲፈትፍት፤ በየቦታ መፈናቀል ሲካሄድ፤ እንዲሁም ትንግ በመቀሌ  መሽጎ እስቲ ንኩኝ ሲል   መንግሥት ወታደርን  እንኳ  በቅጡ ሳይቆጣጠርና ሕዝቡን በመጠኑም ቢሆን በቂ ግንዛቤ ሳያስጨብጥ እርምጃ  መውሰዱ ክጥቅሙ ጉዳቱ ሊበልጥ እንደሚችል መገዘብ አለባቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በበርካታ ሱዳናውያን እየተተፋ ያለው ሌ/ጄነራል አብዱል-ፈታህ አል-ቡርሃንና በአል-ቡርሃን እየተነዳች ያለችው ሱዳን አሁናዊ ገጽታ - ጌታቸው ወልዩ (ከሜክሲኮ ባህረ-ሰላጤ)

 

ኢትዮጵያን እወዳለሁ የሚል ሁሉ መረዳት ያለበት አንድ መሠረታዊ ጉዳይ አለ። እሱም ሥልጣን የሚይዝ ማንኛውም መንግሥት፤ አክቲቪት ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራ የትኛውም ግለስብ ወይም ስብስብ፤ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ና ተራ አባል፤  ማንኛውም  ሃይማኖት ሆነ ተራ አባል፤  እንዲሁም ማንኛውም ሰው ሀገሪቷን የመጠበቅና የመንክባከብ ግዴታ አለበት።ከሩቅ  ቆሞ መንግሥትን  መተቸትና መንግሥትም ሁሉን ነገር እኔ እንደምፈልገው ያስተካክል ማለት አለአዋቅነት ብቻ ሳይሆን ቅንነትም የጎደለው አካሄድ ነው።  መንግሥትን መተቸት ብቻ ሳይን እርዳታ በሚያስፈልገው ግዜ ማገዝ፤ ለሀር መልካም ሲሠራ ጎሽ ማለት፤ ምክር የሚሰማ ሲሆን መምከር፤ ምክርን የማይሰማና ነገሮችን  የሚያጠፋ ከሆነ ደግሞ በአደባባይ መተቸት።  ሕፃንን የምናስደገው እኮ  ክርቅ በመተቸት ሳይሆን አሰፈላጊ ሆኖ ሲገኝ  ጠጋ ብለን ሰገራውን በመጥረግና ዳይፕሩንም  በመቀየር ነው፤ የሚፈለገውም መንግሥት የሚመጣው እንዲህ ነው። ሐቁ ግን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ምንም ሲስራ መንግሥት ስለሆነ ብቻ መተችት ሀገር ወዳድና ጀግንነት ይመስላል። መንግሥትን መተቸት ሀገር ወዳድነትም ጀግንነትም አይደለም።  ደግሞ መንግሥት በሀሪቱ ውስጥ የመታጠቅና ሕግን ለማስከበር ሕጋዊ እውቅና የተሰጠው ብቸና አካል  መሆኑ በሁሉም  መታውቅና መከበርም አለበት።

እነኚህን መሠረታዊ ነገሮችን ካነሳን ወደ ጀዋር መሐመድ እንመለስና ይህንን ጽሑፍ ልቋጭ። ሰሞኑን ጀዋር ሙሐመድና  አቶ ልደቱ አያለው በኦኤም  ኤን (OMN) ቴሌቪዥን ቀርበው ከመስከረም 30 በኋለ መደኛ መንግሥት ስለማይኖር እነርሱን ጨምሮ የሚቋቋም መንግሥት ነው ሕጋዊ ሆኖ ሀገሪቷን የሚመረው ብለው ነበር። ይህ ሃሣብ እነርሱ እንደአሰቡ ብዙ ተቀባይ ስለአላገኝና ዶክተር አቢይም ሃሣቡን በማጣጠል በሃይል ስለተናገሩ ጀዋር አዉቋሙን ቀይሮ  “እንወያይ ማለት ከመቼ ጀምሮ ነው ጠብ መፈለግ የሆነ ነው” ብሎ ጠየቀ። ይህ አባባል ጀዋር ጨዋና ውይይት ፈላጊ በአንጻሩ ደግሞ  ዶክተር አቢይን ፀብ ፈላጊ አስመስሎ ያቀርባል። እውነቱ ይነገር ከተባለ ለ87 ነፍስ መጥፋትና ለሌሎች ተመሳሰይ ወንጀሎችና ፀብ ፈላጊነት መከሰስ ያለበት ጀዋር እንጂ አቢይ አልነበረም። የአቢይ ጥፋቱ (እሱም ጥፋት ነው ከተባለ) ጀዋርን  ከመስከረም 30 በኋላ መከላከያ፤ ፖሊስ ወዘተ ለዚህ መንግሥት እንዳይታዘዝ ጥሪ በማድረጉና በሠራቸው በሌሎች በርካታ ወንጀሎች  በሕገ ወጥ ሥራውና በፀብ አጫርነት ወይም ቀስቃሽነት አለማሳሰሩ  ነው።  ጀዋር ሙሐመድ የኢትዮጵያ አቤሴሎም መሆኑን በገሃድ  እያሳየ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታሪክን ለባለታሪኩ፤ በተደረገበት ቦታ፤ በተፈጠመበት ቀን!! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

 

 

 

1 Comment

  1. አሜሪካና የዓለም ባንክ አደራዳሪዎች እንዲሆኑ አቢይ እንዳደረገ ይጽፋል-Ja-war

    ይህን የጻፈው ሌላ ሰው ቢሆን አዋጁን ጥሷል ተብሎ ገቢ ተደርጎ ነበር፡፡ አስቲ እንመዝነው-ይህ የጃዋር አባባሉ ከዚህ በፊት መቃብር አስቆፍረዋል ብሎ ከጻፈው ጋዜጠኛ ጋር ሲነጻጻር የጃዋር ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ሰውዬው አዋጅ፣ ህግ፣ ደንብ፣ መመሪያ የማያዘው ሽምጥ ጋላቢ —ይመስለኛል፡፡ ለዛውም በረመዳን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share