March 26, 2020
15 mins read

ይድረስ ለመላዉ ለኦሮሞ ነገድ – ሰመረ አለሙ

ሰመረ አለሙ([email protected])

ወደ አንተ ወደ ወገናቸዉ ይጠብቀናል፤ ይንከባበከበናል፤ከክፉ ነገር ይከላከለናል፤ ይመግበናል ብለዉ ለትምህርት የሄዱ የኢትዮጵያ ልጆች አንተዉ ክልል እንደወጡ ቀርተዋል ክልልህንም ንጹሃንን አግቶ ቁጭ ብሏል። ቤተሰብም  ሌት ተቀን በልቅሶ ነሮዉን ይገፋል። ብታዉቀዉ ኑሮ  እነዚህ ወጣቶች ያንተ እንግዶች ነበሩ ቤተሰባቸዉን ጥለዉ አንተን አምነዉ ሲመጡ ከዚህ እምነት ጀርባ ብዙ ነገሮችን ያካተተ ነበር። የኦሮሞ ታሪክ ነዉ ብለዉ እንደሚነገሩን ቤተሰብ ላጡ አባትና እናት እንደሆንክ ነዉ የምንሰማዉ ዛሬ ግን ያየነዉ ከዛ የተለየ ነዉ። እንግዲህ ታሪክ ብለዉ የነገሩንን እንመን ወይስ ያየነዉን? በእርግጥ ላንተ አስብልሀለሁ ያሉ ዉክልና ያልሰጠኸቸዉ ባንተ ስም የሚነግዱትን እናዉቃለን አንተንም ከሌሎች ወንድሞች እሀቶችህ ለይተዉ በተለየ መንገድ እንድታታይ በረቀቀ ስልት ከህዝብ እያራቁህ እንደሆነም ይገባናል። የዚህ ሁሉ ጠንሳሾች ሁለቱ ትግሬዎችና አረቦች ቢሆኑም ይህን እንዲያስፈጽሙላቸዉ ካንተ አካባቢ በተገኙ ግለሰቦች አማካይነት የጥፋት ፐሮጀክቱን በሚገባ እየተገበሩ ነዉ። አገር ይተራመሳል፤ ሰርቶ አዳሪ አገርህ አይደለም እየተባለ ይባረራል፤ይገደላል፤ይሰቀላል፤ይደበደባል፤ይቀማል፤ይሳቀቃል ሌላም ሌላም።

እነዚህ ተንኮለኞች ታሪክ ብለዉ የሚነግሩህ እዉነት አይደለም ወንዝም አያሻግርም። እንደ እዉነቱ ከሆነ ታሪክህ ታሪካችን፤ ኑሮህ ነሯችን፤ በደልህ በደላችን ነበር፡ የተባለዉን ትርክት ተንቆ በመተዉና  ንቆ መልስ የሚሰጥበት በመጥፋቱ ጊዜ አልፎ ጊዜ ሲተካ እያደገ እየፋፋ እዉነት እየመሰለ ሄደ  ሃቁ ግን ከዚህ በተቃራኒዉ ነበር። የደካማ አስተሳሰብ ትርክት እዚህ አድርሶናል። በቅርቡ እንኳን የኔ ልጆች የምትላቸዉ ስልጣኑን ተቆጣጥረዉ ባደረሱት ጫና የኢትዮጵያ  ህዝብ ልቡ ምን ያህል  ካንተ እንደሸሸ አንተዉ ምስክር ነህ።

ሌላዉ ኢትዮጵያዊ አገሬ ብሎ ሰርቶና ነግዶ ለመኖር ወደ ከለሉህ ክልል ሲሄድ በምን አይነት መንገድ እንደሚስተናገድ ጠንቅቀህ ታዉቀዋለህ።   ያለዉን ሊሰጥና ሊቀበል የተዘጋጀዉ የህብረተ ሰብ ክፍላችን እንደራቀህ ያንን ተከትሎ ምን ያህል እንደተጎዳህም በአሀዝ የተደገፈ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል  አንተም ታዉቀዋለህ። አንድ ሀገር ለማደግ  ሰላምና መረጋጋት ያስፈልገዋል ሰላምና መረጋጋት ከሌለ ሰዉ መዋእለ ንዋይም ሆነ የአእምሮ ሀብቱን ለመስጠት ወደ ክልሉ አይሄደም ክልሉም የሌለዉን ከሌላ ማግኘት ካልቻለ ሀብት መፍጠር ህልም ይሆናል በዉጤቱም ስራ አጥ ተበራክቶ አካባቢዉ የወንጀለኛና የቀማኛ ማእከል ይሆናል።

ቄሮ የተባለዉ መንጋ በሀሳብና በእዉቀት የተጎዳ፤ በክፉና በደካማ ሰዎች የሚጋለብ ጫት በቃመ ቁጥር በምናቡ የሚታየዉን ለመተግበር ያ ህንጻ የኔ ነዉ ይህ ድርጅት ለኔ ነዉ የሚገባዉ አይነት አካሄድ የትም እንደማያደርስ ሳትገነዘብ የቀረህ አይመስለኝም። ዛሬ ዚምባቡዌ ዉስጥ ቅኝ ግዛት ለማድረግ የሄዱት ነጮች መሬት እየተመለሰ ነዉ። አገሩን ከጠላት ተናጥቆ ያቆየዉን ግን ስም እየሰጡ በተከለለዉ ክልል ተጠቂ ማድረግ ግን በምንም መልኩ ተቀባይነት አይኖረዉም።

ጁዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ወስዶ ከየመን በብዙ ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘዉ አሜሪካ ዜጋ ሁኖ አሜሪካ የምትሰጠዉን ጥቅምና ነጻነት እያጣጣመ ማሰብ የተሳናቸዉንና ቄሮ ብሎ የሾማቸዉን  ዜጎች በወንጀል ያመጣዉን ብር እየሰጠ ሰላማዊዉን ህዝብ እንዲያስጨንቁ፤እንዲዘርፉ፤እንዲገድሉ ህገ ወጥ ተግባር እንዲፈጽሙ ማድረጉ በየትኛዉም ሀገር ህግ ተቀባይነት ባይኖረዉም በኦፒዲዮ ኢትዮጵያ ግን ገድሉ እንደ ጀግንነት ተቆጥሮለት አጃቢ ተመድቦለት በግፉ ከብሮና ተፈርቶ ይኖራል።  እነ ሌንጮ፤ ዲማ ነገዎ፤ ዳዉድ ኢብሳና የነሱ ቡድን ለወያኔ በዉርደት ልጆችህን አስረክበዉ ከፈረጠጡ በሗላ  ዛሬም እናዉቅልሀለን ሲሉህ መፍቀድ አልነበረብህም። ባለፈዉ ወደ ገደል የወረወሩት ዜጋ በወንጀል ተጣርቶ ብይን እስኪሰጥበት ወዳንተ ቀርበዉ እንዲሸሸጉ ባታደርጋቸዉ መልካም ነበር። ረስተኸዉ ካልሆነ በስተቀር 25፣000 የሚገመተዉን የዳዉድና ሌንጮ ጦር  ታሪክህ እንዲበላሺ በሴት የትግሬ ወታደር ያስማረኩብህ እነዚሁ ጉዶች ነበሩ። ለመሆኑ የት ታዉቃቸዋለህ 30/40/50 አመት በዉጭ ሀገር በጡረታ ከኖሩ በሗላ ነዉ ዛሬም እናዉቅልሃለን ብለዉ የተቀላቀሉህ? በእርግጥ የመጣዉንስ ለዉጥ ያመጡት እነሱ ነበሩ?  እርግጥ ነዉ ላንተ ነዉ የቆምነዉ አንተን እየጠቀምን ነዉ የሚሉህ በስልጣን ላይ ያሉ ያልወከልካቸዉ ተወካዮችህ ተጠቅመዋል ወፍራም ደሞዝ አግኝተዋል ልጆቻቸዉን ከሀገር ዉጭ ልከዋል አገር ቤትም ዘመናዊ መስፍኖች ሁነዉ ተንቀባረዉ እየኖሩ ነዉ ያንተ ኑሮ ግን አለመቀየሩን ባይናችን ተመልክተናል።

ወደ ነገራችን ስንመለስ የእነዚህ ህጻናት መታገት እነደ ነገድ  ሊያሳፍርህ ሊያሳስብህም ይገባል ስምህንም ምን ያህል ሊያጠለሸዉ እንደሚችል መገንዘብም ይኖርብሀል። ዛሬ ህዝቡ ልጆቹን ያገተዉ ኦነግ ሸኔ ነዉ አይልም ወይም ደግሞ ኦፒዲኦ ነዉ አይልም በጥቅሉ ኦሮምያ የተባለዉ ክልል ሂደዉ እንደታገቱበት ነዉ የሚያዉቀዉ። እርግጥ ነዉ የኦነግ ወታደራዊ ክንፉ ባንክ ሲዘርፍ የፖለቲካ አመራሮቹ አብይ አህመድ ጎን ቁጭ ብለዉ ቤትና መተዳደሪያ ተሰጥቷቸዉ የሀጢያታቸዉን ፍሬ እየበሉ ነዉ በመኖራችን ብዙ አይተናል የነሱንም ነገ እናያለን ብለን እንገምታለን የማይቀርም ነዉ።

እንግዲህ የነዚህ ልጆች ስቃይና እንግልት የኦሮሞ ነገድ እንጂ የኦነግ ሸኔ ስራ ብቻ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ኦነግ ሸኔን እንደ ባህር የሸሸገዉ የአካባቢዉ ኦሮሞ በመሆኑ። ዉድ የኦሮሞ ነገድ ሆይ  በተመሳሳይ ሁኔታ ልጆችህ ለትምህርት አምነህ በላክኸዉ ክልል ዉስጥ ቢታገቱብህ እንደ ወላጂ ምን ይሰማሀል? በእርግጥ ኦነግ ሸኔ ከደምቢዶሎ ህዝብ የተሰወረ ነዉን? የደምቢዶሎ ህዝብስ ልጆቹን ወደ ሌላ ክልል አልላከምን? በተመሳሳይ እነዚህ ልጆች ላይ የተደረገዉ በደል ወደ ሌላ ክልል በላክሀችዉ ልጆችህ ላይ ቢደርስ በጸጋ ትቀበለዋለህን  ብለን ብንጠይቅ መልስህ ምን ይሆናል? በእርግጥ ልጆቹ በማስፈራሪያነት በመደራደሪያነት እንደ ተያዙ እንገምታልን ሆኖም እንዲህ ያለዉ አሰራር ባርባሪክ በሚባለዉ ዘመን የነበረ የሞራል ደረጃ እንጂ ዛሬ ላይ እንዲህ አይነት የትግል ስልት ሲሰራበት አይሰተዋልም ስለሆነም  ኦሮሞን በክፋቱ ሊያስቡት ለሚፈልጉ በር የሚክፈት በመሆኑ እነዚህን ልጆች የባህል መንገድህን ተጠቀምህ ነጻ አዉጣቸዉ ብለን እንማጸናለን።በነሱ በኩል የሚገኝ የፖለቲካ ኪሳራ እንጂ የፖለቲካ ትርፍ እንደማይኖርም ላጋቾቹ ማስገንዘብ እንወዳለን። ዛሬ የተማረኩ ወታደሮች    መብታቸዉ ተጠብቆ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሳይቀር እንዲጎበኙ እየተደረገ ባለንበት ዘመን ለትምህርት የሄዱ ህጻናትን አፍኖ ማሰቃየት ከምን አንጻር እንደሚታይ በጤናማ አእምሮ ማሰላሰል ይከብዳል።  ትላንት አንድ ሚሊዮን ኦሮሞ ከሱማሌ ክልል ሲባረር በጉዳዩ ተጸጽተን ሰልፍ ወጥተናል ዛሬም አላግባብ በታገቱት ህጻናት ላይ ለሚደርሰዉ ግፍና ሰቆቃ ጩኸታችን ይቀጥላል።

ህጻናትና ሴት ልጆችን ማገት እንኳን የነጻነት ታጋይ ነኝ ለሚል ድረጂት ቀርቶ ለተራ ሺፍታ፤ ቀማኛና ወንጀለኛ የሚመጥን ተግባር ባለመሆኑ ልጆቹ ተፈተዉ ወደ ቤተሰባቸዉ በክብር የሚሸኙበት ሁኔታ እንዲዘጋጅ በሰብአዊነት ስም እንጠይቃለን። ከነንጉሱ ጥላሁን ፍትህ ከምንጠይቅ ከባለቤቱ መጠየቅም አግባብነት ያለዉ አካሄድ ይመስላል።

ለማንኛዉም ጉዳዩን ለማጠቃለል ከየነገዱ የሀገር ሺማግሌዎች፤ ኑሮ  ያስተማራቸዉ አባቶች፤ ክፉዉን ከደጉ የለዩ፤  ባደረጉት አስተዋጽኦ ህብረተሰቡ  ክብር የሰጣቸዉ የኦሮሞ አባቶች በድፍረት ይህንን ነገር አዉግዘዉ ልጆቹ ተፈትተዉ ወደመጡበት እንዲመለሱ እንዲያደርጉ በዚህም ታላቅነታቸዉን እንዲያሳዩን እንጠይቃለን። የደቡብ ሺማግሌዎች ለነብሳቸዉ ሳይሳሱ ትልቅ እልቂት አስቁመዉ አይተናል ከኦሮሞ ሺማግለዎችም ተመሳሳይ ተግባር እንጠብቃለን። የነዚህ ልጆች መኖርና አለመኖር በሂሳብ አንጻር ብዙም ጉዳት ላያመጣ ይችላል ለኦሮሞ ነገድ ግን ጊዜ የማይፍቀዉ ክፉ ጠባሳ ስለሚተዉ ማንኛዉም የኦሮሞ ነገድ ይህ ተግባር ከእርሱ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ልጆቹ ተመልሰዉ ወደመጡበት እንዲሄዱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እንማጸናለን። መንግስት ተብዬዉ እንዴት እንደተዋቀረና እነማን እነደሚያሸከረክሩት ስለምናዉቅ በዛ በኩል ያለዉ ነገር ተስፋ አስቆራጭ በመሆኑ መላዉ የኦሮሞ ነገድ ጉዳዩን ጉዳዬ ብሎ እነዚህ መታሰር የማይገባቸዉን ህጻናትን አስፈትቶ ከይቅርታ ጋር እንዲሸኛቸዉ ከወላጂ ጭንቀት አንጻር ጉዳዩን እንዲመለከቱት እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሰመረ አለሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop