August 28, 2024
5 mins read

አሜሪካ በዐቢይ አህመድ የተሾሙትን የሌንጮ ባቲን የአምባሳደርነት ሹመት አልቀበልም አለች

456668044 2750390011800456 1633307317353207615 n

በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው አምባሳደር ነው !!

ሹሞቻቸውን በስልጣን ላይ የማያበረክቱት የብልጽግናው መሪ ዐቢይ አህመድ አሊ በ6 ዓመታት ውስጥ ሹመው የሻሯቸው ባለስጣናት ብዛት ካለፉት 60 ዓመታት ሹም ሽር ጋር አቻ ነው የሚሉ አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡

ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ስልጣናቸውን ስለማያምኑ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች “አንድ ባለስልጣን በአንድ መስሪያ ቤት ላይ ከሰነበተ ያሴርብኛል” የሚል ፍራቻ አላቸው ይላሉ፡፡

በዚህም የዐቢይን የሹም ሽረት ዜና መስማት ከችግኝ ተከላቸው ዜና የተለየ ክብደት እንደሌለው ይነገራል፡፡

ከዓመት በፊት ከውሃና መስኖ ሚኒስቴርነት አንስተው በፍጹም አረጋ ቦታ የሾሟቸውን ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡

ታዲያ በወቅቱ ሮሃም ምንጮቿን ዋቢ በማድረግ ዐቢይ ኢንጂነር ስለሺን በሌንጮ ባቲ ለመተካት ማቀዳቸውን ዘግባ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ላይ የሮሃ የውስጥ ምንጮች ባደረሱን መረጃ መሰረት የአሜሪካ መንግስት በዐቢይ የተሾሙትን አቶ ሌንጮ ባቲን መቀበል አልፈቀደም፡፡

በዚህም አቶ ሌንጮ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት ማጣታቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡

 


ይህም ሰውዬውን በኢትዮጵያ ታሪክ በተሾሙበት አገር መንግስት ተቀባይነት ያጡ የመጀመሪያው ሰው ያደርጋቸዋል፡፡ ይህም ከንጉሱ ጊዜ ጀምሮ የታፈረና የተከበረ የነበረውን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዝቅ ያደረገ ሁነት ነው፡፡ በተጨማሪም አገዛዙ ምን ያህል የዘቀጠ የዲፕሎማሲ ቅርቃር ውስጥ አገሪቱን እንደከተታት አንዱ ማሳያ ሆኗል፡፡

ከቀጠናው እስከ አለም አቀፉ መድረክ የተናቀውና ፣ የተገፋው የብልጽግናው አገዛዝም ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀውን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከነበረበት ከፍታ አውርዶ በዳዴ እያስኬደው ነው፡፡

የሚገርመው ደግሞ ሮሃ ባደረገችው ማጣራት ሌንጮ ባቲ የጾታዊ ትንኮሳዎች እና ሌሎች ተያያዥ ክሶች የነበሩባቸው በመሆኑ ነው የአምባሳደርነት እውቅና ማግኘት ያልቻሉት፡፡

ይህም ስርዓቱ ለጾታዊ ጥቃት ያለውን ቦታ በግልጽ ያሳየ ሆኗል፡፡ ታዲያ በህጻን ፌቨን መደፈር የአዞ እንባ ያነቡት የስርዓቱ ቁንጮዎች እነ አዳነች አቤቤ ሌንጮን ከእነ ነውራቸው ለአምባሳደርነት ሲልኩ ግን አልኮሰኮሳቸውም፡፡

ስለተደፈሩ ሴቶች ሲጠየቁ “እነሱ እኮ የተደፈሩት በወንድ ልጅ ብልት ነው፣ አታካብዱ ” ያሉት አብይ አህመድ በጾታዊ ጥቃት የተወነጀሉትን ሌንጮ ባቲን ሾመው መላካቸው ምንም እንኳን የሚያስገርም ባይሆንም ሃገርን አንገት የሚያስደፋ ተግባር መሆኑ ግን የማይታበይ ሃቅ ነው፡፡

ዐቢይ ሌንጮን ከሳዑዲ አረቢያ አንስተው ወደ አሜሪካ መውሰድ የፈለጉት እንደ አሜሪካ ያሉ ወሳኝ አገሮች ላይ የስርዓቱን ታማኞችና ባለቤት የሚሏቸውን መሰግሰግ ስለፈለጉ ነው የሚሉ መረጃዎችም አሉ፡፡ ሮሃም በጉዳዩ ዙሪያ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል፡፡

1 Comment

  1. ጸሀፊ የመጀመሪያው ሰው አይደለም ሲባረር ኤርትራ ሬድዋን ሁሴንን የተጣለ ቀፎ ነው ብላ 6 ወር ሲያዛጋ ከርሞ ተባርሯል። አምባሳደሮቹ የተላኩባቸው አገሮች ለኛ አሳቢ ሆኑ። እንዴት ሰው በሌንጮ ባቲ፣ሱሌማን ደደፎን፣ ሬድዋን ሁስሴን አይነቶች ይወከላል?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Amhara Media Amico
Previous Story

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አሚኮን በምክትል ስራ አስፈፃሚነት የሚመራው የብልፅግናው ሹም በቁጥጥር ስር ዋሉ

193473
Next Story

ፋኖ የሚዋጋዉ ለጽድቅ አይደለም ተባለ | አረጋ ከበደ መርዶ ሰማ | አሜሪካ እነ ጌታቸውን አስጠነቀቀች

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop