August 26, 2023
8 mins read

 ከአመድ አፋሽ ወደ ደም አፍሳሽ

Abiy apointed Amhara pesident 1 1

በኢትዮጵያ  የፖለቲካ  ንቅናቄ እና የለዉጥ ፍላጎት እና ጥያቄ ከጥንት አስካሁን የዓማራ ህዝብ ድርሻ ቀላል አለመሆኑን የታሪክ ድርሳናት እና ትዉልድ የሚዘክሩት ከመሆን በላይ ያላፉት ዘመናት በኢትዮጵያ የተስተዋሉት የፖለቲካ እና ስርዓት ለዉጦች ዓይነተኛ ማሳያወች ናቸዉ ፡፡

ከንጉሰ መገስቱ የዘዉድ ስርዓት ወደ አብዮት ለዉጥ እንቅስቃሴ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር በመሆን የግንባር ቀደም ተሳትፎ መኖሩን ዓለም የሚያዉቀዉ ፀሀይ የሞቀዉ ገሀድ ነዉ ፡፡

Abiy Ahmed warበግል እንኳን መጥቀስ ቢቻል ብዙዎች የዘዉድ ስርዓቱን እንደ ጣኦት በመያመልኩበት እና በሚፈሩበት ጊዜ የትግሉን ችቦ ያቀጣጠሉት እና የመሩት እነ ኮሎኔል አጥናፉ አባተ እና ጥግል ጓዶች ያለፈ ሥርዓት ናፋቂ ሳይሆኑ የህዝብን ፋላጎት እና የአገርን አንድነት መሰረት ያደረገ ብሄራዊ ለዉጥ እና ዕድገት ለማምጣት ነበር ፤ ነዉ ፡፡

ይሁን ዛሬም ላይ ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚደረገዉ የጥላቻ እና ዛቻ ቅስቀሳ ያለፈ ስርዓት ናፋቂ እና አድናቂ፣ አሀዳዊ፣ ብሄራዊ ፣ ኢትዮጵያዊነት….ሲባል ምን ያህል ከታሪክ እና ዕዉነት መራቃችንን የሚያሳይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ፡፡

አዚህ ጋ ሳይጠቀስ የማይታለፈዉ የዓማራ ህዝብ ኢትዮጵያዊነት እና ብሄራዊነት ብዙዉን እና የረጂም ዘመናት የአገር ባለዉለታነት ትተን በ1966 ፣ በ1983፣ 2008   እና መጋቤት 2010 ዓ.ም. ብልጭ ብለዉ ድርግም ያሉት የለዉጥ ምልክት ፋና ወጊነት የዓማራ ህዝብ የጎላ ድርሻ ምስክር የሚያስፈልገዉ አይደለም ፡፡

ሳይጠቀስ የማያልፈዉ በአገሪቷ ለዓመታት ሲከናወን ከነበረዉ የህዝብ ጥያቄ እና የአግሪቷን የለዉጥ ፋላጎት ከኋላ ተነስተዉ ከፊቴ በመደንቀር የየጊዜዉን የታግድሎ ዋጋ የሚያሳንሱ አስመሳዮች እና አድር ባዮች በተለያየ ጊዜ ተከስተዋል ፡፡

ይህም ከረጂም ጊዜ አሁን አስከምንገኝበት ጊዜ እና ሁኔታ ሲቀጥል በዜጎች የህይወት እና የአካል ዋጋ በማሳጣት ለግል እና ቡድን ጥቅም መረማመጃ ማድረግ የማይረካዉ ብአዴን ዛሬም በለመደዉ መንገድ መጓዝ ቀጥሏል፡፡

ይህም በአምስት ምዕራፍ ሲታይ ፡-

  • የዓማራ ህዝብ የቀድሞዉን መንግስት ስርዓት ለማስወገድ ከፍተኛዉን ድርሻ የተወጣዉ እና ለኢህአዴግ መፈጠርም ሆነ መኖር መሰረት የሆነ ህዝብ ከኢህዴግ መስረታ(1982 ዓ.ም) ማግስት ክህደት እንዲፈፀም ብአዴን የኢህአዴግ ባለዉለታ ለኢትዮጵያ እና ዓማራ ህዝብ ጠላትነቱን አሳይቷል፣
  • ኢህአዴግን ዕጁን ይዞ ለስልጣን ያስገበዉን የዓማራ ህዝብ እና ምርጥ ልጆች በመካድ ማሳደድ ሲጀመር ብአዴን ለዚህ ተባባሪ መሆን፣
  • በኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት አገርም ፤ህዝብም እና አህአዴግም በዓማራ ህዝብ ሲሆን ከጦርነት በኋላ የተካደ እና የተሳደደ ህዝብ ፣
  • በምርጫ የተካደ ፣
  • በትህነግ ወረራ እና ምዝበራ የተነሳዉ ጦርነት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ፤ የዓማራን ህዝብ ከምደርረ ገፅ ለመደምሰስ  ጦርነት ሲታወጂበት በጦርነት የጠዋደቀዉም ሆነ የተወረረዉ ህዝብ ዓማራ ሆኖ ዓማራ ሲከሰስ ብአዴን ከሳሽ ኆኗል ፣
  • የዓማራ ህዝብ በላቡ እና በደሙ የያዘዉን መሳሪያ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲፈታ (1ኛዉ ፡ ኢህአዴግ ሲገባ ትጥቅ አይደለም ዜግነቱን እንዲያጣ ሆኗል) በዚህ በምንገኝበት ዘመን ተገዷል ፤
  • በቀለላል እና በጥበብ ሊታረቅ  የሚችልን ቅራኔ እና የህዝብ ታሪካዊ እና ወቅታዊ የማንነት እና የህለዉና ስጋት ” በጥቁር ጠበንጃ ” ሰበብ “ጥቁር የጥላቻ ታሪክ ሙጃ ” ተዘርቶ አንዲስፋፋ የመሀል ተመልካች ሆኗል ፣

ከዚህም በላይ ሰሞኑን አንድ አገር ፣ አንድ ህዝብ  እና የጋራ ማንነት የሉዓላዊት አገር መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ይህ ለዘመናት አስካሁን እንደ ጥፋት እየተቆጠረ ተወቃሽ  ወቃሽ ሲሆን የብአዴን አድር ባይነት እና አይቶ ማለፍ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ ህዝብ እና የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት መደፈር እና መወነካከር ለሆነዉ ተደጋጋሚ  ክህደት እና ለሚደርሰዉ ጥፋት ኃላፊነት ያለበት በስሙ ለሚገለገልበት የዓማራ ህዝብ ለደረሰበት መጠነ ሰፊ ግፍ እና በደል ተጠያቂ ያደርገዋል ፡፡

በአዴን ለእናት ፣ አዉራ ወይም እህት ድርጂቱ ባለዉለታነቱ ከላይ በተጠቀሱት እና በሌሎች ባልተጠቀሱት  ሁነቶች  ከፍ ያለ ሲሆን በተቀራኒዉ ለህዝብ ባላናጣነቱ በዚኅ ልክ መደጋገሙ  ደረጃዉን ከአመድ አፋሽነት ደም አፋሳሽነት ማሳደጉ ባለፉት ጥቂት ዓመታት አረጋግጧል፡፡

የብአዴን በድንነት በታረክም በትዉልድም በይቅርታ እና ህዝብን በማገልገል ሳይታደስ በዚህ ደረጃ መድረስ በዕዉነት ለአገር እና ለህዝብ ከማገልገል ይልቅ ለአላፊ እና ጠፊ ነገር ክፉ ስም ይዞ ማለፍ ምን እንደሚያስደስት ራሱ ዕመረዋለሁ ከሚለዉ ህዝብ አልፎ ዲያብሎስን ያስናቀ ክፋቱ እና  ጥፋቱ ዓለምን ግራ አጋብቷል ፡፡

በቃ…….ዉርደት ፤

በቃ …ስደት፣

አይበቃም ወይ  …እየሞቱ መሞት ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ !

 

Allen!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop