የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት የመልቀቂያ ደብዳቤ

ቀን፡- ነሐሴ  25/2015 .

ለአብን ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተወካይ ኮሚቴ

      ባሉበት 

ጉዳዩ፡ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የለቀቅን መሆኑን ሰለማሳወቅ፤

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እንዲሁም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በርካታ አባላትንና ደጋፊዎችን በማነቃነቅ ቀላል የማይባሉ ተግባራትን  አከናውኗል፡፡ ንቅናቄው የፖለቲካ ዓላማ ከግቡ ለማድረስ በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የነበርን የንቅናቄው  አመራርና አባላት ከቅድመ ምስረታው ጀምሮ ተቋሙ ጠንካራና አታጋይ ድርጅት እንዲሆን ለማስቻል ከትግል ጓዶቻችን ጋር ተሰልፈን የምንችለውን ሁሉ አስተዋጽኦ ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት አብን ይዞት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ከድርጀት ደንብ፣ መመሪያና አሰራር ውጭ የሆኑ ተግባራትን አብዝቶ በመከዎን ከሕዝባዊ ዓላማው እየተነጠለ በመምጣቱ ምክንያት ችግሮች እንዲስተካከሉ በውስጥ ዴሞክራሲያዊ ትግል ለማስተካከል ያላሰለሰ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ለአብነት ያህል መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጉባኤተኛው እውነትና መርህን መሠረት በማድረግ ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል እጅግ የምንኮራበት እና በታሪክ ለትውልድ ሁሉ የሚተላለፍ በጎ አሻራ እንደሆነ እናምናለን፡፡

ሆኖም በጉባኤተኛው በኩል የቀረቡ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠትና ከመፈፀም ይልቅ ስራ አስፈፃሚው፣ ማዕከላዊ ኮሚቴው እና ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ ስህተቶችን እየተለማመዱ በመምጣታቸውና ለመሻሻልም ዝግጁ ባለመሆናቸው ተቋሙ ወደ ባሰ ችግር  ሲገባ ተስተውሏል፡  የተቋረጠው ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እንዲካሄድ ለማድረግ የጉባኤው ተወካይ ኮሚቴ ተመርጦ ከአንድ ዓመት በላይ የታገልን ቢሆንም ጉባኤው በድጋሚ ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ይህ በመሆኑ ድርጀቱ ችግሮችን ከማረም ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ የቁልቁለት ጉዞውን አፋጥኗል፡፡ ስለዚህ  በዚህ ወቅት የንቅናቄው ችግር ሊጠገንና ሊስተካከል ከማይችልበት ደረጃ ላይ  እንደደረሰ እናምናለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  “መንግሥቱ ኃ/ማርያም የአገራቸው ናፍቆትና ፍቅር አሁንም በልባቸው የነደደ ነው፤ አለ።” - ገነት አየለ

ከፍ ሲል ከተገለጹት መሰረታዊ መነሻዎች ባሻገር ቀጥሎ የተዘረዘሩት ማለትም፡-

1ኛ) የአብን ሥራ አስፈፃሚ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አካላት የተጣለባቸውን ድርጅታዊና ሕዝባዊ ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣታቸውና ከንቅናቄው መርህና አሰራር ያፈነገጡ ተግባራትን በመፈጸማቸውና እየፈጸሙም በመሆኑ፤

2ኛ) የአብን ከፍተኛ አመራሮች እየታየባቸው የሚገኘውን በርካታ የአሰራር ግድፈቶችና ችግሮች ለማረም እንዲሁም በጠቅላላ ጉባኤ አባላት የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁና  ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፤

3ኛ) በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የሥራ አስፈጻሚ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ እና የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት የሥራ ዘመን ሦስት ዓመት ብቻ መሆኑ የተደነገገ ቢሆንም የሥራ ዘመናቸው ከሦስት ዓመት በላይ እንዳለፈ እየታወቀ የድርጅቱን መርህና አሰራር በመጣስ አሁንም ድረስ በአምባገነንት የቀጠሉ በመሆኑ፤

4ኛ) የተቋረጠው 3ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በድጋሚ እንዲካሄድ ለማስቻል በጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተወካይ ኮሚቴው በኩል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀረበው ጥያቄ መሰረት የተሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ ለመፈፀም ዝግጁ አለመሆናቸው እንዲሁም ከአመራርና አባላት ባለፈ የህዝቡን አንድነት የሚሸረሽሩ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ላይ በመሆናቸው፤

5ኛ) የአማራ ህዝብ ከገጠመው የህልውና አደጋ አንፃር አብን አመራሮቹን፣ አባላቱንና ደጋፊዎቹን አስተባብሮ በማታገል የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ከማድረግ ይልቅ ራሱ የአማራን ህዝብ ወደ መታገል በመሸጋገሩ፤

6ኛ) ድርጅታዊ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት የማይታይበት ከመሆኑም በተጨማሪ ከአብዛኛው የለውጥ ፈላጊ አባላትና አመራር ይሁንታ ውጭ በጥቂት አካላት የሚዘወር በመሆኑ እንዲሁም ንቅናቄው የአማራ ህዝብ ተሰፋ ከመሆን ወጥቶ የአማራ ህዝብ በፖለቲካዊ ትግል ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርጉ ገፊ ሁኔታዎች እየተከተለ በመምጣቱ እና የመሳሰሉት ከዋና ዋና ችግሮች መካከል ናቸው፡፡

በንቅናቄው የተለያዩ ደረጃዎች የነበርን አመራሮችና አባላት የአማራ ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥያቄዎች አለመመለሳቸው ብቻ ሳይሆን አማራ እንደ ህዝብ የ ልውና አደጋ የተጋረጠበት መሆኑን ጠንቅቀን ስለምናውቅ ከዚህ በኋላ በድርጅቱ ውስጥ በአባልነት መቀጠል ለአማራ እዳ እንደመሆን አድርገን እንገነዘባለን። ስለሆነም ትግሉ የአማራን ህዝብ አቅምና ፍላጎት በሚመጥን ደረጃ ለማስቀጠል እንዲሁም ከመሰል ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በመሆን ትግሉን ለማጠናከር ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው ይህ ደብዳቤ ከተጻፈበት ቀን ጀምሮ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መዋቅር ስር ከነበረን የአመራርነት ኃላፊነትም ሆነ ከአባልነት የለቀቅን መሆኑን በአክብሮት እንገልፃል፡፡

  1. አንተነህ  ስለሺ
  2. ስንታየሁ  ማሞ
  3. ንጉሥ  ይልቃል
  4. አለሙ  ወልዴ
  5. ኤፍሬም  ሲሳይ
  6. ታርቆ   ፈንታው
  7. ፍሥሐ   አታለል
  8. ዶ/ር ጌታሁን  ሳህሌ
  9. መሐሪ  ሲሳይ
  10. ደግሰው  ጥላሁን
  11. ዶ/ር አለሙ  ብዙወርቅ
  12. አስማማው  ሰማኝ
ተጨማሪ ያንብቡ:  “ሸኔን ያደራጀነው እኛ ነን - ፋኖ ግን ያቀድነውን አላማ አክሽፎብናል” -| 80% የአማራ ክልል ብልጽግና ፈርሷል"

 

ከሰላምታ ጋር፤

1 Comment

  1. ወንድሞች፦
    እጅግ የዘገያችሁ ቢሆንም ይህን ካለማድረጉ ማድረጋችሁ ይመረጣልና ውሳኔያችሁ ትክክል ነው፡፡ ለሎችም አርአያነት አለው፡፡ አማራው በደሙ በአጥንቱ በአንድነቱ ክልሉን ከወራሪ መንጋ የኦሮሙማ ሰራዊት ነጻ አድርጎ አገሩን ኢትዮጵያንም ለማዳን ከመሰል ወንድም ኢትዮጵያዊያን ጋር ይሰለፋል፡፡
    የአብን መሪ ተብየው አጎዛ በለጠ ሞላ [ ስሙን ቀለጠ ሰመጠ ቢሉት ይሻል ነበር ] የትም አይደርሱም፡፡
    የትግሉ መዳረሻ አራት ኪሎ የሰፈረውን የወያኔና የኦሮሙማ ጥምር መንጋ ድባቅ መትቶ ህዝቡ በሙሉ ነጻነቱ ስለአገሪቱ እጣ ፈንታ እንድወስን ማብቃት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ምድራዊ ሀይል የአማራው ተጋድሎ አያቆመውም፡፡ ድል ለፋኖ፡፡ እኔም ፋኖ ነኝ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share