April 26, 2019
21 mins read

ትንሣኤ ለኢትዮጵያ “አርጋጅነትን “ለማሶገድና ” አልጫ ፍቅርን” ለመቀነሥ ፣  የባህል አብዮት ያስፈልገናል

ከመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
        ድንገት የሚገራርሙ ሃሳቦች እንዲጫሩ፣መንሥኤ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊ ምሳሌዎች አያሌ እንደሆኑ ይታወቃል።
ለዛሬ ሁለት ምሳሌዎችን አሥንቼ ፣  “የኢትዮጵያን ትንሣኤ በመሻት ” የወቅቱን የኢትዮጵያን ፖለቲካ በወፍ በረር በመዳሰሥሥ፣ እግረ መንገዴን፣በዚች ሀገር ሳይዘገይ የባህል አብዮት መጀመር እንደሚያሥፈልግ ምሤሌዎችን ተገን አድርጌ እጠቁማለሁ ።
 አንደኛው የአበው ምሣሌ ” ላለው ቅጭብም ያረግዳል።” የሚል ነው። እርግጥ ነው፣ ሰው ከአምሳያው አንዳች ለማግኘት ሲል ፣ካለው ላይ እንዲያካፍል ለማድረግ፤ወይም ያለው ሥልጣን ነውና በሥልጣኑ ተጠቅሞ አንዳች እንዲሰጠው ወይም እንዲያደርግለት በመፈለግ  ሲያሽቃብጥ ይሥተዋላል።በዚች ዳቦ ባረረባት ና እንደልብ ዳቦ ለመብላት ሥልጣን መያዝ ቀላሉ አማራጭ በሆነባት እና የበለፀጉት ሀገሮች” ቼዝ ” በሆነችው አፍሪካ።
  የእኛን ሀገር  ጨምሮ በአፍሪካችን ፣ የጉልበት እና የምዕራቡ እጅ የተጫነው የፖለቲካ ውድድር ነውና የሚሥተዋለው።  ደሃ ሀገራት ፣ ለሀብታሞቹ ሀገራት ያሸረግዳሉ። በነገራችን ላይ ፣ አፍሪካን ቼዛቸው ያደረጓት ምዕራባውያኑ ብቻ አይደሉም ። ቻይና ሩሲያ ና አሜሪካም ፣ በተትረፈረፈ ሃብታቸው ተጠቅመው ፣ የዕብድ ገላጋይነት ሚና ተላንት ተጫውተዋል።ዛሬም እንደማይጫወቱ መመሥከር ከቶም አይቻልም።
  እነዚህ በጥበብ የተመነደጉ ሀገሮች ፣ለምንድነው ከጥበብ መራቃችንን እያወቁ ፣ የባሰ ከጥበብ እንድንርቅ የሚያደርጉን ?ለምንድነው ለሸቀጦቻቸው ማራገፊያ ሆነን እንድንቀር ፣በየጊዜው በሥውር እጃቸው ወደኋላ የሚጎትቱን ???
   ለምንድነው ፣ ግብርናችንን ዘመናዊ ለማድረግ በቅንነት ቢያግዙን ባልተራዘመ ጊዜ ከድህነት  ለመውጣት እንደምንችል እያወቁ ፣የነሱ ሥንዴ ጥገኛ የሚያደርጉን??? ለነሱ በጥበብ ፣በዕውቀት፣በብልፅግና ፣ ለተመነደጉ ፣  ዘላለም አላማችንን አጨብጫቢ እንድንሆን አይደለምን???ቅጭብ ሆነን በቅጭብ አቅማችን ማሸርገዳችንን እንድንቀጥል ስለሚፈልጉ አይደለም እንዴ???
የእኛሥ ሀገረ መንግሥት ይህንን አሸርጋጅነት አሜን ብሎ ተቀብሎ ሲያበቃ ፣በተራው በጎሣ ቡድን ተደራጅቶ የበዙ ቅንጭቦችን  ፣በትንንሽ ሥልጣን እና ጥቅም ይዞ አፈር ለሚሆን ሥጋና ሲሞት ለማንም ጥሎት ለሚሄደው  ቁሥ ፣ እየተንሠፈሰፈ ሲኖር የምናሥተውለው።
   ሰው መሆኑን የዘነጋ ፣ የቋንቋ ጦረኛ ሁላ ፣ “እኔ ቋንቋ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም።አምሳዬንም ያለቋንቋዬ ሰው መሆኑን አልቀበልም ።” የሚል ከጥበብ የራቀ” ምሥኪን ” ሁላ ፣ እዛና እዚህ  ክልል በመጠየቅ አጥር አጥሮ ለመቀርጠፍ ሲተረማመሥ እናሥተውላለን።
    የዚህ ትርምሥ ሰበብ ደግሞ ግለፅ ነው።ትላንት ትቢያ የነበሩ ፣ዛሬ ቢጠሩ የማይሰሙ ሀብታሞች የሆኑት  ፣ የቋንቋ ፖለቲካ ፣ቋንቋውን ማወቃቸው ብቻ ፣ የቀበሌ፣የወረዳ፣ የክፍለ ከተማ   የዞን ፣ የክልል አሥተዳዳሪ ሥላደረጋቸው ነው።
      ዛሬም ለነዚህኞቹ ሙቅ ለሚያኝኩ  የሚያሸረግድ ጥቂት አይባልም። ጭራውን የሚቆላ ፣ውን ውን የሚያደርግ፣።የሚያሽቃብጥ፣ ለተትረፈረፈው፣ሥልጣንን የመጨቆኛና ጥቅም ማግኛ መሳርያ ላደረገው ሰው ፣የሚያረገርግ ጥቂት አይባልም። በዚህም አድራጎቱ ጥቂት ቅንጥብጣቢ እንደሚወረወርለትም ያውቃል።
   “ለምን መጠቀሚያ ትሆናለህ? ለምን ታሸረግዳለህ? እንዲህ እንደውሻ ጭራ ቆልቶ   ከሚበላሥ ቢቀርሥ???” ብላችሁ ብጠይቁት አይኑን ሳያሽ ፦
     “የተሻለ ኑሮ ለመኖር መፍትሄው ማሸርገድ ከሆነ ፣ለምንጭራዬን አልቆላም ?ለምንሥ አላሸረግድም? ቀላል አሸረግዳለሁ እንዴ?” የሚላችሁ  ጥቂት አይሆንም።
      በሀገራችን አቋራጭ የመክበርያ መንገድ ይህ ሆኖ ከተገኘ  ፍላሎት የሚያንተከትከው  እና ሥሜት የሚንጠው ፣ሠከን ብሎ የማያሥበውና ከጥበብ የራቀው ወጣት  ሁላ ፣ ይህንን ሥብእናን ዝቅ የማድረግ ተግባር ያለሃፍረት ለመፈጸም ወደኋላ እንደማይል ዛሬም እያሥተዋልን ነው።
       “ወዳጄ ዋናው ‘ሳቢው ‘(ገንዘቡ ነው) ህፃኑን ወዶ ሽንቱን ፣ቅዘኑን እና ንፋጡን ወይም ንፍጦን ጠልቶ እንዴት ይሆናል??   ‘ወደሽ ነው ገባጢት !?’አሉ ወይዘሮዋ። ” የሚል የማያመዛዝን  ወጣት ጥቂት ነው አይባልም።
     ነገሩን ሥናሥተውለው ፣27 ዓመት ሙሉ ከጥበብ ከራቀች እና በቋንቋና በሤራ ፖለቲካ ከምትናጥ  ሀገር ውሥጥ ካለ ወጣት የበዛ  የሞራል ልዕልና እንዴት ይጠበቃል ??????
        እርግጥም  “በጠመንጃ አፈሙዝ ታግዘው ፣በጉልበት የመንግሥትን ሥልጣን የያዙት እና እነሱ የፈጠሯቸው የጎሣ ፖለቲከኞች ፣ በዘፈቀደ  ህዝብን እያሥተዳደሩ  ና ቅንጣት ያህል  የሞራል ልዕልና ሣይኖራቸው ፣ከዚህ ጥበብን እንዳያገኝ በቋንቋ ካጠሩት ወጣት የሞራል ልዕልና  መጠበቅ የዋኸነት  ነው። “
         እናም ፣ምድሪቱ ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፣ለፋሲካ ዶሮ መግዣ ለማግኘት     የሌለው ወዳለው ተጠግቶ ቢሽቆጠቆጥ፣ቢያሸረግድ ፣ የማይታይ ምናባዊ  ጭራውን ቢቆላ፣ ምን ያሥገርማል??? ጭራ ቆይው በዛ እንጂ ፣ላለው አሸርጋጁ ደመቀ እንጂ፣ ጭራ  መቁላት እኮ ትላንት የነበረ ፣ወደፊትም የሚኖር የማናሥቀረው ነዋሪ እውነት ነው።
   ዛሬ፣ዛሬ ግን ጭራ መቁላት ኢ-ምክንያታዊም እየሆነ ነው። ያለአንዳች ተጨባጭ ጥቅም ፣በቀቢፀ  ተስፋ ብቻ ፣ በገደል አፋፍ ላይ ቆመው ለሚጣሩ ፣ ፖለቲከኞች ጭራ መቁላት ፣የራሥ ሃሳብ አልባነት ነው።  ሰበቡም ከጥበብ ርቆ 27 ዓመት ሙሉ በድንቁርና መኖሩ ነው።(ሁሉም የኢትዮጵያ ምድር የእኔ ነው።የሚል ሃሳብ 27 ዓመት ሙሉ አልተነገረም።ዛሬ ነው አዲሶቹ የሀገራችን መሪዎች የተናገሩት። )
       በኢትዮጵያችን  ላለው(ሥልጣን ወይም ገንዘብ ) ከሚቆላው እኩል  ፣ከሥልጣን ሥር፣ሥር እየተከተለ የሚያሸረግድና ያለአንዳች ተጨባጭ ማሥረጃ  ውዳሴውን የሚያንበለብልና ጥላቸውንም በዛው ልክ የሚዘረግፍ ጥቂት አይባልም። በዚች ሀገር  “አካብዴ ና አጋኔ ” የትየለሌ ናቸው ።በሚገርም ሁኔታ በሥሜት እየተናጡ፣ የሚያወሩት የማይረባ ወግ ሁሉ ፣ ምክንያታዊነት ፣የሌለው ነው። የየለአንዳች ተጨባጭ ማሥረጃ……”እንዴ የእርሷ በጎነት እኮ ከቅድሥት ማርያም በላይ ነው።” የሚሉ።”የእርሱ ርህራሄ ከክርሥቶሥ ይሥተካከላል ። ” ብሎ የሚመሥከር “አርጋጅ !” ነው የሚባለው።ምሥክርነቱም ከተጠቃሚነት የመነጨ በመሆኑ   ” ውሻ በበላበት”  ያሰኘዋል።…።”
      ውሻ በበላበት መጮሁ እንደውሻ ካሰብ ነው መልካም ተግባር ነው።ምክንያቱም ውሻ አያርሥም ፣አይዘራም ፣አጭዶና ወቅቶ እህልን አዘጋጅቶ አይበላም። አድኖ ገነጣጥሎ የመብላት ባህሪን ፈጣሪ አልሰጠውምና ታማኝ የሰው ልጅ   ሎሌነቱ አያሥደንቅም።ለሰው ግን ይኽ አይሰራም።እናም ይሄ ማሽርገድ ዛሬ ኢትዮጵያዊው ሰው ቢበቃው መልካም ነው።
      የበላን እዛው ያብላላው እንጂ ፣  በነውር ከተገኘ ጥቅም ነጭ ድህነታችን ይሻለናል።
ዞሮ ዞሮ ሞት ላይቀር ይህንን ቅንጭብ የተሳተፈበትን፣የፍርፋሪ ገበታ ለምን ለመቋደሥ እንመኛለን??ይቅርብን።ንፁህ ህሊና እና መልካም እንቅልፋችን ይሻለናል።
     እነዛ ሀብትና ሥልጣን የሚያጓጓቸው፣ የሚሸረገድላቸው ጥቂቶችሥ ለእኔ ሰይሆን_ሄዳችሁ ለፈጣሪ ስገዱ ብለው ፣ለመመለሥ ለምን ተሳናቸው?ህሊና የሚባል ሥለሌላቸው አይደለምን??
መቼም ይሄ ተረት ዘላለማዊ እንዲሆን ፈልገው አይመሥለኝም።
      ይህን ከንቱነትን የሚያስቀረው ሁለተኛው ሃሳቤ” አልጫ ፍቅር ” አውዳሚ ነው። ይሰኛል።”
     ፍቅር ማለት የራሥን ህይወት ፣ ለሌላው አሳልፎ መስጠት ነው። እውነተኛ ፍቅር ፣እርጅናን አያውቅም።”  ከሚለው ጋራ የሚቃረን ነው። ” ጨው አልጫ ቢሆን ሰው ምግቡን በምን ያጣፍጣል? ” እንዲሉ ነው ነገሩ።
   በዓለም  አልጫ ፍቅር ነው፣የሞላው። እውነቱኛውን ፣እስከሞት የሚዘልቀውን ፍቅር እምብዛም አናገኘውም።
    ይህ ፍቅርበቅዲስ መፅሐፍ  ውስጥ ፣ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በፃፈው ደብዳቤ በምዕራፍ ፩፫(13 የሀገራችሁን ቁጥር ለማወቅ” በየኔታ ” መማር ለነበረባችሁ የተተረጎመ) ላይ  በቅጡ የተነተነው  ፍቅር  ነው ፤ ይህ ፍቅር።
     ይሁን እንጂ በዚህ ፍቅር ዓለም አትዳኝም።  እጅግ የበዛው ሰው፣ ራሥ ወዳድ እና ሥግብግብ ነው። ሆኖም ደግ ፣በጎ አድራጊና ለጋሥ ለመሆን ሲጥርና በአልጫ ፍቅር ውሥጥ ሲዳክር ይሥተዋላል።
   ባይገርማችሁ ጥቂት የማይባል ሰው ፣  እርሱ መንግሥተ ሰማያትን ወርሶ ሌሎች ወደ ሢኦል ሲወረወሩ ለማየት ያሰፈሰፈ ነው። የተቀደሰው መፀሐፉፍ ግን እንዲህ አይልም።ክርስቶስ ኢየሱስም ፃድቃንን ፍለጋ እንዳልመጣ ተናግሯል። በእኛ በፍጡራኑ ፣የተገረፈውም ፣የተንጓጠጠውም ፣የተሰቀለውም፣ የተሰቃየውም ፣የሞቱውም ፣የተቀበረውም ፣በሦሥተኛው ቀን መቃብርን ፈንቅሎ ፣የእኛን ትዕንሣኤ ያወጀውም ፣ ለእኛ ለሐጢያተኞች ነው።።
     ይሁን እንጂ ፣ የዛሬ ሰው ለደካማው ከመፀለይና በተቻለው ሁሉ ከመርዳት ይልቅ ሥለራሱ ሥኬት ብቻ ነው ሲጨነቅ የሚስተዋለው።
      ሰው፣ ለራሱ ሥኬት አብዝቶ  ይጨነቅ እንጂ ፣ወደደም ጠላም፣  ለአንዱ ውድቀት ሰበቡ በተጣመመ መንገድ ስኬታማ የሆነ ሌላው ሰው ነው።
     በዘረፋ የከበረ ባለሥልጣን እና ተባብሮት ሀብታም የሆነው፣ ተምሮ ሥራ ሥላጣ በየመንገዱ በሚከላወሰው ወጣት መማረር እና  “አይ ይሄ የማይረባ ትውልድ ! “ማለት ይገባዋልን??  ለዚህ ትውልድ ብልሽት እኳ ፣ ያለፈው እና በማለፍ አፋፍ ላይ ያለው ትውልድ  የበኩሉን አሥተዋፆ አበርክቷል።ሌላ ፣ሌላውን ና በየጊዜው ከትርምስ የማይወጣውን የፖለቲካ ሰበብ ትተን፣ የያንዳችንን የኑሮ ትስስርን ሥናሥተውል የሚያሳፍር ነው።
  ይገርማል፣   በመሸታ ንግድ፣ የከበረ ፣በጠጪው ውድቀት ከተቺዎች ጋር ተደምሮ በእርሱ ገንዘብ  የከበረበትን ደበኛው የሆነውን የመጠጥ ልክፍተኛ ቢያማ አያስገርምምን? ።
      በጫት ና በሺሼ ንግድ የከበረች ና የከበረ ፣በሱሰኛው ውድቀት ከተቺዎች ጋር ተሰልፋ ና ተሰልፎ፣ ወይም በሱስ ካልተጠመዱት እና በኑሯቸው ስኬታማ ከሆኑት ጋር አፍ ለአፍ ገጥማ ና ገጥሞ “የሱሰኛው ህይወት የማይረባ እና ከቆሙት በታች ከሞቱት የማይተናነስ ነው።”ብትል ና ቢል  ህሊና ያላቸውና የሚያሥተውሉ “ሆቸው ጉድ?!”በማለት ተገርመው አያባሩምን???
     ግን፣ግን፣ዓለም በእንደዚህ አይነት እርስ በእርሱ በሚጣረስ ቀለበት ውስጥ እየተሽከረከረች በየቀኑ መጓዞን   አታባራም።
     ይህ የህይወት  ሽክርክሪት ባያባራም፣ ለመበስበስም ትልና ምሥጥ አስፈላጊ መሆናቸውን አንዘንጋ።ዓለም እንዲህ ናት።
       እኛ ተራ ሞቾች በእንዲህ ዓይነት አስገራሚ ዓለም እየኖርን በሌላው ላይ ለመሣቅ ወይም “ጎሽ የታባቱ !!ዋጋውን አገኘ !”ለማለት ባንቸኩል ጥሩ ነው።”አትፍረድ ይፈረድብሃል” የተባለው በዋዛ አይደለምና!!። ( ከሞተ በኋላ ለሚያረጋግጠው እውነት ፤ቀድሞ የሚፈርድ ሰው፣አይረባም።ከመፍረድ ይልቅ በፅድቅ በመኖር ለወድምና ለእህት በመፀለይ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩም መንገድ በማሳየት መትጋት ያሥፈልጋል።
    እውነት ፣እውነት እላችኋላሁ የሚመፃደቅ ሰው በመንግስተ ሰማይ ቦታ የለውም።
         ደግሜም እውነት፣እውነት እላችኋለሁ፣ በዚህች ምድር ላይ የበዛው ፍቅር “አልጫ ፍቅር ” ነው።….እስቲ በማስተዋል ተመልከቱ ሌሎች ” ሰናይ ፍቅሮችን”በቃና ፣በኢቲቪ፣በኢቢኤስ ፡እንዲሁም በኢትዮጵያ ፊልሞች፤ በየሲኒማ ቤቱ ፣ ሰው እያየ የሚያለቅሰው ይህንን እውነተኛ ፍቅር በማጣቱ አይደለምን???
       በአብዛኛው የኪነጥበብ ሥራዎች ውስጥ የሚንፀባረቀው የደራሲዎችና የፊልም ፀሐፊዎች ተረት ተረት እና የከረረ የፍቅር ና የጥላቻ ሃሳብ እኮ ነው፣ ተመልካቹን የሚያስለቅሰው።
     –ብዙዎቹ ፊልሞች ድህነትን በመፀየፍ የተቀናጣ ህይወትና የሌለን ቪላና ምግብ በማሳየት የሚያስጎመጁን ናቸው። 90 ፐርሰንቱ  መላው ዜጋ ፣ ደሃና የደሃ ደሃ መሆኑን መዘንጋት ግን አልነበረባቸውም። የመላው ዜጋን ህይወትና  ኑሮውን በመፈተሽ ወደለውጥ የማያመጣ  ኪነት ፣ ከእግር በታች ነው። —
      ምናባዊውና ህልመኛ ድርስት ወይም የፊልም ፅሑፍ ፣ተመልካቹን ፣ተስፈኛና በህልም ዓለም ነዋሪ እንዲሆን ይገፋፋዋል።
      ያለበትን ሁኔታና የነባራዊውን ዓለም እውነት እንዲገነዘብ አያደርገውም።
በፊልሙ ወይም በድራማው ከምናየው ሰው የባሰ ጨካኝ ሰው ሆኖ ሳለ እንኳን ጨካኝነቱን የማያምን ሥንት ሰው ባለበት ማህበረሰብ  የራሡን ማንነት የማታሳይ ኪነት ከእግር በታች ናት።
      እናም ፣ ከዚህ እውነት ተነስቼ፣ በዚች ሀገር የነገሠውን ማሸርገድና አልጫ ፍቅር ለመቀነሥ “የባህል አብዮት”  ያስፈልጋል።…
      ዜጎች ሰው መሆናቸውን እንዲያውቁና በዕውቀትና በጥበብ እንዲጎለብቱ ፤ የሀገርን ታሪክ ና ፣ባህል  እንዲሁም መልካሞቹን እሴቶቻችንን አውቆው ፣  በኢትዮጵያዊነታቸው እንዲኮሩ ለማሥቻል የባህል አብዮት እጅግ አሥፈላጊ ነው።

2 Comments

  1. This Clown Philosophy doctor PM Abiy and team Lemma are not fit to lead Ethiopia. Philosophy majors are usually into religion , Public admistrators , writing or foreign relations not politics.

  2. Cost of residences are going through the roof. People do anything , say anything and please anyone just to have a roof over their heads.Nowadats the love for a place to live is greater than anyother love people have.

Comments are closed.

Previous Story

በአማራ ህዝብ ላይ የተደነቀሩ ከፀጥታ ጋ የተያያዙ ችግሮችና መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ሃሳቦች – ከመሰረት ተስፉ

Next Story

“ዘረኝነት” በፊዚክሱ ቤተ-ሙከራ ሲመረመር – ከበ.ከ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop