April 27, 2019
16 mins read

“ዘረኝነት” በፊዚክሱ ቤተ-ሙከራ ሲመረመር – ከበ.ከ

በህዋ ላይ ጠንካራ የስበት ተፅዕኖ (strong gravitational effects)ያለው ጥልቅ ቀዳዳ ወይም ጉድጓድ አለ። ይህ ቀዳዳ ትልቁንም ትንሹንም ቁስአካል፣ ቅንጣት ኤሌክትሮማግኔቲክ ፍንጣቂዎችን እንዲሁም የብርሃን ጨረሮችን (light)ሳይቀር ውጦ የሚያስቀር ነው። በዚህ ሽንቁር አጠገብ ያለፈ ሁል ከመዋጥ አይተርፍም። ጥቁር ቀዳዳ (Black Hole – BH) የተባለው ይህ አስፈሪ ሽንቁር ብርሃን አልባ ጥልቅ ጨለማ ነው።

በሃገራችን ኢትዮጵያውም ከጊዜ ወዲህ የመሳብ ተፅዕኖ ያለውና ስቦ እውስጥ የሚከት ጉድጓድ ተከስቷል። ይህ ጉድጓድዘረኝነት” ሲባል እሱም እንደ (Black Hole – BH)ብርሃን አልባ ነው። የዘረኝነቱ ጉድጓድ መቆፈር ከጀመረ ምናልባት ሃምሳ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ቅሉ ጉድጓዱ በሠፊው መታየት ከጀመረ ሰላሳ ዓመታት ሊጠጉት ጥቂት ቀርቷል። እነዚህ አስፈሪ ጉድጓዶች በሰው ልጅ የተፈጥሮ ዓይኖች እየታዩ ነው። እነዚህ አገራችን ውስጥ የሚታዩት ሁለቱ የዘረኝነት ጥቁር ጉድጓዶች አንደኛው በኃይማኖት አክራሪነት ስም የተቆፈረ (x1) ሲሆን ሌላኛው በብሄር ጭቆና ስም (z1) የተቆፈረ ጉድጓድ ነው። አነስተኛው ጉድጓድ (x1) ግድግዳው በንቀትና እልህ ” ጭቃ የተለሰነ ሲሆን ትልቁ ጉድጓድ (z1) ግድግዳው በሃሰት ትርክት፣ በቀል፣ ሤራ፣ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ጥላቻ” የተለሰነ ነው። ሁለቱም ጉድጓዶች ለጊዜው ዝምድና ያላቸው ቢመስሉም የኋላ ኋላ (z1) ጊዜአዊ ወዳጁንና አጋሩን (x1) ይውጣል።

የሁለቱም ጉድጓዶች (x1 and Z1) ዋነኛው የስበት ኃይል ዘረኝነት” ነው። BH – ማንኛውንም ጠቃሚ እሴቶች(positive value) እንደውሚውጥ ሁሉ – ዘረኝነትም መልካም የሆኑትን ሁሉ ይውጣል። ዘረኝነት የኔየኛ” ያበዛል። ግሳንግሶችንና ቆሻሾችን ሳይቀር የሚውጠው – BH – በዋጠ ቁጥር ሆድቃው እንደሚሰፋ ሁሉ (BH continues to grow by absorving additional matters) ዘረኝነትም መልካም እሴቶችን፣ አብሮነትን፣ ጓደኛምነትን፣ ትዳርን፣ ፍቅርን፣ ባህላዊ ትስስረን፣ ወዘተ፣ በዋጠ ቁጥር እየገዘፈና እያስፈራ ይታያል።

የሰው ልጅ ፍላጎት በደስታ መኖር ነው። የሰው ልጅ በጎ ነገሮችን በዓይኑ ተመልክቶ ይረካል። ዓይናችን በርካታ ዓይነት ቀለሞችን ይመለከታል። ቀይ (red)ብርቱካንማ (orange) ቢጫ (yellow) አረንጓዴ (green) ሠማያዊ (blue)፣ ወዘተ፣ እያልን ቀለሞችን ለያይተን እናያለን። ዓይኖቻችን እውስጡ ባለው ረቂቅ የብርሃን ተርጓሚ አላካት እየተረዱ(electromagnetic radiation in the visible spectrum) ቀለማትን ይመዘግባሉ። ወደ ዓዕምሯችን የሚሠርጹት የፖለቲካ ጽንሰ ሃሳቦችም ቀለማት አላቸው። እንደ እይታዎቻችን ይለያዩ እንጂ ሠብዓዊ መብት” አረንጓዴ(green)፣ ዴሞክራሲ” ቢጫ (yellow)፣ ነጻነት” ደግሞ ቀይ (red) ሊመስልይችላል። ቀለሞች ትርጉም እንደሚሰጡን ሁሉ ጽንሠሃሳቦችም ሲተገበሩ እንደ ልዩ ልዩ ቀለማት ፈክተው ይታያሉ። እነዚህን ጽንሠሃሳቦች እውን እንዲሆኑ ነው የሰው ልጅ የሚታገለው። ዘረኝነት የነዚህ ቀለማት ጠር ነው። ዘረኝነት ጨለማ በመሆኑ ደስታ ፈጣሪ ቀለማትን ያጠፋል። ዘረኝነትን የተሞላ ዓዕምሮ ሳይንሳዊ የሆኑትን የፖለቲካ ጽንሠሃሳብ ቀለማትን ለማየት ከመጣር ይልቅ ጊዜውን በክፋት ላይ ያውላል።

ዘረኝነት” አልሚና ቀና ሃሳቦችን ስቦ የመዋጥ ኃይል አለው። ዘረኝነት” በቃል ኪዳንና ነጻነት ስም (promise and freedom) ምሎና ተገዝቶ ሲያበቃ ብዙዎችን ያሳስታል። ዘረኝነት – ስምን፣ ቋንቋን፣ አለባበስን፣ አመጋገብን፣ ቅርሳቅርስን፣ ፀጉር አበጣጠርን፣ አጋጌጥን፣ አቋቋምን፣ የብሄሩ ልዩ መገለጫ” አድርጎ በማስደመም ብዙዎችን ያሞኛል። የዜግነት መብትየሚለው መልካም ጽንሰ ሃሳብ በሰዎች ንቃተ ኅሊና ውስጥ ተገቢውን ሥፍራ እንዳይዝ የዘረኝነቱ የስበት ኃይል – ሰበባ ሰበብ ፈጥሮ የዋሆችን ያማልላል። መሠረታዊ ፍላጎቱ ያልተሟላለት ግለሰብ አንድም ለስደት እንግልትና ውርደት” አልያምለዘረኝነቱ” ፖለቲካ ሰለባ ይሆናል። ስደትም ዘረኝነትም ነፍሰ በላ ጉድጓዶች ናቸው። የምድራችን ስበት አንድን ቁሳካል 9.8ሜትር በሰከንድ የመሳብ ኃይል (gravitational force) አለው። የዘረኝነቱ ጉድጓዶች (x1 and Z1) ደግሞ አንድን ሳይንሳዊ ሃሳብ አጣሞና አወላግዶ ወደ ውስጣቸው ለመሳብ የሚያስችል ከምድር ስበት እጥፍ የሆነ ኃይል አላቸው።

አንድ ብረት የስበት ኃይሏ ትልቅ በሆነው ምድራችን ላይ 100 ኪሎ ግራም ቢመዝን – የስበት ኃይሏ አነስተኛ በሆነው ጨረቃ ላይ ደግሞ 16.5 ኪሎ ግራም ነው። የብረቱ ይዘቱ፣ ቅርጹ (ንብረቱ) (mass of an object) እንዲሁም በስበት ወደ ታች የመጎተቱ ጊዜ (acceleration of gravity) – የሁለቱ ብዜት ውጤት ነው ክብደቱን (weight) የሚወስነው። የአንድ ነገር ውጭያዊ ክፍል (surface) ሠፊ ሲሆን ስበትን ተቋቁሞ በዓየር ላይ የመንሳፈፍ እድሉ ትልቅ መሆኑን ሳይንስ ያስረዳናል። ከላይ ከፎቅ ላይ ከተጣለ – ቆርኬ – ይልቅ – ወረቀት – የመንሳፈፍ እድሏ ሠፊ ነው። (the greater the surcace area the greater the air resistence) በዘረኝነት የተለወሱ ሃሳቦች ሠፊ አይደሉም። ጽንሠሃሳብ ደግሞ ሠፊ ነች። ሠፊ ያደረጋት በእውቀት ምርምር ተፈልጋ የመገኘቷ ምስጢር ነው። ከላይ ከሰማይ የተወረወረችልንን ፍትህወደ ዘረኝነቱ ጉድጓድ ተስባ ገብታ ምርኮኛ” እንዳትሆን ሌላ ጠንካራ የስበት ኃይል መፈጠር አለበት። ይኼኛው የስበት ኃይል ንቃተኅሊና (consciousness) ይባላል። ንቃተኅሊና አንድን ነገር በቅጡ መረዳት (quality of awareness)እንዲሁም ልምድን ያካበተ ችሎታ (ability of experiance) መጨበጥ – ከሁሉም በላይ ደግሞ ንቁነትን(wakefulness) መልበስ ማለት ነው። ፍትህ” በአዋቂዎችና በደጋጎች እጅ ላይ ከተራራ ይልቅ ትከብዳለች። ፍትህበዘረኞችና በክፉዎች እጅ ላይ እንደ ቁም ነገር አትታይም።

ያሁኒቷን ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ስንመረምር በዘረኝነትና በንቃተኅሊና (እውቀትመሃከል ቅራኔና ትግል እንዳለ እንገነዘባለን። እውቀት – “ፍትህ ይስፈን” ስትል ዘረኝነት – “መሬቱ የኔ ነው” ትላለች። እውቀት – ምጣኔ ኃብቱን ለማሳደግ ስትጥር – ዘረኝነት– ቤት እያፈረሰች ዜጎችን እጎዳና አውጥታ ትጥላለች። በእውቀትና በዘረኝነት መካከል ያለው ትግል በድል እንዲጠናቀቅ ንድፈሃሳቦች” የስበት ኃይሏ ትልቅ በሆነው ንቃተኅሊና ውስጥ እንዲጣበቁ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለብን። ሰዎችን – ደግሞ ደጋግሞ ሃቅንና እውነታን (truth and reality) እንዲረዱ በማድረግ እንዲሁም ትዕግስትን እንዲላበሱ በመርዳት ዘረኝነትን መቋቋም ይቻላል። ሥራ የለህም – ለምን አትሰደድም” – ወይም – “ሥራህን የነጠቀህ ይሄኛው ብሄር ነው” – ለሚሉት መጋኛ ሃሳቦች ማምከኛው – “ችግር የለም ሥራን እፈጥራለሁ፣ አልሰደድም፣ ከወገኔም አልጣላም – ከታገሱ ሁሉም ያልፋል” –የሚለው ከንቃተኅሊና የሚፈልቀው ብርቱ መልስ ነው። ክፉ ሃሳብን አለመግዛት ብልህነት ነው። ሁለቱን የዘረኝነት ጥልቅ ጉድጓዶችን ለመሸሽ የሚያስችለው ብልህነት፣ ማስተዋልና ጥበብ የሚጋገሩት ንቃተኅሊና ውስጥ ነው። የሰው ልጅ ንቃተኅሊና ትላልቅ ግብረገቦችንና (moral) ሥነምግባርን (ethics) ዘወትር መልበስ የሚያሻውም ከዘረኝነት የሚወነጨፉ ክፉ ሃሳቦችን መመከት እንዲችል ነው።

ሃገራችን ኢትዮጵያውን እያናወጣት ያለው በኃይማኖት ስምና (x1) በብሄር ጭቆና ስም (z1) የሚቅበዘበዙት ተንኮለኞች ናቸው። የሁሉም ድብቅ ፍላጎት ሥልጣንና ሥልጣንን ተገን አድርጎ መዝረፍ ነው። ሕዝብ ዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብት ጥበቃ፣ የምጣኔ ኃብት እድገት፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ፣ ወዘተ፣ የተባሉትን የፖለቲካ ጽንሰ ሃሳብ ቀለማት ውብ ሆነው እንዲታዩ ለማድረግ ሲታገል ዘረኞች” እነዚህኑ ጽንሠሃሳቦች ወደ ታች ወደ ጥቁሩ ጉድጓድ አስወርውረው ድብቅ ዓላማቸውን ይሰብካሉ። በሁለቱ ጉድጓዶች መሃከል (x1 – z1) ያለው ርቀት (distance) እጅግ አጭር በመሆኑ መልካም ነገሮች ሁሉ በቀላሉ ወደ ጉድጓዶቹ ሊሳቡ ይችላሉ። አንድ ጽንሠሃሳብ” ከአንደኛው ጉድጓድ (x1) ልታመልጥ ስትሞክር ሌላኛው ጉድጓድ(z1) ቀስፎ ይዞ መላወሻ ያሳጣታል። ተንኮለኞች ግብረገብን መስበር፣ ታሪክን ማዛባት፣ ድንቁርናን ማስፋፋት፣ ዝርፊያ፣ ብዝበዛ፣ ሌብነትና አድሎ ይችሉበታል። ዘረኞች ይቅርታ መጠየቅ የማይችሉ እልኸኞች ናቸው።

የሃገራችን ኢትዮጵያ ፈተና ይበልጥ የበረታው ንቃተኅሊና (consciousness) በባዕድ ሃሳቦች ስለተመሰቃቀለች ነው። ቀድሞ ጉልታዊውን ሥርዓት” በማስወገድ ትግል ስም ወጣቱ እርምጃው ተሰናክሎበታል። ዛሬ ደግሞ ዘረኞች ባገኙት ማህበራዊ መገናኛዎች የሚረጩት የሃሰት ትርክት ወጣቱን ግራ አጋብቷል። ዘረኝነቱን የሚያራግቡት ፖለቲከኞች – እራሳቸውንም ጨምረው ተከታዮቻቸውን ወደ ጥልቁ ጉድጓድ ከመክተት ውጭ አንዳች መልካም ነገር አያመጡም። በቋንቋ ስም ሕዝብን አታሎ ማነሳሳት ወይም በኃይማኖት ስም ሌላው ኃይማኖት ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚደረገው ሴራ ትልቅ ጥፋትን ከመፈጸም ውጭ አንዳች ፋይዳ የለውም። ክፉዎች አርቀው ማየት አይችሉም እንጂ ዛሬ የሚያናፍሷት ሃሰት ነገ ራሳቸውን ትበላለች። ነገ የሚፈጠረው የብርቱ ኢትዮጵያውያን አደረጃጀት ዘረኝነትንና ዘረኛን ያስወግዳል። ዘረኞች ይህን ቢያውቁ ኖሮ ዛሬ በእሳት አይጫወቱም ነበር።

ዘረኝነትን የሚያራምዱ ሁሉ ሥራቸው ትክክል አለመሆኑን ቀልባቸው ቢረዳውም እንኳን ከጠማማ ሥራቸው ነቅሎ የሚያወጣቸው አንዲት ብጣቂ እውቀት እንቃተኅሊናቸው ውስጥ እንዳትኖር ኃጢዓት ጠቃሚ ኃይልን (positive energy) ከውስጣቸው አሟጦ አውጥቶ ራሳቸው እቆፈሩት ጥልቁ ጉድጓድ ከቶታል። ዘረኛ ቢማርም አልተማረም፣ ዘረኛ ሥልጣን ላይ ቢወጣም አመድ ይመርጣል፣ ዘረኛ ክፉ ልቡን በከረባት ቢሸፍንም፣ ከአፉ የሚወረወሩት – እናፈናቅለው፣ እናባረው፣ ከቀዬአችን እናስወጣው፣ ቋንቋሽን ካልቻለ ፍችው፣ ኃይማኖትህን ካልተቀበለ አግለው፣ ወዘተ፣ የሚሉት የወረዱ ንግግሮች መልካም ማዕዛን በክለው የአካባቢው ጠረን ያቀረናሉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፣ አሜን።

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop