ቴዎድሮስ ካሳሁንየአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ትርዒት በዲቪዲ ተዘጋጅቶ የፊታችን ቅዳሜ ለሕዝብ እንደሚደርስ ታወቀ

ዝነኛው ድምፃዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም 25 ሺህ ሕዝብ በታደመመበትና በታሪካዊው የአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ትርዒት በዲቪዲ ተዘጋጅቶ የፊታችን ቅዳሜ ለሕዝብ እንደሚደርስ ታወቀ::

ይህ ሲዲ ለገና በዓል ሊቀርብ የነበረ ቢሆንም በአርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬ ጥያቄ መሰረት መራዘሙን ዘ-ሐበሻ ቀደም ሲል መዘገቡ ይታወሳል::

https://youtu.be/_Na9XUN2kfA

ቴዲ ከ16 ዓመታት የሙያ አጋሮቹ አቡጊዳ ባንድ ጋር ያቀረበው የሙዚቃ ኮንሰርት ከድምፅና ሙዚቃ ቅንብሩ እስከ መድረክ ቁጥጥሩ የተሳካና በኮንሰርቱ የታደሙትን ያረካና የተዋጣለት ቅንጅት የነበረው ታረካዊ ትርዒት እንደነበር ሲነገር የቆየ ሲሆን ይህን ታሪካዊ ዝግጅት በቦታው ተገኝተው ላልተመለከቱ፣ በዕለቱም ታድመው ለታሪክ ማስታወሻነት በከፍተኛ የድምፅና የምስል ጥራት የተቀረፀውንና የተቀነባበረውን ቪዲዮ ለሚፈልጉ ሁሉ፤ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው ታሪካዊ ዲቪዲ ከፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን ጀምሮ በገበያ ላይ እንደሚውል አሳታሚዎቹ ከላኩት መረጃ ተረድተናል::

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጃኪ ጎሲ በሳዑዲ ላሉ ወገኖቻችን መታሰቢያ ነጠላ ዜማ ለቀቀ
Share