በሸዋ ሮቢት ከተማ ጎማ እየተቃጠለ ለሰአታት መንገድ ተዘግቶ ዋለ

የዛሬው መንገድ መዝጋትና ጎማ ማቃጠል ደግሞ ለየት ያለ ነበር፡፡ ከስፍራው እንደደረሰን መረጃ በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋ ሮቢት ከተማ አንዲት ሴት በጩቤ ተወግታ ስትሞት አብሯት የነበረው ህፃን ልጇ ደግሞ በመታፈን ህይወቷ አልፎ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች በተገደሉበት ቤት ውስጥ ታፍኖ የነበረ ሌላ ህጻን ልጅ ወደ ህክምና ተወስዶ በተደረገለት እገዛ በጥሩ ጤንነት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

https://www.youtube.com/watch?v=SvwytfrDZTg&t=73s

ይህን ድርጊት በመፈፀመም የተጠረጠረው ግለሰብ አብሯት ይኖር የነበረ ሲሆን ድርጊቱ ከተፈጠረ በኋላ ጠፍቶ ቆይቷል፡፡ በዛሬው እለት ግን ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ እንደተሰማ በርካታ የሸዋ ሮቢት ነዋሪ ግልብጥ ብሎ አደባባይ እንደወጣ ሰምተናል፡፡ የተወሰኑ የከተማው ነዋሪዎች፣ ‘ግለሰቡን ፓሊስ አሳልፎ ይስጠን እና እንግደለው፣ ወይም በመንጋ እንፍረድበት’ በማለታቸው ከፓሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተዋል። ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን ጥይትም በብዛት ሲተኮስ የነበረ ሲሆን ይህን ተከትሎም ነዋሪዎቹ ጎማ አቃጥለው ለሰአታት መንገድ መዝጋታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲስ አበባ "ለእሪታ ቀን" እንድትዘጋጅ ተጠየቀ! "ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!"
Share