ዶ/ር አብይ አህመድ እና ለማ መገርሳ ም ዕራብ ወለጋ ተገኙ

ኦሮሚያን እያስተዳደረ የሚገኘው ኦዴፓ ሊቀመበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ  ከምዕራብ ወለጋ ከማኅበረሰብ አባላት ጋር ተወያዩ። አብዛኛው የም ዕራብ ወለጋ አካባቢ በኦነግ ቁጥጥር ሥር ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል::

https://www.youtube.com/watch?v=Fu1uIyUHtps&t=186s

ሁለቱ መሪዎች በምዕራብ ወለጋ የቄለም ወለጋ ዞን አዋሳኝ ከሆነችው ቤጊ ወረዳ የማህበረሰብ አባላት ጋር በዛሬው ዕለት ሲወያዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ወቅታዊ ጥያቄዎችን አቅርበዋል:: በተለይም ሰላም እና የመሠረተ ልማት እጦት ችግርን እንደዋነኛ የአካባቢው ችግር አድርገው ጥያቄ አቅርበዋል::

” በአካባቢው ለሰላምና ልማት መረጋገጥ የአንድነትን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ይኖረዋል:: ” በማለት ” ችግሮቹን በተቀላጠፈ መልኩ ለመፍታት ነዋሪዎቹ ልማት ተኮር ተራማጅነትን እንዲመርጡ” ማሳሰቢያ የሰጡት ዶ/ር አብይ ወረዳው ያለበትን የመሠረተ ልማት ችግር በማመን የወረዳውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ስለሚያደርገው ጅምር የመስኖ ፕሮጀክትም ማብራሪያ ገለጻአ ሰጥተዋል::

ዶ/ር አብይ አህመድ ከኦሮሚያ የተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ወገኖች ጋር በአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ውይይት ባደረጉበት ወቅት ግጭት ሲፈጠር ለምን ወደ ምእራብ ወለጋ አልሄድክም በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው  “በአካባቢው ችግር ሲከሰት ለምን ወደ ስፍራው አልሄድክም ለሚለው ጥያቄ ላይ በተደጋጋሚ ከለማ ጋር ተወያይተንበታል:: .ከዛ በኋላ እኔ ወደ አካባቢው ያልሄድኩት ለደህንነት አስጊ የሆነ መረጃ ስላለኝ ነው። ህዝብ ከተፈናቀለ ሁለቱም ይመጣሉ፣ ሲመጡም ህዝብ ውስጥ ይገባሉ፣ ህዝቡን ይስማሉ….። ያን ጊዜ ሁለቱንም እዛው እናስቀራቸዋለን (እንገላቸዋለን) ይላሉ። አሁን ጉዳዩ ወደ አካባቢው መሄድ አይደለም::  የሚያሳስበኝ  እኔ ወደ ሌላ ስፍራ ሄጄ #ብሞት #ኦሮሞ አንድ ሆኖ በትግሉ ይቀጥላል፤ እኔ ወለጋ መጥቼ ብሞት ግን በህዝብ መካከል ያለውን አንድነት ሊጎዳ ይችላል። ጉዳዩ #የመስዋትነት ጉዳይ አይደለም። አንድነታችንን ሊጎዳ የሚችል ነገር ነው። “ይህ ህዝብ ግን አንድነታችን በናንተ ምክንያት አይናድም የሚል ከሆነ እኔ ችግር የለብኝም። ነገውኑ ወደ ስፍራው እሄዳለው” ማለታቸው ይታወሳል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ ነኝ: ፋኖ ነኝ | በኢትዮጵያ የኤርትራውያን አፈና ለምን በረከተ | ባህርዳር ሰራዊቱ እርስበስ መዋጋት ጀመረ |

ዛሬ ዶ/ር አብይ አህመድ እና ለማ መገርሳ የሄዱባቸው አካባቢዎች ከወራት በፊት ኦነግ ሸኔ መዋቅሩን ተቆጣጥሮት በነበረውና መከላከያ ገብቶ ባረጋገው ሥፍራ ነው::

ስለሆነም ነዋሪዎቹ የተከሰተውን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የውይይት ባሕልን እንዲያዳብሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Previous Story

በጎንደር ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ | መከላከያ ገባ 

Next Story

አቶ አርከበ እቁባይ ለሕወሓት መልቀቂያ  አስገቡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው

Latest from ዜና

ልዕልት ሂሩት ደስታ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

ከአንሙት ስዩም እስካሁን በኖርኩባቸው አመታት የተረዳሁትና የገባኝ አንድ ነገር አለ፡፡ በዝህብ ላይ መጥፎ ስራ የሰሩትን ወንጀለኞች ለፍርድና ለቅጣት የማቅረብና የማስፈረድ ልምድ ያለንን ያህል፤ መልካም ለሰሩት ግለሰቦች ግን ተመጣጣኝ የሆነ የስማቸው

Share