በነአብዲ ኢሌ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ተፈቀደ

ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው የቀረበብኝ ክስ ድራማና ውሸት ነው ያሉት አብዲ ኢሌ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረብይ:: በዛሬው የችሎት ውሎ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በሶማሌ ክልል የቀድሞ ርእሰ መስተዳድር  አብዲ መሀመድ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ያቀረበውን አቤቱታ ተቀበለ።

https://www.youtube.com/watch?v=bsEiZlueJBA

ክስ ከተመሰረተባቸው 47 ግለሰቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የተነበበላቸው አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር፣ ራህማ መሀመድ ሀይቤ፣ አብዱራዛቅ ሰሀኔ ኢልሚና ፈርሃን ጣሂር በርከሌ ናቸው። ሌሎቹ በቱርክ ሃገር እንደጠፉና የሚፈለግጉም እንዳሉ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ዘግቦ ነበር::

በዛሬው ችሎት ጉሌድ ኦበል ዳውድ እና ወርሰሜ ሼህ አብዲ የፍርድ ቤቱን የስራ ቋንቋ ባለማወቃቸው ምክንያት እስካሁን ድረስ ዐቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ እንዲረዱት አለመደረጉ የተገለጸ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ዛሬ በዋለው ችሎት የሶማሊኛ ቋንቋ አስተርጓሚ በቋሚነት እንደሚመደብ አዟል::

ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው ምስክሮች ከተከሳሾች መዝገብ ጋር በማያያዝ በምስክሮች ላይ ሞራላዊ፣ አካላዊ እና የደህንነት ስጋት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ለማድረግ እና ህጉም የሚፈቅድ መሆኑን በማስረዳት የተከሳሾች ማንነትና አድራሻ እንዳይገለፅ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን መቀበልይ ተሰምቷል:: የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ተለዋጭ ቀጦር ለየካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም  ሰጥቷል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጸረ ሙስና የዝቋላ ብረታ ብረት ፋብሪካን አስተዳደር በምክር ማለፉ አነጋጋሪ ሆኗል
Share