ጢስ አባይ ፏፏቴ ጉብኝት ላይ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል አንድ ህይወቱ አለፈ

https://www.youtube.com/watch?v=tUdOX1BEMNc&t=105s

በጢስ አባይ ፏፏቴ ጉብኝት ላይ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል አንድ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ወደፏፏቴው ተንሸራቶ ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አሰማሀኝ አስረስ ገለሱ::ባህር ዳር ከሚገኙ የተለያዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ40 በላይ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ጭስ አባይ ፏፏቴ አምርተው ጉብኝት እያደረጉ እንደነበር አቶ አሰማሀኝ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ከረፋዱ 4 ሰዓት ፏፏቴው አጠገብ ፎቶ ሲነሱ ከጥንቃቄ ጉድለት አንድ ተማሪ ተንሸራቶ ወደ ፏፏቴው ውስጥ ሲገባ ሌላኛው ተማሪ ወደ ውኃው የገባውን ልጅ ለማዳን ወደ ፏፏቴው መግባቱ ተነግሯል፡፡

በዚህ ሂደት ቀድሞ ወደ ፏፏቴው የገባው ዮናታል አዲሱ የተባለ የ3ኛ ክፍል የኢትዮ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ተማሪ ህይወቱ አልፏል፡፡ ሁለተኛውን ተማሪ ግን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ተረባርበው አትርፈውታል፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: አንድሬስ ኢንዬሽታ - የዘመኑ የእግር ኳስ ቴክኒሽያን
Share