የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን በጎንደር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት እያየን ዝም አንልም አለ

የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን በጎንደር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት እያየን ዝም አንልም አለ::

https://www.youtube.com/watch?v=tUdOX1BEMNc&t=105s

“በተደጋጋሚ በጎንደር ላይ እየታየ ያለው ትንኮሳ ለእህት ወንድሞቻችን ቤት አልባ መሆንና መፈናቀል እንዲሁም መሞት ከነገ ዛሬ ይሻለዋል ብንልም መሻሻልን ማየት አልቻልንም።” ያለው ኮሚኒከሽኑ “ገዳይ ሲሸሽ ሟች ይገሰግሳል እንዲሉ ተስፋ የሌላቸው፥ ነገን አርቀው መመልከት የተሳናቸው ህሊና ቢሶች የእብድ ተግባራቸውንና እንስሳዊ ባህሪያቸውን አጠናክረው በመቀጠል ቤቶች እና በግብራቸው እነሱን የማይመስሉትን እንስሳት እያቃጠሉ ይገኛሉ።ይህን ድርጊት መንግስት አስቸኳይና የማያዳግም መፍትሔ ካልሰጠውና በወንጀለኞች ላይ  ህጋዊ እርምጃ ካልወሰደ እነዚህን አውሬዎች ከገቡበት ገብተን ልካቸውን ለማሳየት የምንገደድ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን።” ሲል አስጠንቅቋል::

በአሁኑ ሰዓትም የክልሉ የጸጥታ ኃይል ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚያደንቅ የገለጸው ኮምዩኒኬሽንኑ ሁሉም ማህበረሰብ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ወንጀለኞችን አሳልፎ እንዲሰጥ አሳስቧል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሊተገበሩ የማይችሉና ህወሓት በጦርነቱ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለዉ አመላካች መሆናቸውን ምሁራን አመለከቱ
Share