January 26, 2019
3 mins read

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በዛሬው ዕለት በናዝሬት ከተማ የማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን መክፈቱን አስታውቋል

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በዛሬው ዕለት በናዝሬት ከተማ የማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን መክፈቱን አስታውቋል::

https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s

አብን  በተጨማሪም ከሰሞኑ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተከሰተው ግጭት ምክንያት የአካል ጉዳት በደረሰባቸውና ሕይወታቸውን ባጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ገልጾ መግለጫ አውጥቷል:: “በድሬድዋ ከተማ አስተዳደር የረጅም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄ ሆነው ከቆዩ ጉዳዮች መካከል የዜጎችን እኩልነት የሚነፍገው አፓርታይድ 40-40-20 ቀመር አንዱ ነው፡፡ ይኼ ቀመር የዜጎችን ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በጣሰና በዜጎች መካከል እኩልነትን በነፈገ፣ አግላይና ነጣይ በሆነ መንገድ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ የተነሳም በከተማዋ የሚኖሩ ዜጎችን በተለይም አማራውን ለኢፍትኃዊ ተጠቃሚነትና ለሥራ አጥነት እየዳረገ ይገኛል፡፡” ያለው አብን “በዜጎች መካከል መበላለጥን የሚፈጥረው የአፓርታይድ ቀመር እንዲቀር በተደጋጋሚ ጊዜ የድሬድዋ ሕዝብ በተለያዩ መድረኮች ጥያቄ ቢያቀርብም መፍትሔ ከሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ ሊገኝ ባለመቻሉ ሕዝባችን ለግጭቶችና ደኅንነት ስጋቶች በመዳረግ ላይ ይገኛል፡፡” ብሏል:: 

ስለሆነም አብን ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና ዜጎችም ሁሉን አቀፍ ጥያቄዎቻቸውን በሰከነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመንግሥት እንዲያቀርቡ እየጠየቀ፤ መንግሥት የድሬዳዋ ሕዝብ ላቀረበው የፍትኅና እኩልነት ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ፤ 40-40-20 የተሰኘ የአፓርታይድ አሰራርን በማስወገድ ዜጎች በእኩልነትና በፍትኃዊነት የሚስተናገዱበትን አሰራር እንዲዘረጋ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በድጋሜ በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ኃዘን እንገልፃለን፡፡” ብሏል::

ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድሬስ በድሬደዋ በተከሰተው ግጭት ዙሪያ መግለጫ የሰጠው ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ አብን ብቻ ነው::

Go toTop