በኢትዮጵያ የኦሮሚኛ የሙዚቃ ውስጥ ትልቅ ሥፍራ ያለው አፍራን ቀሎ የሙዚቃ ቡድን በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ ታሪካዊ የተባለውን የሙዚቃ ኮንሰርቱን አቀረበ::
https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s
በስደት ቆይቶ ወደ ሃገሩ ከሁለት ሳምንት በፊት የተመለሰው ይኸው የሙዚቃ ቡድን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም የሙዚቃ ኮንሰርቱን ሲያቀርብ በርካታ አድናቂዎቻቸው እና የተለያዩ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ሰዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል:: የአፍራን ቀሎ የሙዚቃ ቡድን በሃገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ሰምተናል::
አፍራን ቀሎ ባንድ በ1960ዎቹ ውስጥ በድሬደዋ ከተማ እንደተመሰረተ የተጻፉ ታሪኮች ያስረዳሉ::