ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ኡመርና የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አህምድ ሽዴ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል::
https://www.youtube.com/watch?v=p8iBU5RCUVc&t=50s
ዶ/ር አብይ ከሙስጠፋ ኡመር እና አህመድ ሺዴ ጋር ከስብሰባው በፊት የተነሱትን ፎቶ አድርጎ ባሰራጨው ዘገባው ዉይይቱም የተኮረው በሶማሌ ክልል ልማትና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሲሄን ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም የክልሉን ልማት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አቅጣጫ ሰጥተዋል ሲል ጽህፈት ቤቱ ጠቅሷል::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች በበኩላቸው ስብሰባው እንዳልተጠናቀቀና እስከነገ ድረስ እንደሚቀጥል ገልጸውልናል:: በዚህ ስብሰባ ላይ 11 አባላት ያሉት የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን ስብሰባው እንዳለቀ መረጃ እንደሚያቀብሉን ቃል ገብተውልናል:: እንደደረሰን መረጃውን ለዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች እናደርሳለን::