በኢትዮጵያ የሚገኘው የናይጄሪያ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ዜጎቹ ማስጠንቀቅያ ሰጠ

በአፍሪካ ህብረትና በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቋሚ መልእክተኛና የናይጄሪያ አምባሳደር ቃል አቀባዩ ካስተን ኦጆሞ ዛሬ በአቡጃ በሰጡት መግለጫ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ናይጄሪያዊያን ከ3 ሺህ ዶላር በላይ

https://www.youtube.com/watch?v=G6LalCqO72M
የሚበልጥ ገንዘብና ውድ ጌጣጌጦችን እንዳይዙ አሳስበዋል፡፡ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡትም በኢትዮጵያ ህግ አስከባሪዎች ንብረታቸው እንዳይወረስባቸው በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመግለጫቸው ‹‹ከ3 ሺህ ዶላር የሚበልጥ የውጭ ምንዛሬ ወይንም የዚህ ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ የምትይዙ ከሆነ ልክ ኢትዮጵያ እንደገባችሁ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ማስታወቅ አለባችሁ፡፡›› ማለታቸውን ዛሬ የናይጄሪያ ጋዜጦች ዘግበውት ተመልክተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን በፍርድ ቤት ረታች
Share