ለቀናት ታግተው የተለቀቁት የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ‹‹እኔ ፖለቲካ አይመለከተኝም፣ ያገቱኝ ሰዎችም የተሳሳቱ ይመስለኛል›› አሉ

ለቀናት ታግተው የተለቀቁት የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቱ ዶ/ር ደላሳ ቡልቻ ‹‹እኔ ፖለቲካ አይመለከተኝም፣ ያገቱኝ ሰዎችም የተሳሳቱ ይመስለኛል›› አሉ::
https://www.youtube.com/watch?v=G6LalCqO72M

ዛሬ በአዲስ አበባ ለንባብ ከበቃው ሸገር ታይምስ መፅሄት ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት ዶ/ር ደላሳ ቡልቻ በታገቱበት ወቅት ምንም የደረሰባቸው አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጥቃት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ይሁንና የማያውቁት ነገር ስለገጠማቸው እንደከበዳቸው አስረድተዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ወታደር ብሆን የገጠመኝ ምንም ላይመስለኝ ይችላል፡፡ እኛ ከቢሮ ውጭ ምንም አናውቅም፡፡›› ብለዋል፡፡ የሙያ ሰው እንጂ ፖለቲከኛ አለመሆናቸውን ገልፀውም የታገቱበት ምክንያት ግራ እንደሆነባቸው ጠቁመዋል፡፡ በቃለምልልሱ ‹‹እኔ ስለተማሪ ሽሮና ጤንነት እንጂ ስለፖለቲካ የማይመለከተኝ ሰው ነኝ፡፡›› ያሉት ዶ/ር ደላሳ ጨምረውም ‹‹ስለተማሪው ደህንነት እንዲሁም ስለትምህርት ጥራት ቀኑን ሙሉ የሚያወራና እሱንም ማድረስ የማይችል ሰውን እንዲህ ማድረግ አይገባም፡፡ ከእንደዚህ አይነት ሰውም ምንም አታገኝም፡፡ በዚህ ጉዳይ እነሱም የተሳሳቱ ይመስለኛል›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ዶክተሩ ለቀናት ታግተው የተለቀቁ ሲሆን ለእገታው ሃላፊነቱን የወሰደ አካል እስካሁን የለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢዜማ መሪ ሆነው ስለተመረጡ እንኳን ደስ ያለዎት! (አንዱዓለም አራጌ )

1 Comment

Comments are closed.

Share