አብን መከላከያ ሰራዊቱ ይቅርታ እንዲጠይቅ ጠየቀ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ ዋና ፅህፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚህ መግለጫው ሰሞኑን

https://www.youtube.com/watch?v=G6LalCqO72M
በተፈጠረው ጉዳይ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፣ የመከላከያ ሚኒስትሯና ኤታማዦር ሹሙ ማብራሪያ እንዲሰጡት ጠይቋል፡፡ ጨምሮም ‹‹ከሰሞኑ ገንዳኋና ኮኪትን ጨምሮ ራሳቸውን የቅማንት ኮሚቴ ነን ብለው የሚጠሩ የትሕነግ/ሕወኃት አሽከሮችን ውንብድና ወቅት መከላከያ ሰራዊቱ ከሕግ ውጭ ወደ ፀጥታ ማስከበር በመግባት ላደረሰው ግድያ ይቅርታ እንዲጠይቅና ለተጎጂ ቤተሰቦችም ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን፡፡›› ብሏል፡፡

ለግድያው ትዕዛዝ ያስተላለፉ፣ በወንጀሉ የተሳተፉና ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሞከሩ የመከላከያ አመራሮችና አባላት ለሕግ እንዲቀርቡም ጥሪ ያቀረበው አብን፣ መከላከያ ሰራዊቱ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ መዋቅሮች ሳይጠይቁት ወደ መደበኛ የፀጥታ ማስከበር ስምሪት እንዳይገባ አሳስቧል፡፡

መከላከያ የአገር ዳር ድንበርን የመጠበቅ ዋነኛ ተልዕኮው ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እንጂ በፍፁም የግል ድርጅት ጠባቂ መሆን እንደሌለበት በጽኑ እምነት እንዳለው ድርጅቱ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎቹ በአስቸኳይ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ መላውን አማራ በማንቀሳቀስ ተፈጥሯዊ መብቱን እንዲያስከብር የሚያስተባብር መሆኑን እሳውቋል፡፡

በሌላ ዜና:
በሰሜንና በምዕራብ ጎንደር ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ ከ500 በላይ ታጣቂዎች ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ዛሬ ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
Share