በምዕራብ ጎንደር የገጠር ቀበሌዎች የቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል:

በምዕራብ ጎንደር የገጠር ቀበሌዎች የቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል:: በመተማ ወረዳ ጉባይ በተባለ ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን ሰምተናል::
https://www.youtube.com/watch?v=G6LalCqO72M

በተያያዘ መረጃ ጎንደርን ከመተማ የሚያገናኘው መንገድ ዛሬ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። መንገዱ በግጭቱ ወቅት በድንጋይ እና በአፈር ተዘጋግቶ ነበር::
በምዕራብ ጎንደር ሁለት ሹፌሮች በታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ ትንናት በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል;; በተያያዘ መረጃም በምዕራብ ጎንደር ትናንት በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 12 ሰዎች ተጎድተው ወደ ቋራ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጌትሽ ማሞ በሚኒሶታ አስገራሚ ብቃቱን መድረክ ላይ ያሳየበት ሙዚቃ - 'የጠላሽ ይጠላ"
Share