መከላከያው በሌሎች ክልሎች ያሳየውን ትዕግስት በጎንደርም መድገም እንደነብበረበት የአማራ ክልል ባለስልጣናት ተናገሩ

https://www.youtube.com/watch?v=ncwpPfdrV3E&t=991s
መከላከያው በሌሎች ክልሎች ያሳየውን ትዕግስት በጎንደርም መድገም እንደነብበረበት የአማራ ክልል ባለስልጣናት ተናገሩ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር የተደረገ ቆይታ - Anchor Media

2 Comments

  1. በትግራይ እየታየ ያለው ህግን እየጣሱ ህገ-መንገስቱ ይከበርልን አንደምታው እኔ ስፈልግ አከብረዋለሁ፣ ሳልፈልግ ደግሞ እነደዋለሁ አይነት ነው፡፡ ህገመንግስቱ ይከበር ብሎ የወጣው ሰልፈኛ የትኛው የህገመንግስቱ ድንጋጌ እንደተጣሰ፣ በየትና በማን እንደተፈጸመ አልነገሩንም–በቅርቡ የድንበር ኮሚሽን አዋጅን አስመልክቶ ከሚያነሱት ውጭ፡፡ ህገ-መንግስቱ ተንዷል የምትሉን አካላት በምትኖሩበት ክልል ህዝቡ ምን ያህል በህገ-መንግስቱ ድንጋጌ ልክ መብታችሁ ተከብሮ እየኖራችሁ እንዳልሆነ ለማወቅ ነጋሪም አያስፈልገንም፡፡
    የፌዴራሉን መንግስት ጦር ወዴት ነው የምትሄደው፣ በቅድሚያ እኛን አናግረን ብሎ መንገድ በህጻናት ማዘጋት ህጋዊነት ምን ድረስ ነው፤ መጠየቅ መብት ሊሆን ይችላል ጥያቄውን እያቀረቡ መከራከር እንጂ በየትኛውም መመዘኛ በሞብ የወታደሩን እንቅስቃሴ መግታት በዛ ሰሞን መሳሪያ አንግቶ ቤተ-መንግስት ካልገባሁ ከለው ዋልጌ ጦር በምን ይለያል፡፡
    ይሁንና ወታደሩ ከስሜት ነጻ በመሆን የወሰደው እርምጃ የአጋቾቹን ሳይሆን የወታደሩን አሸናፊነት፣ የሴረኞችን ክሽፈት የመለክታል፡፡
    በሌላ በኩል በአማራ ክልል በእንቅስቃሴ ላይ የነበሩ የግንባታ ተሸከርካሪዎች ህዝቡ ጥርጣሬ አለን እና ፍተሸ ይደረግልን በማለቱ የተነሳ የሰው ህወት መጥፋቱ ያሳፍራል፣ ያሳዝናልም፡፡ ለመሆኑ የፌዴራሉ መንግስት ወታደር ክልሉ ሳይጠራው ከየት ተገኘ፤ የግለሰቦችን ንብረት/ሱር ኮንስትራክሽን/ በፌዴራል መንግስት ነው እንዴ የሚጠበቀው፡፡ የሱር ኮንስትራክሽን ንብረት የሆኑትን ተሸከርካሪዎች ሲጓዙ ክልሉ ደህንነታቸውን መጠበቅ ፍቃደኛ አልሆንም ብሎ ነው ወይንስ ክልሉ ስለማይመጥናቸውና በፌዴራል መታጀብ ያለባቸው ልዩ ስለሆኑ ነው፡፡

  2. በምእራብ ጎንደር በደረሰው እልቂት የተለኣዩ መግለጫዎች እየወጡ ቢሆንም የተረጋገጠውን ለማወቅ የኣጣሪ ኮሚቴውን ሪፖርት ጠብቆ መስማት ይበጃል።
    ኣንድ የተረጋገጠ ነገር ቢኖር ያካባቢው ህዝብ በሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት ላይ ያለው ጥርጣሬ ነው።የህዝብን ኣመኔታ ያጣን እንቅስቃሴ መንግስት በቀዳሚነት ማጣራት እና ህጋዊ ያልሆነ ድርጊት ካለ ለሚመለከተው የፍርድ ቤት ኣካል ማቅረብ ግዴታው ነው።
    ከላይ ከተጠቀሰው ድርጅት ባለቤት የሆነው ኤፈርት ድርጅት በሚያስተዳድራቸው ሌሎች ድርጅቶችም ውስጥ ኢፍታዊነት አና ጸረ ህግ ተግባራት በሰፊው በህዝቡ ዘንድ ሲነሳ በተደጋጋሚ ይሰማል።
    ስለዚህ መንግስት የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅትን መነሻ በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ በሰፊው የሚነሳውን ጥርጣሬ ለማጥራት በ ኤፌርት ያሉ ድርጅቶችን ከመነሻቸው ጀምሮ ያለውን ሂደታቸውን ተኣማኝነት እና ገለልተኛ በሆኑ ባለሞያዎች ኦዲት ኣስደርጎ ጥፋትም ካለ ልማት ለህብረሰሰቡ እንዲያቀርብ ቢያረግ የህዝቡን ጥርጣሬ ሊያረጋግጥ ወይም ሊያስወግድ ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።
    እንኩዋን የህዝብ የኣንድ ግለሰብም ጥርጣሬ መናቅ ኣይገባውምና።

Comments are closed.

Share