“ፌዴራል መንግሥት” ሆይ! አማራ ሲያልቅልህ ወታደሮችህን የዒላማ ተኩስ በምን ልታሰለጥን ይሆን?

ወልደማርያም ዘገዬ

ተደጋግማ የምትተረት አንዲት ያማርኛ ተረት አለች፡፡ ፈርዶባት እኔም አሁን ልጠቀምባት ነው፡፡

“የምታሸንፈውን ምታ” ቢሉት “ወደ ሚስቱ ሮጠ” ይባላል፡፡

የዶ/ር ዐቢይ “ፌዴራል” መንግሥት መከላከያ ጦር ትግራይ ውስጥ “እኛስ ለምን ይቅርብን?” ባሉ የመንደር ኩታራዎች ሳይቀር በየሥፍራው እየታገተና በልመናና በልምምጥ ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት ያን እልህና ቁጭት ለመወጣት በሚመስል አኳኋን በለውጡ ኃይል የሚታዘዘው “ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት” ዐማራውን እየጨፈጨፈ እንደሚገኝ በሚዲያ እየተከታተልን ነው፡፡ ይህ ዕንቆቅልሽ በፍትህ አስተካካዩ ፈጣሪ አማካኝነት በቅርብ እንደሚፈታ ባምንም ለጊዜው ግን እጅግ ያናድዳል፤ እንደሰውና እንደዜጋም ያሳዝናል፡፡ ከዚህ አኳያ በሁሉም ሥፍራዎች የሚገደሉና የሚሰቃዩ የወያኔና መሰል ተባባሪዎቹ የጥቃት ሰለባዎች መኖራቸው አይቀርምና የሚመለከታቸው አካላት ከዚህ የበለጠ ጉዳት ሳይደርስ በአግባቡ ቢንቀሳቀሱ መልካም ነው፡፡

ግፍ ሲበዛ ምፅዓትን ትጠራለች፡፡ የምፅዓት ቀን ስትመጣ ወንድና ሴቱ ይለያል፡፡ ያኔ የደፈረሰው ይጠራል፡፡ አሁን ግን ጸሎት ብቻ!! ውድ ኢትዮጵያውያን በርትታችሁ ጸልዩ፡፡ ክፉኛ የመጨለሙ ምሥጢር የንጋቱ ብሥራት ነውና በአንድ በኩል ደስ ይበለን፡፡ ጭንቅ ወንዶችን እንደምትወልድ እኔ በበኩሌ በደምብ አውቃለሁ፡፡ ምሥጋና ለአስጨናቂዎቻችንና ወፍ ከሰማይ የሚያወርዱ ወንዶች ሊወለዱ እናቶች ምጥ ላይ እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡ ይብላኝ ለአስጨናቂዎች እንጂ እንደተቸገረ የኖረ ሕዝብ የለም፤ ዓለም የሎሚ ተራ ተራ መድረክ ናት፡፡ ከባዱ መውለድ እንጂ መግደል አይደለም፡፡ የፊት ኪንታትን አጠፋሁ ብለህ እንደምታባዛው ሁሉ ዐማራን አጠፋን ብለው ብዙ የለፉና የደከሙ በተወሰነ ደረጃም የተሳካላቸው ወገኖችም ዐማራን በእልህና በቁጭት ብዛት ሳያከሩት የቀሩ አይመስለኝም፡፡ እነዚህ ዕኩያን ወገኖች ደግሞ ሂሳባቸውን የሚያወራርዱበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ችግራችን ሂሳብ ሲያወራርዱ መኖርን ባህላችን አደረግንና የውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ፈሊጥ ምርኮኞች መሆናችን ነው፡፡

አንዲት ተረት ልጨምር፡፡ “አጥሩን ካልናቁ ባለቤቱን አይነቀንቁ” …. የለም … አዟዟርኩት መሰለኝ፡፡ “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” – እንደዚህ ነው የሚባለው፡፡ ለነገሩ ባለቤቱም አጥሩም መነቅነቃቸው አልቀረም፡፡ ባለቤትስ ሲኖር አይደል አጥር የሚኖረው? አሁንና ዛሬ እኮ አጥርም ባለቤትም የሉም፡፡ “ሚስትህ ወንድ ወለደች?” ቢለው “ማንን ወንድ ብላ!” አለው አሉ፡፡ ወይ ብአዴን – ማነው – አዴፓ!

በአሁኑ ወቅት ዐማራ ባለቤት የሌለው፣ አለሁህ ባይ ያጣ፣ እንደጠፍ አህያ ማንም የሚጭነውና አልፎ ተርፎም በአሁኑ “የነፃነት ዘመን” ሳይቀር የተኩስ መለማመጃ ተደርጎ ዘሩ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ እየተደረገ ያለ አሳዛኝ ሕዝብ ነው፡፡ ማወቅ ያለባቸው ሁሉ ይወቁት – ይህን በዐማራ ላይ የሚፈጸም ግፍ የሚመለከታቸው ሁሉ በዕጥፍ ድርብ ይከፍሉታል፡፡ እያስፈራራሁ እንዳይመስላችሁ፡፡ የ“ብድር በምድር”ን ትርጉም ጠንቅቄ ስለማውቅ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዩክሬን ወረራ (በአንድ ኢትዮጵያዊ ዕይታ) - አንዱ ዓለም ተፈራ 

ዐማራው ባለቤት የሌለው ሆን ተብሎ ነው፡፡ ብአዴን የዐማራ ወኪል አልነበረም፡፡ በምናውቀው ምክንያት፡፡ አሁን አዴፓ የተባለውም “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል” ዓይነት ነው፡፡ ለምን ቢባል – ውስጡን ስለሚያውቁት እንኳንስ ዐማራን ራሱንም መከላከል የማይችል በሙስና የበሰበሰና በዘረኝነት ልክፍት ተተብትቦ በሥውር ለወያኔ ባደሩ ጀሌዎች እንደፈለገው እንዳይራመድ የተቀየደ፣ ገና ጠርቶ ያልጠራና ብዙ መፈተሽ ያለበት ድርጅት ነው፡፡ ወያኔዎች አሁን ድረስ እንደምርቅ የተሰገሰጉበት የዘረኝነቱ ጣጣ ይቅርና “የበላን ያብላላዋል” እንዲሉ ብዙዎቹ አባላት በፈጸሙት የሙስና ወንጀል ገና ለገና እንጠየቅ ይሆናል ከሚል ፍራቻ ተረጋግተውና አቅል ገዝተው ከልባቸው እየሠሩ አይመስሉኝም – ለሀገርና ለወገን ማሰብ የሚቻለው ደግሞ ከራስ ወዳድነትና ከሥጋት ነጻ ሲሆኑ ነው፤ እየፈሩና እየቸሩ ሕዝብን በቅንነትና በፍቅር ማገልገል አይታሰብም፤ ደረትን ነፍቶ ሕዝብን በቀናነትና በፍትህ ማገልገል የሚቻለው አንገትን ከሚያስደፋ ነውረኝነትና ከጥልፍልፍ የሙስና ድርጊት ነፃ ሆኖ በመገኘት ነው፡፡ ይህን ዕድል ደግሞ ብዙዎቹ የሚያገኙት አይመስልም፡፡ (የእስካሁኖቹን ሊናቁ የማይገባቸው ለውጦች ግን ሳላደንቅና ሳላመሰግንም ማለፍ አልፈልግም፤ ትልቅ መስዋዕትነት የተከፈለባቸው ናቸውና የማጣጥለው ነገር የለኝም)፡፡ ….

አዴፓ ተሰሚነት ቢኖረው ኖሮ ትናንት ከትግራይ በአማላጅና በልመና – ከታንክና ከመድፍ ሳይቀር እያስወረዱ ጎረምሦች የተጫወቱበት መከላከያ ዛሬ ጎንደር ላይ ሕዝብን እንዲረፈርፍ ባልታዘዘ ነበር፡፡ ከእንግዲህ ዐማራው ራሱን መከላከል የሚያስችል የራሱን ድርጅት ማቋቋም ይኖርበታል፡፡ እንዲህ ሲባልም ዐማራው ዘረኛ ይሁን ለማለት አይደለም፡፡ የተኩስ መለማመጃ ሆኖ ላለመቅረትና ራስን ለማስከበር በእግረ መንገድም ትውልድን ለማስቀጠል የቀረው ብቸኛ አማራጭ ሁነኛ ድርጅት አሁኑኑ መመሥረት ነው፡፡ ስለሆነም – ዐማራ ሆይ! ከዕንቅልፍህ ንቃ፡፡ ይሄ የጎንደር፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የጎጃም ዐማራ … የሚሉት ጠላቶች የፈጠሩልህ የልዩነት ሽኩቻ ደግሞ ያስጨርስሃል እንጂ በጭራሽ አይጠቅምም፡፡ ዐማራ ዐማራ ነው፡፡ ባያድለን እንጂ ዐማራም ትግሬ ነበረ፤ ትግሬም ዐማራ ነበረ፤ ኦሮሞም ዐማራ ነበረ፤ ዐማራም ኦሮሞ ነበረ፡፡ ሰው በሰውቱ ብቻ፣ ሰው በዜግነቱ ብቻ ቢተዛዘንና ቢፈቃቀር ይበቃው ነበር፡፡ አንድን መጥፎ ነገር ዘመን ያመጣዋል፤ ይወስደዋልም፡፡ ይህን ቆሻሻ ዘመን ፈጣሪ ወደ ታሪክ ማኅደር እስኪያስገባው ብዙ እየተሰቃየን ነን፡፡

ባለሦስት ዐይኖች በጉጉት የሚጠብቁት ወርቃማው ዘመን እስካልመጣ ድረስ እንዳለፈው የወያኔና እንደ አሁኑ አዲስ የለውጥ ሂደት ሁኔታዎች ከሆነ ዐማራ በዐማራነቱ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ቦታ የለውም፡፡ በቃላት ጨዋታ የመደለልን ትርጉምና ውጤት አየነው፡፡ ሁሉም ባዶና የቃላት ኳኳታ ብቻ ነው፡፡ … ለነገሩ ልፋ ሲለኝ እንጂ ንግርት አይቀርም፡፡ የሚከተሉት በጣም ጥቂት እውነታዎች ለምሬቴ አስተዋፅዖ አላቸው፡፡ ሆድ ያስብሳሉ፡፡ ያስጨንቃሉም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን አግቶ ወታደርን ከታንክ በማውረድ መዘባበቻ እንዲሆን ለማድረግ ትግሬ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ሰርቆና ዘርፎ፣ አሥሮና ገድሎ፣ አኮላሽቶና ወንድን በወንድ ሴትንም በሴት አስደፍሮ፣ የሀገርን ሀብትና ንብረት መዝብሮና ወደ ውጭ አጓጉዞ መቀሌ ላይም ሆነ በሌሎች ሥፍራዎች  በሰላም መኖር የሚቻለው ትግሬ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡ ለ27 ዓመታት ኢትዮጵያን እንደጥገት ቦጥቡጦ፣ ሀገርን በገዛ ፈቃድ ወደብ አሳጥቶ፣ የሀገርን ዳር ድንበር ለባዕዳን ሸጦና ለውጦ፣ ሕዝብን ኮድኩዶ፣ የሰላም ዕንቅልፍ መለጠጥ የሚቻለው ትግሬ ከሆኑ ብቻ ነው፡፡ ስማኝ ልንገርህ እንግዲያውስ ወንድማለም…. የሽቁጥቁጡ ዐማራ … የድንጉጡ ዐማራ ነገርማ አይነሣ! እንኳንስ ወደሀብትና ሥልጣን ሊጠጋ በሕይወት መኖሩ ራሱ እያስቀናቸው – እያናደዳቸው … ኧረ ተወኝ ልጄ፡፡ የምትገርም ዘመን ናት ግን፡፡

ያዝ እንግዲህ! ዐማራን ከየመሥሪያ ቤቱ እየለቀምክ ከሥራና ከኃላፊነት ማገድ በነሱም ምትክ የራስን የዘር ሐረግ ካለምንም መሥፈርት ከየሥርቻው እየሰበሰቡ ከአግባብ ውጪ መተካት የሚቻለው “ቀን የሰጠው” ትግሬ ወይም ኦሮሞ ሲሆኑ ብቻ ነው – ምኑ ሊቀርብኝ ታፍኜ እቀራለሁ? ከ40 እና 50 ዓመት የስደት ፖለቲካ በኋላ እንደ ጠ/ሚንስትሩ አባባል በልመናና ህግን በመለወጥ ወደ ሀገር እንዲገቡ ተደርጎ በሀገር ሀብትና በዜጎች ደም መቀለድ የሚቻለው ኦሮሞ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡ ሁለት ሺህ ያልሞላ ወያኔ የተቀላቀለበት ጦር ተይዞ በመቶ ሽዎች የሚገመትን የ“ፌዴራል” ጦር ማንቀጥቀጥ የሚቻለው ኦሮሞ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ እንሰማው የነበረውን ዓይነት ኢትዮጵያዊ አይሲስና አልቃኢዳ በዴሞክራቶቹ መሪዎቻችን ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ በገዛ መንግሥታችን ተፈጥሮልን በአንድ ዋና ከተማ ውስጥ በተሰየሙ ሁለት ተቃራኒ አዋጊዎች ሕዝባችን ሊያልቅ የሚችለው ኦሮሞ ተቃዋሚ ስትሆን ብቻ ነው – ዋሸሁ እንዴ! ዐማራ ቢሆን ይሄኔ ዓለም አልፋለች፡፡ ዐማራማ “ይህን የተጫነ ነገር በሌላ ነገር እጠረጥረዋለሁና ለደኅንነቴና ለንብረቴ ዋስትና ሲባል መኪናው ይፈተሸልኝ” በማለቱ ብቻ በጥይት እየተቆላ ነው – ሌላ መቀናጣት ሳያሻ በዚህች ምክንያት ብቻ በገዛ ቀየው እየታረደ ነው፡፡ ስህተት ከተናገርኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ፡፡ “ና ብሎ ዕዳ” እንዲሉ ሆኖ በስደት አገር በሰላም ይኖር የነበረን ጎምቱ ሰውዬ ጠርቶና አጠገብ አስቀምጦ በሹመት በማስጎምጀት “ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ቢሮየ አናት ላይ ለምን ፀሐይ እንድትወጣልኝ አልተደረገም!” በሚል ሰበብ አስባብ መንግሥትን “ሱሪ ማስወቀለቅ” የሚቻለው፣ “ለአመራሮቼ ዘመናዊ አውቶሞቢልና ዘመናዊ ቪላ ካልተሰጠ ሠራዊቴ ራሱን እንዲከላከል ትዕዛዝ ማስተላለፌ ነው፤ ያን ሁሉ የስደት ትግል ያደረግነው እኮ ታጋዮቼ ተንቀባርረው እንዲኖሩ ነው – በዚያም ተስማምተን ነው ወደ ሀገር የገባነው ” የሚል ፌዘኛ የፖለቲካ ቻርሊ ቻፕሊን ተፈጥሮ በዋና ከተማ በመንግሥት ገንዘብ እየተጠወሩ ፌዴራልን ማስፈራራት የሚቻለው ኦሮሞ ሲኮን ብቻ ነው፡፡ ወይ ትያትር! ምን ዓይነት ትያትር ናት ይቺ ይቺኛዋ ደግሞ! ብለው ብለው ወያኔን ሊያስመሰግኑን እኮ ነው፡፡ “አላዋቂ ሣሚ …” እንዳይሆን ጊዜ የለንምና በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገር ይከናወን… አለዚያ ከራሴ ፀጉር ይነቀል እያንዳንድሽ ከጎንሽ ታገኛታለሽ … you will get your price from your side (አንተ ደግሞ ለእንግሊዝኛ  አዲስ ነህ ልበል? ‹ ዋጋህን ከጎንህ ታገኛታለህ!› ለማለት እኮ ነው፡፡ ‹እያነቡ እስክስታ› … አለ ያ ቁም ነገረኛ ቴዲ ….  ሰሞኑን ግን ጠፋብኝሳ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወንጀል እና ህግ ፣ እውነት እና ውሸት በብሄረሰቦች ነፃነት ዘመን (ታሪኩ አባዳማ)

 

ሁሉም ያልፋል፡፡ ይህም ያልፋል፡፡ ትዝብቱ ግን አያልፍም፡፡ የሚያርግ እንጂ የሚጠፋ ነገር የለም፡፡ የሚቀመጥ ነገር ሁሉ ቦታ ቢለውጥ እንጂ ከነወለዱ መገኘቱ አይቀርም፡፡ ያኔ ማቄን ጨርቄን አይሠራም፡፡ የኛ ቀን ዛሬ ብቻ ናት – ለመሞትም ለመዳንም ያለችን ቀን ዛሬ ብቻ! “እንዲህ ባደርግ ኖሮ”ም ጉንጭ አልፋ ይሆናል – ሊያውም ያን ለማለትም ዕድሉ ከተገኘ፡፡ አይ ዐማሮች – “ምክር የድሃ ነበርሽ – ማን ቢሰማሽ” አሉ?

 

ለማንኛውም እኔ ዐማራ ባልሆንም ዐማራን እየደረሰበት ካለ ተደጋጋሚ መከራና ስቃይ ለመታደግ በሚደረገው ጥረት ሁሉ ለመሣተፍ ዝግጁና ፈቃደኛ ነኝና ስለዐማራ ያገባኛል የሚል የትኛውም ወገን ሰውን ከሰው፣ ዘርን ከዘር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ወዘተ. ለማያስበልጥ፣ እኩልነትና ፍትህ ለተሞላበት ኢ-ብረታዊ ትግል ቢጋብዘኝ አድራሻየ mz23602@gmail.com  መሆኑን በታላቅ ደስታም ባይሆን ያለ አንዳች መከፋት በትኅትና እገልጻለሁ፡፡

 

በኦሮሞና በትግራይ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች በወያኔ ሸርና ተንኮል እንዲሁም በመንግሥታችን የላቀ ትግስት ምክንያት እያለቁ የሚገኙ ወገኖቼን ነፍስ ይማር፡፡ እግዚአብሔር ዐማራንና ኢትዮጵያን ይባርክ፤ አሜን፡፡

 

4 Comments

  1. የድሮው ምስኪን አማራ ላይመለስ ሄዷል፣የጊዜ ጉዳይ ይሆናል እንጂ፣ደማችንን በእጥፍ እንመልሳለን።

  2. “የምታሸንፈውን ምታ” ቢሉት “ወደ ሚስቱ ሮጠ” ይባላል፡፡
    Kan dandeessu dhaani jedhnan dhirsi galee niitii dhaane, jedha Oromon.

    ይህን ተረት በራስህ ላይ ነው የተረትከው! የህወሃት/ኢህአደግ ሰራዊት አሁንም በየቦታዉ ህዝብ እየጨፈጨፈ እያለ፣ አሁንም አፍህን የምትጠርገው ግን በኦሮሞ ህዝብና በvanguard ድርጅቱ ላይ ነው። ስለማታዉቀው ነገር ባትቃባጥርስ??

  3. አየ አባጫላ!እውነትም vanguard፤ለምን ቀነካ አፍህ vagabond የሚለውን መጣኙን ስም አትጨምርለትመ? ትንሽ እፈር፡፡ በቆምክበት መጨፈርም ይብቃህ፡፡ ለማደግ ሞክር ማሙሽዬ፡፡ ሕጻናትን ቦምብና መትረየስ አስይዞ በሰው ደም የሚነግድና በታዳጊዎች ሥነ ልቦና የሚጫወት ዕድሜ የማያስተምረው ዘላለም ከአንቀልባ የማይወርድ ቡድን አንተን እንጅ ሰፊውን ኦሮሞ አይወክልም፤ እንደዚያ ማለት ለኦሮሞ ስድብ ነው፡፡ አንተ ግን generically idiot and ignorant ስለሆንክ አዝናለሁ አይገባህም፡፡ በዓላማና ለዓላማ ሆንብሎ ከደነቆረ ‘ሰ
    ው’ ጋር ደግሞ መግባባት ፈጽሞ አይሞከርም፡፡

  4. በፌደራል መንግስት ወታደሮች የሚገደል ያለው አማራ ሳይሆኑ ሃገሪትዋን የደፈሩ ብዛት ያላቸው ድንበር አልፈው የገቡና በየክልሉ ያሉ የሶማሊያ ሃገር ሰላይ ወታደሮች ናቸው :: በብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት የተመሰረተው የኢህአዴግ ፓርቲ አማራን ላለፉት 28+ አመታት የሰላም አየር እንዲተነፍስ አስችሎታል::

Comments are closed.

Share