ከ3 ሚሊዮን ዲያስፖራ በቀን አንድ ዶላር እንያዲዋጣ በዶ/ር አብይ ከየተጠቀው ውስጥ እስካሁን ያዋጣው 2800 ሰዎች ብቻ መሆኑ ተገለጸ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በአሜሪካና አውሮፓ ተጉዘው ከኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ውይይት ዲያስፖራው በቀን $1 እንዲያዋጣ ከጠየቁ ወዲህ ከ3 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ገንዘብ ያዋጡት 2800 ብቻ እንደሆኑ አመለከቱ።

እስካሁን የተገኘውም $507,094 መሆኑን ከማሰባሰቢያው ድረገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁም ተገልጿል::

ዲያስፖራው በድጋሚ አሁንም ይህንን ጥሪ ተቀብሎ በአንድ አንድ ዶላር የማዋጣቱን ተግባር እንዲቀጥል የተጠየቀ ሲሆን በአንጻሩም ዶ/ር አብይ የሾሙት ቦርድም በዋሽንተን ዲሲ ብቻ ስብሰባ አድርጎ ክመበተን ይልቅ በተለያዩ ስቴቶች እየተዟዟረ ሕዝብን የማንቃት ሥራውን እንዲያከናውን ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያና የግንዛቤ መስጪያ ፕሮግራሞችን እንዲዘረጋ ሕዝብ በተለያየ መንገድ እየጠየቀ ነው::

በሌላ በኩል ዶ/ር አብይ ዛሬ “ግዴታየን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ዛሬ በይፋ በተጀመረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የግብር ገቢ ለአገር እድገትና ስልጣኔ ዋነኛ መሰረት እንደሆነ ገልፀው ግብር ከፋዮች ለሀገርና ለወገን ያላቸውን ፍቅር ለማሳየት የግብር አከፋፈል ሀላፊነትና ስነልቦና ማጎልበት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል::

ግብርን የሚያጭበረብሩ ዜጎችን እንደ ብልጥ መመልከት መቆም ያለበት ድርጊት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶችን ልናወግዛቸው ይገባልም yalut dor abye በአግባቡ ግብር የሚከፍሉትን መንግስትንና ልጆቹን እንደሚወድ ዜጋ እንመለከታቸዋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለንግድ ፍቃድ መነገድ፣ ሙስና፣ በግብር ማጭበርበር እና ሌሎች ህገወጥ የሆኑ አካሄዶች የዘርፉ ማነቆዎች መሆናቸውን አንስተው ይህ ሊቆም ይገባልም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር ግብር ለ ኢንቨስትመንት ያለውን አስተዋጽዖ አብራርተዋል፡፡ የንቅናቄው ዐላማ ኢትዮጵያን በ2017 ወደ ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ ያለመ ነው፡፡ ለዚህ ማስፈጸሚያም እስከ 2012 መጨረሻ 2.3 ትሪሊዮን ብር ከግብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን 75 በመቶው ከታክስ ገቢ የሚሰበሰብ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 60 በመቶው መሠረታዊ አግልግሎቶችን ለማስፋፋት ይውላል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዐመታት ከሀገራዊ ምርት አንጻር የታክስ ገቢ ምጣኔ በተከታታይ ቀንሷል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=s58PBvypjSM

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነፃ እና እራሱን የቻለ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ የተደራጀው ግብረ ሀይል ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ

1 Comment

  1. ከዳያስፖራው በቀን አንድ ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶ በነበረው ፕሮጀክት እስካሁን 2800 ሰዎች ብቻ መሳተፋቸውን መንግሥት በመገናኛ ብዙኀን ገልጿል። የዶ/ር ዐቢይ ሐሳብ በውጭ ከሚገኘው ቢያንስ 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ 1 ሚሊዮኑ ይሳተፋል የሚል ነበር። ይህ አልሆነም። ይህን ተከትሎም አንዳንድ የአገር ውስጥ መገናኛ ጣቢያዎች ዳያስፖራውን ለመውቀስ ዳር ዳር ብለዋል። ይሄ ትልቅ ስሕተት ነው። ያለጥናትና ምክክር ሳይደረግበት በጥድፊያ የሚጀመር ነገር ሁሉ ውጤቱ ይህ እንደሚሆን መገመት አስቸጋሪ አይደለም።

    የተሳታፊው ቁጥር የቀነሰበት ምክንያት ዳያስፖራው ለአገር የሚሆን በቀን አንድ ዶላር ሰስቶ ወይም አገሩን ለመርዳት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ እንዳልሆነ ግን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ምክንያቱም በአግባቡ በተቀሰቀሰበትና ከልቡ ባመነበት ጉዳይ ብዙ ሲያደርግ ይታወቃልና። ለቤተዘመዶቹም እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር በዓመት የሚልከው ይኸው ዳያስፖራ መሆኑ መዘንጋት አይኖርበትም። ታዲያ ይህን የሚያደርግ ዳያስፖራ ለtrust fund መዋጮ ያላደረገበት ምክንያት ምንድን ነው? ይህን ማጥናት አስፈላጊ ነው። በምን መንገድ ቢሆን መዋጮውን ለማድረግ ፈቃደኛ ይሆናል? ሐሳቡ ከራሱ ከዳያስፖራው እንዲመጣ የልብ ለልብ ምክክር ማድረግ ያስፈልጋል ማለት ነው። ከዚያ ሁሉም ሰው ዘንድ መድረስ የሚችልና ያልተቋረጠ ቅስቀሳ ያስፈልጋል። ሥራው ውጤታማ እንዲሆን ደግሞ ከሌሎች አገሮች ልምድ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው። ያ ሳይከናወን ወደወቀሳ ከገባን የ trust fund ዱ ዓላማ ከመጀመሪያውም ሌላ ነበር የሚያሰኝ ብቻ ነው የሚሆነው።

Comments are closed.

Share