አቶ ዳውድ ኢብሳ የ ጀነራል ከማል ገልቹ ሹመት ጦርነት ውስጥ እንዳስገባቸው ገለጹ | “ሰራዊታችን ጥቃት አያደርስም እራሱን እንዲከላከል ግን ትዕዛዝ ተሰጥቶቷል” አሉ | በዶ/ር አብይና ለማ የሚመራው. ኦዴፓ ጠንከር ያለ መስጠንቀቂያ ሰጠ

የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ በአዲስ አበባ መግለጫ ኦነግ ወደ ጦርነት የገባው የቀድሞው የኦነግ አመራር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ደህንነት ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው መሆኑን ተናገሩ::

በህጋዊነት በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ተስማምቶ ወደኢትዮጵያ ከገባ አራት ወራት ያስቆጠረው ላለፉት 27 አመታት ከመንግስት ጋር ጦርነት ሲያካሂድ መቆየቱን ያወሱት አቶ ዳውድ አሁን ጦርነት ለማቆም ከስምምነት ላይ እንደተደረሰ አስረድተዋል፡፡

“ኦነግ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ በህጋዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ወደ ሀገር ከገባ 4 ወራት ተቆጥሯል:: በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ለውጥ የመጣው የኦነግ አባላት፣ የኦሮሞ ህዝብ በተለይም ደግሞ ወጣቱ በከፈለው መስዋእትነት ነው ብሎ ያምናል:: ለውጡ ወደ ትክክለኛ ዴሞክራሲ እንዲሸጋገር እና ስልጣን የህዝቡ ሆኖ ህዝቡ በምርጫ ተወካዩን እንዲመርጥ እና ህዝባዊ መንግስት እንዲመሰረትም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ወስዶ እየሰራ ነው:” ያሉት አቶ ዳኡድ “በአሁኑ ወቅት ከመንግስት ጋር የተገባው ስምምነት እየተጣሰ ነው ብለው እንደሚያምኑ አቶ ዳውድ አስረድተዋል። የኦሮምያ ክልል ጀነራል ከማል ገልቹን የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አድርጎ መሾሙ የኦነግ የታጠቀ ሀይል መንግስትን እንዲጠራጠር ማድረጉን” ገልፀዋል።

አቶ ዳውድ ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት በሰላሌ፣ በባሌ፣ በጉጂና በወለጋ ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ ማካሄድ መጀመሩን የገለጹ ሲሆን “ሠራዊታችን ጥቃት አይፈጽምም፤ ራሱን ግን እንዲከላከል ትዕዛዝ ተሰጥቶታል’ ያሉት አቶ ዳኡድ ትናንት ኦዴፓ የጦርነት የመሰለ አዋጅ አውጥቷል በዛሬው ዕለት ከኦነግ ዋና ጽህፈት ቤት ምግብ በመመገብ ላይ የነበሩ አባላቸው ዶክተር ገዳና ሌሎች ተይዘው መወሰዳቸውን አስታውቀዋል።
“ችግሮችን ለመፍታት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፣ የደህንነት ሃላፊው ጄነራል አደም መሐመድ እና የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ጠይባ ሁሴን ባሉበት ያደረግነው ውይይት አልተተገበረም” ሲሉም ቅሬታቸውን ያቀረቡት አቶ ዳኡድ በካምፕ ያለው ሠራዊታቸው የተያዘበት አግባብ የተሃድሶ ሳይሆን የእስር አይነት ያሉት አቶ ዳውድ ይፈቱ ሲሉ ጠይቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደብረ ብርሃን የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ነው

ባለፉት 27 አመታት የመከላከያ ሰራዊት፣ የደህንነት አገልግሎት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልል ፖሊሶች ፓርቲውን ሲያገለግሉ እንደነበር አቶ ዳውድ ጠቁመው ወደአገር ውስጥ ሲመለሱ ከመንግስት ጋር የፀጥታ ሀይሉ ገለልተኛ እንዲሆን የመንግስት እንጂ የፓርቲ እንዳይሆን በሚል መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡ የኦነግ ሰራዊትም በፀጥታ መዋቅር እንዲካተት እና ይህንን የሚስራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ከስምምነት ተደርሶ እንደነበር ያወሱት ሊቀመንበሩ ‹‹በአሁኑ ወቅት ግን ከመንግስት ጋር የተገባው ስምምነት እየተጣሰ ነው፡፡›› ካሉ በኋላ በስልጠና ያሉትን የኦነግ ሰራዊት አባላት በአመራሮቹ እንዳይጎበኙ መደረጉን እንደምሳሌ ጠቅሰዋል፡፡ አቶ ዳውድ በመግለጫቸው ‹‹የመከላከያ ሰራዊት የኦነግ ታጣቂዎች ያሉበት አካባቢ መስፈሩ ግጭት እንዲከስት ምክንያት ሆኗል፡፡

ሰሞኑንም በምእራብ ወለጋ በመከላከያ ሀይል እና በኦነግ ታጣቂዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር›› ብለዋል፡፡ አሁንም ቢሆን በክልሉ ሰላም እንዲኖር ቁርጠኛ አቋም ካለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በቀጣዩ ምርጫ በተቀመጠለት ጊዜ እንዲካሄድም አሳስበዋል፡፡
የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ድርጅታቸው አሁን ወደ ጦርነት የገባው የቀድሞው የኦነግ አመራር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ደህንነት ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው መሆኑን ከገለጹ በኋላ “ለአንድ ሰው ሹመት ይህ ሁሉ ሰው በሞት መቀጣት አለበት ወይ?” ሲሉ የሚጠይቁ አሉ::

ይህ በ እንዲህ እድናለ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ‘በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ቃል የተገባዉ ተንዶ የፓርቲያችን ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ ያሳየዉ ትዕግስት እንደ ፍራቻ’ ተቆጥሯል ሲል ገለጸ::

ኦዴፓ በመግለጫው ‘ሲዘርፉን፣ ሲያስጨንቁን እና ሲያኮላሹን የነበሩ፤ ከስልጣን የተባረሩ፤ ከህዝባችን በዘረፉት ገንዘብ ኦሮሞንና ኦሮሚያን የጦር ሜዳ ለማድረግ የሞት ትግል እያደረጉ ነዉ’ ብሏል።
በተፈጠሩ አለመረጋጋቶች በህዝብ ላይ ደረሰ ያለውን ችግር የዘረዘረው ኦዴፓ፣ በትዕግስት እና በአንድነት ችግሮች ይፈታሉ ብሎ እንደሚያምን፣ ግጭቶች ከቀጠሉ ግን በሀገርና በወገን ላይ ጉዳት እንድሚደርስ አስጠንቅቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕወሓት መንግስት በጣሊያን ተለጣፊ ኮምዩኒቲ (ማህበረሰብ) አቋቋመ * በአውሮፓ ቤተከርስቲያኖችን ለመቆጣጠርም እየሠራ ነው (ልዩ ልዩ አጫጭር ዜናዎች)

መግለጫው አክሎም ‘የውስጥ እና የውጭ የጥፋት ሀይሎች ኦሮሞ ሀገር መምራት አይችልም በማለት በጋር ሴራ ሸርበውብናል :: ኦዴፓ ሰፊዉ የኦሮሞ ህዝብንና ቄሮዎችን ከጎኑ በማሰለፍ… የለዉጡ ጉዞ ለአንድ ሰከንድም ሳይደናቀፍ ወደ ድል ምዕራፍ እንዲሸጋገር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ ማንኛዉንም እርምጃ ለመዉሰድ ወስኗል’ ብሏል::

https://www.youtube.com/watch?v=s58PBvypjSM

Share