አርበኞች ግንቦት 7 በአዲስ አበባ ዋና ዋና አደባባዮች ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሏል

ድርጅቱ ዛሬ በአዲስ አበባ ዋና ዋና አደባባዮች ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሏል፡፡ ቅስቀሳውም የንቅናቄው አመራሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ውይይት የሚያደርጉበት መድረክ መዘጋጀቱን የሚገልፅ ነው፡፡ ከዚህ የመኪና ማስታወቂያ እንደሰማነው ቅዳሜ ህሳስ 13 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ሜክሲኮ በሚገኘው ኤሌክትሪክ ክበብ (መብራት ሀይል አዳራሽ) እንዲሁም እሁድ ታህሳስ 14 ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ ህዝባዊ ስባሰባ ተዘጋጅቷል፡፡ በስብሰባው ላይ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እና አቶ ቸኮል ጌታሁን የሚገኙ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በማስታወቂያ ቅስቀሳው ስለህዝባዊ ውይይቱ አላማ የተገለፀው ‹‹የንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ አዲስ ስለሚመሠረተው የፖለቲካ ፓርቲና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ቀጠሮ ይዘዋል። እርስዎም በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።›› በሚል ነው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=s58PBvypjSM

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢሳት:-ጋምቤላ ክልል በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር ወደቀች።

1 Comment

  1. በአዲስ አበባ በአሁኑ ዘመን አውሮፕላን እና ሄሊኮፕተር ላለው ብዙ ቤቶችን መቀየር ተለምድዋል :: አንድ ወይም ሁለት ተሸከርካሪ ላለው ደግሞ አንድ የመኖሪያ ቤትን መቀየር ተለምድዋል በአዲስ አበባ:: የመኖሪያ ቤትን በተሸከርካሪ እንቀይራለን የሚሉ የሽያጭ አማራጮችም በስፋት የቤቱን መገኛ አድራሻ እና የቤቱን ይዞታ በፎቶ ግራፍ ጭምር አስደግፈው የሚወጡት እኚሁ የፌስቡክ እና ትዊተር ማስታወቂዎች እየተስዋሉ ነው::

Comments are closed.

Share