“የጆሮ ቀለብ ያ’ርገው” የሚባል እውነተኛ ድክረታ! | አቤል ምትኩ (ከአዲስ አበባ)

ካርታ ተጫውተህ ታውቃለህ? ካወቅህ ዲካርት ምን ማለት እንደሆነ ይገባሃል፡፡ ይህን ጨዋታ የማያውቅ ግን የቃሉን ትርጉም ለመረዳት ሊከብደው ይችላል፡፡
የቃሉን ምንጭ ለማወቅ ሞክሬ አልቻልኩም፡፡ ሰው ለመጠየቅም ሆነ መዛግብትን ለመፈተሸ ደግሞ ጊዜ አጣሁ፡፡ ልጄ ከሚሆን አንድ ወጣት ጋር ከደቂቃዎች በፊት ምሣ ስንበላና ቡና ስንጠጣ የነገረኝ አንዱ የድክረታችን ማሣያ ምልክት በጥድፊያ እንድጽፍ አሯሩጦ ቢሮ አስገባኝ፡፡ ለነገሩ በዚህች ርዕስ ለመጻፍ ከከጀልኩ አንድ ሁለት ቀን ሆነኝ፡፡ ስለአንድ ነገር መጻፍ ስፈልግ ያ ነገር በቅንጭላቴ እየተመላለሰ ዕረፍት ይነሣኛል – እንዳመል ሆኖብኝ፡፡

በካርታ ጨዋታ – ኮንከርም ይሁን ሴካ – መሬት የምትጥለውን ጨምሮ ሦስት ካርዶች ብቻ በእጅህ ከቀሩ ዲካርት ገባህ ይባላል – በደንቡ መሠረት እንደማትጨርስ ለመጠቆም ነው፡፡ ምክንያቱም የምትጥለውን ጥለህ የሚቀርህ የካርታ(የካርድ) ብዛት ሁለት ብቻ ይሆንና ከሦስት ጀምሮ በሚደረግ መቀናጆ ካርታህን ደርድረህ መጨረስና ማሸነፍ አትችልም፡፡ ለማሸነፍ ያለህ ብቸኛ ዕድል ያንተኑ ጨምሮ ካርዶችህን በወረዱ ካርዶች ላይ በመሰካት ብቻ ነው፡፡

ዲካርት ከዚህ ከፍ ሲል ከጠቀስኩት የካርድ ጨዋታ ይነሳል፡፡ ወደ አማርኛ የብዜትና የዕርባታ ጠባይ ይገባና ደግሞ “ደከረተ፣ ደክርቶ፣ ይደከርት ዘንድ፣ …” እያለ በኢ-መደበኛ መልኩ – በአራድኛው አገባብ – ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለእንደመለስ ዜናዊ ያለ እንደልቡ የሀገር መሪ ግን “ትምክህተኞችና ጠባቦች በዚች ሀገር እስካሉ ድረስ መደክረታችን አይቀርም” ቢል ክልክል የለውም፡፡ መለስ እንኳን ለአንደበቱ ለግፈኛ ተግባሩም አንድም ምድራዊ ልጓም አልነበረውም፡፡ እንደሱ ያሻውን አድርጎ የሞተ የሀገር መሪ ብዙም አላውቅም፡፡
ደከረተ ከካርታው ጨዋታ ውጪ ለሌሎች አገባባዊ ትርጓሜዎችም ይውላል፡፡ አንድ ሰው ሥራውን ሲያጣና ገቢው ሲቀንስ – በዚያም ሰበብ በኢኮኖሚ ረገድ ሌላ ጊዜ ከሚያደርጋቸው ነገሮች ሲታቀብ “እገሌ ደክርቷል” ይባላል፡፡ በጊዜያዊ የገንዘብ ዕጦትም አንዱ ጓደኛህ “አቦ ዛሬ ደክርቻለሁ፣ ጋብዘኝ” ቢልህ አንተም እንደርሱ ካልደከረትክና ካልሰሰትክ ትጋብዘው ይሆናል፡፡ ገንዘብ ማጣት – “በጠብሽ መወገር”ም – ከድክረታዎች አንዱ መሆኑ ነው፡፡

ድክረታ ብዙ ገጽታዎች አሉት፡፡ አንድ ሰው ደከረተ ሲባል ገንዘብ ከማጣትና ካለማጣትም ባለፈ በብዙ አእምሯዊና ሥነ ልቦናዊ ጣጣዎች ሊወጠርና መልካም ስብዕናውን ሊያጣ ይችላል፡፡ ለምሣሌ እጮኛው ወይም ሚስቱ የከዳችውና ፍቅሯን ለሌላ አሳልፋ የሰጠችበት ሰው – ብዙ ገንዘብ እያለውም ቢሆን – ሊደከርት ይችላል፡፡ እንዲህ ሲባል ደግሞ ሰውዬው ራሱን እየጣለ፣ በፊት የሌለበትን ባሕርይ ለምሣሌ እንደመቃም፣ ማጨስ፣ መጠጣትና መዘሞት… እያዘወተረ ከጊዜ ወደጊዜ ከሰውነት ተራ እየወጣ ሊሄድ ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ጨርቁን ጥሎ ሊያብድም ይችላል፡፡ መደክረት ጦሱ ብዙ ነው፡፡ መደክረት ተስፋ መቁረጥም ነው፡፡ የደከረተ ሰው ተስፋውን በራሱ ጊዜ አጨልሞ እንዳበደ ውሻ ሞቱን ብቻ የሚጠብቅ ተስፋቢስ ነው፡፡ የደከረተ ሰው ወደ ዐበደ ውሻነት ከተለወጠ በራሱም ላይ ሆነ በጎረቤቶቹና በማኅበረሰቡ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በምንም ዓይነት ሚዛን አይለካም – የሚያደርሰውም አደጋ ሊቀለበስ የሚችል አይደለም፡፡ አያድርስ እንጂ የደከረተ ሰው ከሃይማኖቱም፣ ከባህሉም፣ ከጤናማ ኅሊናውም፣ ከማኅበራዊ ወግ ልማዱም፣ ከይሉኝታና ከሀፍረትም ይወጣና ከእንስሳት ሳይቀር የወረደ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስ እጅግ አደገኛ እንስሳ ይሆናል፡፡ ከደከረተ ሰው ይልቅ አንበሣንና ጅብን በባዶ እጅ መጋፈጥ ይቀላል፡፡ ከእንስሳት ውስጥ በሞራላዊ ሥነ ምግባራቸው ሰው ነን ከምንል ብዙ ሰዎች የሚበልጡ ጉሬዛንና ዕርግብን የመሳሰሉ ግሩም የዓለማችን እንስሳዊ አባላት መኖራቸውን መርሳት የለብንም፡፡ ብዙ እንስሳት ካልደረሱባቸው አይደርሱም፤ የዘንድሮዎቹን እንጃ እንጂ የዱሮ እባቦች ለምሣሌ ሕጻናት እንደጡጦ አፋቸው ውስጥ ቢያስገቧቸው እስኪለቋቸው ይታገሱና አምልጠዋቸው ይፈተለካሉ እንጂ አይነድፏቸውም (ይባል) ነበር፡፡ እንደወያኔ ያለ መጥፎ እባብ ግን የለም – ወያኔ ሕጻናትን ቀርቶ ዐፅምን የሚበቀል፣ በጠላትነት የፈረጀውን ሕዝብ በጥይት፣ በማምከኛ መርፌና በበሽታ በጅምላ የሚያጠፋ፣ በበቀልና በጥላቻ የታወረ መጥፎ አናኮንዳ ነው፡፡ውይ! ወያኔንስ ለጠላትም አይስጥ!
ድክረታ ከተነሳ ዘንድ ወያኔ ከመነሻው የደከረተ ውድብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ የወያኔው ጉጅሌ ከበፊቱ በጥላቻና በቂም በቀል ተነሳስቶ “እነእከሌን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ እነሱን አጥፍቼ የትግራይን ሪፑብሊክ እመሠርታለሁ” በማለቱ ብቻ ያኔ ነው የደከረተው – በመሠረቱ እንኳንስ በድርጅት ደረጃ በግለሰብ ደረጃ እንኳን “እነእገሌን አጠፋለሁ” ብሎ መነሣት በትንሹ ዕብደት ነው – ለዚያውም መዳኛ የሌለው የውሻ ዕብደት፡፡ ዘረኝነትን እንደ መመርያ ያነገበ ሰው፣ ሃይማኖትን እንደ መጠቃቀሚያና መጎዳጃ አድርጎ የተቀበለ ሰው፣ በዘመድ አዝማድና በአምቻ ጋብቻ ሰውን ለመጥቀም እና/ወይም ለመጉዳት የሚፈልግ ሰው፣… ደክርቷል፤ የሰውነት ዋጋም የለውም፡፡ ሃይማኖትም አማናዊ ምግባርም የሌለው በመሆኑ ከፈጣሪ ጋርም ተጣልቷልና የመጨረሻ ምድቡ በምድራዊ ሕይወታቸው የጠፉ ሰዎች ከሚታጎሩበት የሲዖል ከተማ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ወያኔዎች ለድክረታና ለቀቢፀ-ተስፋዊ የጥፋት ዘመቻ ዓይነተኛ ምሣሌዎች ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ አለቃቸው መለስ ከሞተ ወዲህ ለይቶላቸው ደክርተዋል፤ ዕብደት ዓይነቱ ብዙ እንደመሆኑ ጨርቃቸውን አልጣሉም እንጂ በሥልጣን ሱስ፣ በሀብት ፍቅርና በሰው ደም ጥማት ዐብደዋል፡፡ በውነቱ በዚህስ እነሱም በጣም ያሳዝኑኛል – ወደው እንዳልሆነም ይሰማኛል፡፡ ወያኔዎች ይሠሩትንና ይሆኑትን አጥተው ለታዛቢ – ለእኛ – ሳይቀር የጭንቀት መንስዔ ሆነዋል፡፡ በነዚህ ዕብዶች አጓጉል ተግባር የላኳቸው የውጪ ኃይላት ራሳቸውም እጅጉን ሳይገረሙ የሚቀሩ አይመስለኝም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ድርድር ከወያኔ ጋር? የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና መጪው ጊዜ! (ለውይይት መነሻ) - ባይሳ ዋቅ-ወያ

ወያኔዎች ባይደከርቱ ኖሮ በአሁኑ ሰዓት ፕሮ. መረራ ጉዲናን ማሰር አልነበረባቸውም፡፡ ይህ የጅል ሥራቸው የሚያሳየው እጅግ ተስፋ ቆርጠው የሚሠሩትን ነገር የማያውቁ መሆናቸውን ነው፡፡ ይህ ነገር ለማንም የሚገባ አይደለም፡፡ በየትኛውም የአንጎላችሁ ክፍል አስቡት ግራ ነው የሚሆንባችሁ፡፡

ግን ግን ማነው ወያኔን እየመራው ያለው? የሀገራችን መሪስ ማን ነው አሁን? ሀሽሽ ወይንስ አወዳይ ጫት? አበሾ ወይንስ በቂም በቀል ጌሾ የተለወሰ ዕፀፋርስ? ማንስ ነው የሚጠየቅ? ማንስ ነው የሚነግረን? ከየትኛው ቢሮ ነው ሀገሪቱ እየተመራች ያለችው? ዐዋጅ የሚያውጅውስ ማን ነው?ይሄ ኮማንድ ፖስት የሚሉትስ የት ነው ያለው? ረቂቅ ነው ግዑዝ? ሚሊዮኖች የሚታሰሩትና ደብዛቸው የሚጠፋው በማን ትዕዛዝ ነው?የሚደንቅ ነው!! ሀገር እንዲህ እንደዋዛ የጨረባ ተዝካር ትሁን? በኪነ ጥበቡ እኮ ነው ውለን እምንገባው፡፡ መሪ የለን፤ ዳኛ የለ፤ ፖሊስ የለ፤ ፍትህ የለ፤ ዘረፋ እንጂ ንግድ የለ፤ ቤተ ክርስቲያን እንጂ አገልጋይ የለ፤ ገበያ እንጂ ዕቃ ወይ ሸቀጥ የለ፤ እርሻ እንጂ ምርት የለ… ከዚህ በላይ ኪነ-ጥበብ የለም፡፡
ወያኔዎች እስኪወድቁ ድረስ – አሁን አልወደቁም ብዬ ልመንና – በነፃ የማማከር አገልግሎት ልሰጣቸው እችላለሁ፡፡ ግን ደግሞ ዕብድ ለካንስ አይመከርም፡፡ ተስፋ የቆረጠንና ደክርቶ በየፌርማታው የጫት ገረባ እየሰበሰበ የሚያኝክን ወፈፌ መምከርና ወደሰውነት መመለስ እንደማይቻል ሁሉ ወያኔዎችን ለመምከር ማሰብም ራሱ ዕብደት ነው እንጂ ቢሰሙኝ ጥቂት ወራትን በሥልጣን ሊቆዩ የሚያስላቸውን ምክር ልሰጣቸው በተቻለኝ ነበር፡፡ ዐይንም ጆሮም የላቸውም እንጂ እነሱን መምከር እኮ በጣም ቀላል ነው፡፡

ተመልከቱልኝ፡፡ ደግሞም ልድገመው – መረራን ማሰር ምን ጠቀማቸው? ምንስ ይጠቅማቸዋል? የፈለጉትን ማድረግ እንደሚችሉ ለማሳየት ከሆነ ያንን “ችሎታቸውን” ማንም ያውቃል፡፡ ይህ ዕብደት እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም፡፡ አሁንም ቢሆን ቶሎ ይፍቱት፡፡ መረራ ኢትዮጵያ ውስጥ በመኖሩ ብቻ ዱሮውን የታሰረ ነው፡፡ እነሱ ያደረጉት እስር ቤት መለወጥና የስቃይ ዓይነትን ማሻሻል ነው፡፡ ሲገርሙ!

ሰውን ማዋረድና በዚያም መኮፈስ የወያኔዎች የዝቅተኝነት መንፈስ የወለደው መደሰቻቸው እንደሆነ ደግሞ እንኳንስ እኛ መላው ዓለም ያውቃል፡፡ ስለዚህ ይህን ሰውን የማዋረድና በርሱ የመዝናናት በሽታቸውን አሁኑኑ ይታከሙትና ከራሳቸው ጋር ይታረቁ – “አልኩ” ለማለት አልኩ እንጂ ይህን እንደማይሞክሩት አውቃለሁ፡፡ ከዚህ አንጻር ፕሮ. መረራንም ሆነ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን በካቴና እያሰሩ ፍርድ ቤት ማቆም – “አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ” እንዳለችው በቁጥጥር ሥር የሚገኝን ታላቅ ዜጋ በካቴና አላሰርክም ብሎም ንጹሕን ሰው ማሰር ለኔ የጅልነት ሥራ ነው፡፡ እርግጥ ነው ከደከረተ የሰይጣኖች ጉጅሌ ከዚህም በላይ ቢጠበቅ ቢያንስባቸው እንጂ አይበዛባቸውም፡፡ “ልካቸውን አሳየናቸው! ፕሮሶፌር ተብያቸውን ቀፈደድንላቸው! ጀግና ተብያቸውን በካቴና ጠረነፍንላቸው! ወንድነታችንን አሳየናቸው!…” የሚል የጅሎች ሥነ ልቦና የፈጠረውን መልእክት ለማስተላለፍ በሚያደርጉት የቡልሃ ሥራ ወያኔዎች ይበልጥ እየተዋረዱ ናቸው – ለነገሩ ወያኔና ውርደት የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደሚባለው ዓይነት በመሆናቸውና ይሉኝታና ሀፍረት የሚባል ስለማያውቁ ምንም ነገር አይሰማቸውም፡፡ እንጂ ሰው ቢሆኑማ አሟሟታቸውን እንኳን ባሳመሩ ነበር፤ አንድ እግሩ የመቃብር ጉድጓድ ውስጥ የሚገኝ አካል ሶበር ማለት ሲገባው እነዚህ ግን በሚገርም ሁኔታ ድንቁርናቸው እየባሰባቸው ይሄዳል፡፡ ሰው እንዴት ዕድሜ ልኩን እንደተጃጃለ ይኖራል? መቼ ነው አቦይ ስብሃት ሰው የሚሆነው? መቼ ነው አባይ ፀሐይ ሰው የሚሆነው? መቼ ነው አባይ ወልዱ ሰው የሚሆነው? መቼ ነው አርከበ ዕቁባይ ሰው የሚሆነው? መቼ ነው ሣሞራ የኑስ ሰው የሚሆነው? … መቃብራቸው ውስጥ? እውነቴን ነው እኮ ….እየተናደድኩ እኮ ነው እንዲህ የምለው፡፡ በርግጥ መቼ ይሆን እነዚህ ጎምቱ ወያኔዎች ሰው የሚሆኑትና በዕውቀትም በሀብትም በአመለካከትና በአስተሳሰብም የመጨረሻ ዝቅተኛ የሆነ አንድ የዓለም ዜጋ የሚያስበውን ያህል እንኳን ማሰብ የሚጀምሩት? እነሱም እንደኛው ሰው ሆነው እንደሰው መቆጠራቸው አያናድዳችሁም? እኔ እናደዳለሁ፡፡ እነዚህን መሰል ዕኩይ ፍጡራን ምድራዊ ባልደረቦቼ በመሆናቸው የእግር እሳት ሆኖብኛል፡፡ ፕላኔት አልቀይር ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ ጋር እንደሰው መቆጠር በውነቱ ክፉኛ መረገም ነው፡፡

ተመስገን ደሳለኝን መሰወር ለወያኔ እንዴት ሊጠቅም እንደሚችል ሳስብ ውዬ ሳስብ ብውል ሊከሰትልኝ አልቻለም፡፡ ይህን ልጅ ገደሉትም ደበቁትም በዚህ ሰዓት ይህን ማድረግ የነፃነቱን ትግልም ሆነ የእግዜርን የማይቀር ፍርድ ለአፍታም አያቆመውም፡፡ ጎርፍ እየመጣ ነው፡፡ ወያኔን የሚጠራርግ ጎርፍ ከጽርሃ አርያም እየገሰገሰ ነው – ምን ይዋጣቸው? የትግራይ ምድርም ትተፋቸዋለች፡፡ መግቢያ የላቸውም፡፡ መላ የወያኔን ወቅታዊ እንቅስቃሴ ስታዘብ ታዲያ ይህ እየገሰገሰ ያለ ጎርፍ ለምን ዘገዬ በሚል ቁጭት የተቃኘ ይመስላል፡፡ ወያኔዎች በአሁኑ ወቅት ሌት ተቀን የተጠመዱት ሚሊዮኖችን በማሰርና በመግረፍ፣ ሚሊዮኖችን በማሰቃየት፣ ሚሊዮኖችን በጦር በማሳደድ፣ ሚሊዮኖችን በማስፈራራት፣ ሚሊዮኖችን ለመግደል ስናይፐር የታጠቁ ሥልጡን አጋዚዎችን በማሰማራት … ነው፡፡ የመንግሥትና የልማት ሥራ ሁሉ ቀርቶ ዋና የሀገሪቱ በጀት እየወደመና እየባከነ ያለው በሥልጣን ማቆያ ግዳጅ ላይ ነው፡፡ የትም ቢሮ ሂዱ ከሞላ ጎደል በሁሉም ቦታዎች ቅርጻዊ የማስመሰል ሥራ እንጂ እውነተኛ አገልግሎት የለም፤ ዋናው ትኩረት የወያኔን ነፍስ አውሎ እማሳደሩ ላይ ሆኗል – ውሸት እንዳይመስላችሁ – ሃቅ እኮ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ዘጠኝ ሱሪ ምን ይጠቅማቸዋል? ይህ ሁሉ ልፋታቸው በአንድ በኩል ያሳዝነኛል፡፡ የማን እንደሆነ ትዝ የማይለኝ አንድ ቀደምት ትንቢትም ያስታውሰኛል – “…በዚያን ዘመን ሌትም ቀንም ከትከሻቸው የጦር መሣሪያ የማይወርድ የእረኛ ታጣቂዎች ሀገሪቱን ወርረው ከጥንፍ እስካጥናፍ ያጥለቀልቋታል፡፡ መጨረሻቸው ግን …” (እውነቴን ነው…፤ መጨረሻቸውን ግን ሲመጣ እንየው እንጂ ‹ሆድህን ሲቆርጠው ውሎ ቢያድር› አልናገርም!)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማፈንና አደባባይ በመከልከል መገደብ በህግም በታሪክም ያስጠይቃል!! ሲሉ አንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

ወያኔዎች ለምን ይወድቃሉ? “ስለደከረቱ” እንዳትለኝ ብቻ፡፡ እሱ ብቻ አይደለም፡፡
ወያኔዎች የሚወድቁት የኢትዮጵያ ሕዝብ አምርሮ ስላዘነባቸውና ስላለቀሰባቸው በዚያም ምክንያት ፈጣሪ ስለሕዝቡ ዕንባና ስለራሱም ክብር ሲል በሚያወርድባቸው ድንገተኛ ግን የሚጠበቅ መቅሰፍታዊ ውርጅብኝ ነው፡፡ ያም ቀን ደርሷል፡፡ እነሱም ያውቁታል፡፡ የሚርበተበቱትም ለዚህ ነው፡፡ የሣሙና አረፋና የሚንሳፈፍ ገለባ በመጨበጥ ሥልጣናቸውን ለማቆየት የሚዳክሩትም ለዚህ ነው፡፡ አንተ ብቻ “አሄሄ! ማን ሊነካቸው!” እያልክ ተስፋህን ቁረጥ፡፡ ይልቁንስ ቀና በል፤ ወደፈጣሪህም ጩኽ፡፡
አማራንና ኦርቶዶክስን በዐዋጅ ለማጥፋት ካደረጉት ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ሃይማኖት ዕኩይ ተግባር በተጓዳኝ ብዙ ወንጀል ሰርተዋል፡፡ 0.00001 በመቶውን ከዚህ ቀጥዬ ላስታውስ፡፡ አትሰለቹ(ኝ)ም አይደል?
ከቅድሙ ልጅ የመረረ ጨዋታ ልጀምር፡፡ እውነተኛ ተባራሪ ዜና ነው፡፡ ከተደበቁት ሚሊዮናት ዜናዎች አንዱ ነው ይሄ – ግን እነሱ እንወክለዋለን ብለው መሣሪያቸው ካደረጉት ወገናችን ጋር ሌላው ወገናችን ይብስ እንዳይቀያየምና ሆድ እንዳይብሰው ስንል ይህን ዓይነቱን የወያኔዎች ወንጀል በስፋት አንናገረውም – በሌላም በኩል ስለነሱ እኛው እያፈርንም ነው ይህን ቁሣዊ ቅሌታቸውን አዘውትረን የማንናገረው፡፡ ያሳፍራል እኮ…
ቦሌ አካባቢ ነው፤ አንድ ከውጪ የመጣ ሰው ከአንድ ቤተሰብ ጋር ተስማምቶ ሆስፒታል ሊሠራ ይፈልጋል፡፡ ገንዘብ ስላጠረው ዳሸን ባንክን 5 ሚሊዮን ብር ብድር ይጠይቃል፡፡ ብድር ፈቃጁ ወያኔ-ትግሬ ነው፡፡ ታዲያ በሁሉም ባንኮች ወሳኝ የኃላፊነት ቦታዎችን የሚይዙት በአብዛኛው ወያኔ ትግሬዎች መሆናቸውን በእግረ መንገድ ልብ ይሏል፡፡ ያ ብድር የተጠየቀ ኃላፊ ዐይኖቹን በበረኪና አጥቦ “ 1.5 ሚሊዮኑን ለኔ ከሰጣችሁኝ የጠየቃችሁት ብድር ይፈቀድላችኋል!” ይላቸዋል፡፡ በቀሪው 3.5 ሚሊዮን ብር ምኑን ይሥሩት? ይሄው ኃላፊ ለሌላ ሀብታም ትግሬ ወያኔ ያለምንም ማስያዣ(ኮላተራል ይሉታል ባለሙያዎቹ) 40 ሚሊዮን ብር አበደረው – ሰጠው እንጂ ምኑን አበደረው ይባላል፡፡ አትገረሙም እንዴ?
አንዲት ቅልብጭ ያለች አጭር ጥያቄ – ለመሆኑ ኢትዮጵያ አሁን የማን ናት? አንዲት ሌላ ልጨምር ደግሞ – ዱሮስ የማን ነበረች? የቤት ሥራ – ታሪክን እንመርምር፡፡ ወደ እውነቱ ማማም እንውጣ፡፡
ያለምንም ማጋነን የመንግሥት ጓዳ ጎድጓዳ ሁሉ በትግሬ ወያኔ የተያዘ ነው – የግሉም ሳይቀር፡፡ የኮንስትራክሽን ፈቃድ ሌላው የሚያገኘው ከደረጃ 5 በላይ ነው፤ የኔ ወንድሞች ግን ከዚያ በታች ነው፡፡ ሁሉንም የመንግሥት ጨረታና የግንባታ ፕሮጀክት የኔ ወንድሞች ይወስዱና በሰብኮንትራት ለምሥኪኑ ሌላ በመስጠት በትንሽ ዋጋ ያሰሩታል፡፡ እነሱ ቁጭ ብለው ሚሊዮኔርና ቢሊዮኔር መሆን ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ ለምን ቢባል በየመሥሪያ ቤቱ ያለው ሹም የነሱና ስለነሱ የተሾመ ነውና፡፡ “ጉድ ነሽ ያንኮበር ቅጠል” አሉ?
ቦሌ መድኃኒዓለም አካባቢ “አዝመራ ሽሮ” የሚባል ትልቅ ሆቴል አለ – በሽሮው የሚታወቅ፤ (ከኔ የማይጠበቅ ተራ ሀሜታ መሆኑን ሳትነግሩኝ አውቀዋለሁ – ሌላ ምርጫ አጥቼ ነው)፡፡ ያ ሽሮ ቤት የወያኔ ነጋዴ ቤት ነው፡፡ አንድ ንጹሕ ሽሮ – ምንም አጃቢ የሌለው ማለቴ ነው – 80 ብር ሲሸጥ አንድም ትኬት የለም አሉ፡፡ ቫት ግዛዕ ምዛዕ በነዚህ የትግሬ ወያኔዎች የንግድ ቤቶች ተረት ነው – አይታወቅም፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴርም ወደነዚህ ቤቶች ቢሄድ – ደግነቱ አይሄድም እንጂ – እግሩን ቀልጥመው ነው አሉ የሚልኩት – ስድብም ተመርቆለት ሊያውም፡፡ የሚ/ር መ/ቤቱ ሠራተኞች ምን ጥልቅ አድርጓቸው ነው ሀገሪቱን በወለድ አገድ ጠፍረው ወደያዙት የወያኔ ንግድ ቤቶች የሚሄዱት? ባይሆን ወደምሥኪኖቹ ቤት እየሄዱ “ላለፉት አምስት ዓመታት ላጭበረበርከው/ሽው ንግድ 6 ሚሊዮን ክፈል/ይ” ይሉና በማስፈራራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ብር የሚያገኙት ከአንበሦቹ ሳይሆን ከዐይጦቹና ከጥንቸሎቹ ነው፡፡ “ላለው ይጨመርለታል፤ የሌለው ግን ያቺ ያለችው ትንሽ ነገርም ትወሰድበታለች” የተባለው የትኛው መጽሐፍ ላይ ይሆን? ዝኮነ ኮይኑ አኅዋትና ከምዚ ዓይነት ዝብዒን ዐሠማን ኢዮም፡፡ ብኣየነይቲ መዓልቲ ከምዝተፈጠሩ ድማ ጎይታና ጥራሕ እዩ ዝፈልጥ፡፡ ኦ! ኳርት ቀየርኩ?
ወደ ማርካቶ እናምራ፡፡ ዱሮ በደጉ ዘመን ማርካቶ በጉራጌ እንዳልተጥለቀለቀች ዛሬ በወያኔ የጅምላና ችርቻሮ ነጋዴ ከአፍ እስከ ገደፏ ሞልታለች – ለነገሩ ማርካቶ ብቻ ሳትሆን ሁሉም የንግድ ማዕከላት እንዲሁ ናቸው፡፡ ነገሩ ታዲያ እንዲህ ነው፡- ትግሬ ወያኔ ቀረጥና የቤት ኪራይ የለበትም፤ ቢኖርበትም የይስሙላና ለታይታ በጣም ጥቂት ገንዘብ ነው የሚከፍል – መክፈል ከተባለ፡፡ ምስኪኖቹ ሌሎቹ ግን ይከመርባቸዋል – መጨረሻችንን ያብጅልን እንጂ ይሄ “እነሱ”ና “እኛ” እኮ ጉድ አፈላ ጎበዝ፡፡ በትግርኛ “ውፃዕ አይተበሎ፣ ከምፅወፅዕ ግበሮ” ይባላል፡፡ መተርጎም የሚያስፈልገኝ አይመስለኝም፡፡ ግልጽ ነውና፡፡ እንጂ “ውጣ አትበለው፣ እንዲወጣ ግን አድርገው” ብዬ ወደ ወንድሙ ወደ አማርኛ መመለስ አያቅተኝም ነበር፤ ወይ ዘበን! ከመይ ዓይነት ዘበን መፂኧን! እናልህ ምሥኪኖቹ ሌሎች ነጋዴዎች በ3000 ብር ቢሸጡት የሚያከስራቸውን አንድ ዕቃ እነወዩ በ1800 እና በ2000 ብር ‹ኳ› ያደርጉትና ስንጥቅ ያተርፉበታል፡፡ የግፍ ግፍ፡፡ የምትከሰው የምትወቅሰው የለም፡፡ ሥርዓቱ እንዲህ ከላይ እስከታች የበከተና የደከረተ የዱርየዎች ስብስብ በመሆኑ አንተ ያለህ አማራጭ ለነሱ እንጨት ፈላጭ መሆን ወይም የምትወደውን ቤተሰብ ሜዳ ላይ በትነህ ለግርድናና ለእሽክርና ወደ ውጪ መሰደድ ብቻ ነው፡፡ እዚያም ሄደህ ላይቀናህ ይችላል፡፡ ወያኔዎች ዘር አይውጣላቸው!
ይህን ሁሉ ታሪክ ታዲያ አሜሪካውያን ያውቃሉ፡፡ ይህን ሁሉ ጉድ አውሮፓውያን ያውቃሉ፡፡ በነዚህ እፍኝ በማይሞሉ ጥጋበኛ ትግሬ ወያኔዎች የሚደርስብንን ይህን ሁሉ ግፍና በደል አውስታራሊያና ኤዥያ ያውቃሉ፡፡ እነጃፓንና ራሽያም ያውቃሉ፡፡ ይህን ሁሉ የወያኔ ሕዝብና አገር ላይ መጨማለቅ ሰማይና ምድር በደንብ ያውቃሉ፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያን ሰዎች ቢተዋትና ከዚያም ባለፈ ለጥፋቷ ቢሰለፉ ፈጣሪ ግን ፈጽሞ እንደማይረሳትና ወያኔዎችን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ድምጥማጣቸውን እንደሚያጠፋቸው የምናምነውና አምነንም በልበ ሙሉነት የምንመሰክረው፡፡ እመኑኝ እነዚህ እርጉማን አይቀጡ ቅጣት ይቀጣሉ፡፡ደግሞ ለቅጣት ጌታን ማን ብሎት! እሱን እንደኔ “እባክህን አንዲት ቪትዝ ግዛልኝ!” ብላችሁ አትነትርኩት እንጂ ብድራትን ለመክፈልማ እንደርሱ የሚሆን የለም፤ እኛ ግን እንቸኩላለን፤ ስለምንቸኩልም በቶሎ እናኮርፈዋለን፤ ስለምናኮርፈውም እናስቀይመዋለን፤ ስለምናስቀይመውም ፊቱን እያዞረብን የሥርየታችንን ጊዜ ያርቅብናል፡፡ ይሁንና መራቅ መቅረትን እንደማያመለክት መረዳትና ወደርሱም መጠጋት ይገባናል፡፡ …
ከጀመርኩ አይቀር በትምህርቱ ረገድ እንዴት እንደገደሉን ጥቂት ልበል፡፡ እኔ የምለው የለም፡፡ ግን ቀጣዩን ማስታወቂያ አንብቡና ራሳችሁም የምትሉትን በሉ፡፡ መረጃው ከፌስቡክ የተገኘ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሿሿው በኋላ ስለሚሆነው ልንገርህ ይልቁንስ - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

አንድ ትልቅ የሀገር ጠላት አንድን ሀገር ማጥቃት ሲፈልግ በመጀመሪያ የሚያደርገው የዚያን ሀገር ቁሣዊና መንፈሣዊ ዕሤት ማጥፋት ወይም ማውደም ነው፡፡ የአንድ ሀገር አጠቃላይ ዕሤቶች መሠረት ደግሞ ትምህርት ነው፡፡ ስለሆነም የጥፋት ዒላማ ውስጥ የገባን ሀገር የትምህርት ሥርዓት ደብዛውን ማጥፋት የዚያ ሀገር ዋና ጠላት ትልቁ ዓላማና ግብ ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢትዮጵያ በወያኔ አማካይነት የትምህርት ሥርዓቷ እንዲህ እንዳሁኑ ድራሹ እንዲጠፋና ከፍ ሲልና ዝቅ ሲል እንደምናየው ያለ ክስረት ውስጥ እንድትገባ የተደረገው፡፡
ከፍ ሲል የምታዬት ማስታወቂያ መንገድ ላይ በድፍረት ተሰቅሎ ከሚታይ የማስታወቂያ ቢልቦርድ የተገኘ ነው፡፡ የድፍረቱ መጠን ጎላ የሚለው ይህ “ተቋም” የሚሰጠው ትምህርት የእንግሊዝኛ ቋንቋ መሆኑ ነው፡፡ስህተቶቹን እኔ እንደገባኝና እንደመሰለኝ ላርማቸውና ወደሌላ እውነተኛ ስህተቶች እንለፍ፡፡ እዚህ አካባቢ እያልኩት ያለውን የምለው ስህተትን መፈለግ ጠባየ ሆኖ ሳይሆን – ይቅርታችሁንና – የአወዳደቃችንን መጠን ለማሳየት ፈልጌ ነው፡፡ እንጂ መሳሳት ሰውኛ መሆኑን፣ ከስህተትም መማር ብልህነትና ተገቢም መሆኑን ዘንግቼው አይደለም፡፡ ስህተትን እንደፋሽን አድርገን ከተኮፈስንበት ወይም ፈላስፋው እንዳለው አለማወቃችንን ባለማወቅ በድንቁርናችን የምንኮራ ከሆነ ነገር ተበላሽቷልና ጠንቀቅ ማለት፣ መፍትሔም መሻት ይገባናል፡፡ አሁን የምናየው አካሄድ ዕውቀትም እንደፍቅር ገደል የገባች ይመስላል፡፡

1. forign — to mean Foreign (spelling and mechanics error)
2. languge — to mean Language (spelling and mechanics error)
3. inistitute — to mean Institute (spelling and mechanics error)
4. Arebic —- to mean Arabic (spelling error)
5. amharic — to mean Amharic (mechanics)
6. forigners —- foreigners (spelling error)
7. intermidiate — intermediate (spelling error)
8. advance level — advanced level (grammar error)
9. አመት —— ዓመት (የሆሄ ችግር)
10. ለህፃናትም —- ለሕጻናትም (የሆሄ ችግር)
11. english —- English (mechanics)
12. vision —- Vision (mechanics)

ዛሬ እዚህ ደርሰናል፡፡ ከዚህም አልፈናል ኧረ! ላሳያችሁ፡፡

EPRDF has winned the election — የምርጫ ቦርዱ ፕሮፌሰር የተናገረው …
We support it equivocally … ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬው የተናገረው …
I didn’t knew that … አንድ ዶክተር ሲናገር የሰማሁት
I doesn’t know that you was here… ከካባ (ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲን ካባ – ድንጋይ ማምረቻ ይሉታል) በማስተርስ ዲግሪ የተመረቀ አንድ ጓደኛየ የተናገረውና በጆሮየ በታምቡሩ የሰማሁት…
Do not afraid me guys! አንዱ የቋንቋ ሊቅ የተናገረው — ግን ብዙዎችም የሚሉት …
The buying government of Federal Republic of Ethiopia – “ገዢው የኢትዮጵያ መንግሥት” (the incumbent government) ለማለት አንድ ዶክተር የዩንቨርስቲ መምህር በሚያስተምራቸው ተማሪዎች ፊት (ክፍል ውስጥ) በቅርቡ እንደተናገረው በተባራሪ ወሬ የሰማሁትና በጣም እያሳቀቀ ያሳቀኝ ( ዕድገታችን አያኮራም ታዲያ?)

ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፡፡ ዋናው ግን በትምህርትም በሉት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካም በሉት በሃይማኖትና በሞራል … ምን አለፋችሁ በሁሉም ረገድ ደክርተናል፡፡ የደከረተ ማኅበረሰብ ደግሞ መታደስ ይኖርበታል፡፡ ነጋዴው ደክርቷል፡፡ መምህሩ ደክርቷል፡፡ ጳጳሣቱና ቀሳውስቱ ደክርተዋል – ለሥጋቸው እንጂ ለማተባቸው አልቆሙምና፡፡ ፓትርያርኩ ከደከረቱ ሰነበቱ – ከዘረኝነት ወዲያ ሰውን የሚያደከርት ላሳር ነውና፡፡ ወያኔ ከመደክረትም አልፎ በስብሶ ግማቱ በኢትዮጵያ በሮች በኩል አላሳልፍ ብሏል፤ ግን የሚደፍር ጠፋ፡፡ የጌታ ቀን ባለመድረሷ ምክንያት ይህ ሥርዓት እንዲህ በቁሙ በክቶና ጠንብቶ እያለ ጠጋ ብሎ የሚገነብረው ጀግና ሊገኝ አልቻለም፡፡ እነሱ እባካችሁን ጣሉን እያሉ ሲማጠኑ የሚሰማቸው ሰው አልተገኘም፡፡ የትግሬን ባህል ያላወቀው ፈረንጅ ተስፋ ቆርጦ ኮትና ሸሚዙን ሲለባብስ “አውድቀኒ” ያለችው ወዳ አልነበረም፡፡ ወያኔዎችም “አውድቁና” እንዳበሉ እዮም፡፡ ሠናይ ጊዜ ንኹላትኹም ዜጋታት ኢትዮጵያ፡፡

Share