ዩቱብ ኢንተርኔት በሌለባቸው ቦታዎች ቪዲዮዎችን መመልከት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

(ዘ-ሐበሻ) በጎግል ኩባንያ ስር የሚገኘውና በአሁኑ ወቅት ካሉት ማህበራዊ ሚዲያ ኔትወርኮች መካከል ከፌስቡክ ቀጥሎ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዘው ዩቱብ ኢንተርኔት በሌለባቸው ቦታዎች ቪዲዮዎችን ለመመልከትና ዳውንሎድ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ::

ዩቱብ (YouTube Go) የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኸው ቴክኖሎጂ በአሁኑ ወቅት በሃገረ ሕንድ ሙከራ ተደርጎበት በመስራት ላይ ይገኛል::
ዩቱብ በሰጠው መግለጫ ይህን ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረግ ያስገደደው ቀርፋፋ ፍትነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው ስፍራዎች ዩቱብን መጠቀም እንዲችሉ በማሰብ ነው::

ዩቱብ ጎ በተለይም የኢንተርኔት ዳታዎችን ለመቆጠበም ይረዳል የሚለው ይኸው መግለጫው ቪዲዮዎችን ለማውረድና ለመጫን ምን ያህል ዳታዎችን እንደሚወስድ እንደሚያሳይና የቪዲዮን ኳሊቲ በመጨመርና በመቀነስ መጫን እና ማውረድ ይችላሉ ይላል::

በፐርሰናል ሆትስፖት ኢንተርኔትን ለጓደኛ በማጋራትም ቪዲዮዎችን ከጓደኞችዎ ጋር በዩቱብ ጎ መመልከትም እንደሚቻል ተገልጿል::

 

ይህ አፕ በቅርብ ቀን በስልኮች ላይ ይለቀቃል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የምክር ቤት አባላት ለ ዐቢይ አሕመድ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች
Share