የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች 12 አማሮችን በመተማ ገደሉ | ከ30 በላይ ቆስለዋል

 

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በመተማ በተፈጠረው ሕዝባዊ ተቃውሞ የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት ወደ ሕዝብ ቀጥታ በመተኮስ እስካሁን የተረጋገጠ 12 አማሮችን መግደሉንና የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

መተማ ከተማ የትግራይ ነጻ አውጪ ጦር በአማሮች ላይ የዘር ማጥፋት ለመፈጸም ወደ ህዝቡ ሲተኩስ ከ30 በላይ ወጣቶች ደግሞ እግሮቻቸውን በጥይት በምመታት እንዳቆሰላቸው ለማወቅ ተችሏል::

በመተማ የትግራይ ተገንጣይ መንግስት ደጋፊ የሆኑ የንግድ ድርጅቶች መቃጠላቸው ሲሰማ ሕዝቡም እስካሁን ቁጥራቸው በይፋ ያልታወቀ ወታደሮችን መግደሉም ተሰምቷል::

የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር የሆንችው የንግድ ከተማዋ መተማ ዛሬ በጭስ ታፍና ውላለች:: የትግራይ ነጻ አውጪ ጦር ወደ ሕዝቡ ቀጥታ መተኮሱን የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች በሁለት ሃገራት መካከል የሚደረግ ጦርነት ይመስል ነበር ብለዋል::