ዓባይ ሊያለማን ወይስ ሊያጠፋን? – የሕዳሴው ግድብና ዐባይ፣ የሚሊኒየሙ ዐባይ ተጋቦት

አዘጋጅ ለኢትዮጵያ ፍቅር ከቃሊቲ

የዐባይ ሥረ_መሠረትና የሕዳሴው ግድብ ማነጣጠሪያ እነሆ!
ጥናቱ የተፈጸመው ሚያዚያ 2003 (2011 እ ኤ አ) ነው። አቅርቦት የፀሐፊው ትክክለኛ ቅጂ (በአቀራረባዊ ጥንቅር) መነሻ የጊዜው የኢትዮጵያ ጉዳይ ሆኖ የቀጠለውና ሕዝቡም የጠየቁትን እያደረገ ያለበት የሚሌኒየሙ ታላቅ የዐባይ ግድብ እንደተነገረው፤ የሚገደበው ከሱዳን ድንበር 17 (አሥራ ሰባት) ኪሎሜትር ባለ ቀረቤታ በዐባይ ወንዝ ላይ ነው። ግድቡ ወደ 62 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም አለው። የውኃው መጠን የጣና ሐይቅ ከሚይዘው ውኃ እጥፍ ይሆናል።
በሚታቆረው ውኃ 6ሺ (ስድስት ሺ) ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ሊመረት ታቅዷል። የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሱዳንና ለግብፅም ሊሸጥ ታስቧል። ይህ ግንባታ 80
ቢሊዮን ብር ይፈልጋል።

ገንዘቡ በግብፅ ተፅዕኖ ሳቢያ የውጭ ብድር ወይም ዕርዳታ እንዳያገኝ ስለተደረገ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ የመዋጮና ቦንድ ሺያጭ ሊሸፈን ተወስኗል።ለሕዝቡም ታሪካዊ ተዐምር ሊሠራ እንደሆነና የልማት
ሁሉ አንጋፋ እንደሆነ ተነግሮት የቻለውንና ያልቻለውንም ከማድረጉ በላይ ለሃገር የሚበጅ ልማታዊ ድንቅ እንደተፈጠረ ተበስሮለታል። ባለፈው ሚያዚያ (April) 2013 እ ኤ አ
ወር ማብቃያ አካባቢ በወጣው ዜና ደግሞ (ይህ ጥንቅር ከቀረበ ከሁለት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው። ቻይና ለሚሌኒየሙ ግድብ ግንባታ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ልታበድር ነው ተብሏል።
ታዲያ ግብፅና ሱዳን ምነው ዝም አሉ?
እኮ ቢጠቅማቸውማ ነው ዝምታቸው፤ የዐባይ ልጅ ይህ እንዴት ያየዋል? አባይ (ናይል)እየተባለ የሚጠራው በዓለም ረዥሙ ወንዝ፣6671 ኪሎ ሜትር እርዝማት ሲኖረው፣ከዘጠኝ አገሮች ይመነጫል።ግብፅ ምንም የምታመነጨው የውኃ አስተዋፆ የላትም። ሆኖም በናይል ውኃ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ አገር ናት። ግብፅ 100% የሰሐራ በረሃ አካል በመሆኗ በሜዲቴሪንያን አካባቢ ጥቂት ዝናብ ጠብ ከማለቱ ሌላ ከዓመት ዓመት ዝናብ አይጥልም።
በሌላ በኩል ደግሞ ከሁሉም የናይል ተፋሰስ አገሮች ይበልጥ የ80% በመቶ ከአባይና ከሌሎች የኢትዮጵያ ወንዞች የሚገኘው ውኃ አባይን ይገልጸዋል። በጠቅላላው የናይል ወንዝ 74 ቢሊዮን
ሜትር ኩብ ውኃ በዓመት ሲሰጥ ከዚህ ውስጥ ከኢትዮጵያ የሚገኘው የውኃ ድርሻ መጠን 54 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ነው። የዚህ ሁሉ ውኃ ምንጭ ኢትዮጵያ ስትሆን፤እንደ ሱዳንና ግብፅ እምነት ጥቂት ውኃ እንኳን ለመጠቀም መብት የላትም።ሌሎቹንም የናይል ውኃ አመንጪና ባለቤት የራስጌ አገሮችን በማግለል መብታቸውን ገፍፈው ሱዳንና ግብፅ ተከፋፍለውታል።
እ ኤ አ 1959 ዓ ም በተፈራረሙት ስምምነት መሠረት ግብፅ 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ፤ሱዳን ደግሞ 18.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ይወስዳሉ።በተለይ ግብፅ የውኃው ዋና ባለቤት እራሷን አድርጋ በመቁጠር አመንጪዎቹን የራስጌ አገሮች ለአነስተኛ የውኃ ጠቀሜታ እንኳን ፈቃጅ መሆን አለብኝ ባይ ናት። ለዚህም ኢትዮጵያን ማዳከም ወይንም ማጥፋት ተልዕኮዋ ሆኗል።
የአባይ ጠቀሜታ
ግብፅና ሱዳን ፍፁም ተጠቃሚዎች ሲሆኑ፤ በተቃራኒው የውኃ መነሻ የሆነችው ኢትዮጵያ ተጠቃሚ አልሆነችም። ግብፅ 3.0 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመስኖ ታለማለች። ሱዳን 1.8 ሚሊዮን ሄክታር እንደዚሁ በናይል መስኖ ታለማለች። ኢትዮጵያ አትጠቀምም በመስኖ አለማችም። የግብፅ በረሃ በናይል ውኃ በሺ ዓመታት የሚቆጠር የመስኖ እርሻ ልምድ ለምቶ እራሳቸውን ከመመገብ አልፈው የዳበረ ኢኮኖሚ ገንብተውበታል። አባይን ወደ ምዕራብ የግብፅ በረሃ ቀይሰው በመውሰድ ተጨማሪ 1.2 ሚሊዮን ሄክታር በረሃ ለማልማት መንቀሳቀስ ከጀመሩ ቆይተዋል።በዚህ ምዕራባዊ ከተማ ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የሚኖርበት ዘመናዊ ከተማ እየተገነባ ነው። የሲናይንም በረሃ ለማልማት በዓመት 4.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ የአባይ ውኃ የሚያስተላልፍ ቧንቧ ዘርግተዋል። የመስኖ ሥራቸውን ለማካሄድ ያስቻላቸውም ታላቁ የአሳዋን ግድብ ነው።ግድቡ 162 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የማከማቸት አቅም አለው። በክረምት ወራት ከኢትዮጵያ የሚፈሰውን ውኃ አጠራቅመው በመያዝ በሰከንድ 1500 ቶን ውኃ እየለቀቀ በረሃውን ያለማል። ይህም ሆኖ በግብፆች ዕቅድ ተጨማሪ በረሃ ለማልማት 15ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ተጨማሪ ያስፈልገዋል። ለዚህም የተለያዩ
ፕሮጀክቶች አስጠንተዋል። ጥናቱ ተጠናቆ ግንባታውም ተጀምሮ የነበረው አንዱ ፕሮጀክት በደቡብ ሱዳን ክልል ያለው የጀንገሌ ካናል ፕሮጀክት ነበር። የናይል ወንዝ በደቡብ ሱዳን ሱድ እየተባለ
የሚጠራውን ረባዳና ረግረግ ሰፊ መሬት አቋርጦ ያልፍል።ወንዙ በክረምት ከአፍ እስከ ገደብ ሲሞላ ግደቡን ጥሶ ለጥ ወዳለው ሜዳ መፍሰስ ይጀምራል።ግድቡን አልፎ የተንጣለለው ውኃ ተመልሶ ወደ ወንዙ ሊገባ ስለማይችል፤እንደተንጣለለ ይደርቃል።ይህም በፀሐይ ሙቀት እየተነነ ይጠፋል። ታዲያ ግብፃውያን የጀንግሌ ካናልን ፕሮጀክት ያጠኑትና ሥራውንም የጀመሩት በትነት የሚባክነውን ውኃ
በማግኘት የናይልን ውኃ መጠን 10% ከፍ ለማድረግ ነበር።
1ኛ የጀንግሌ ካናሉ ግንባታ የተጀመረው የደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ድርጅት የነፃነት እንቅስቃሴ በጀመረበት ወቅት ስለነበር ፕሮጀክቱ ሳይገፋ አገራችን ይደርቃል፣ ኢኮሎጂውም ይለወጣል፣ በማለት
ኤስ .ፒ .ኤል. ኤም ፕሮጀክቱ ላይ ጥቃት በመሰንዘር አጨናገፈው።
2ኛ ተጨማሪ ውኃ ለማግኘት ያስችላል ተብሎ የተጠናው ሌላው ፕሮጀክት ደግሞ በኢትዮጵያ ትልልቅ ግድቦች መገንባትና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ነው። ግብፅ በረሃማ አገር በመሆኗ የፀሐይ
ሙቀት ያጠቃታል፤በዚያ የተነሣ በአገራቸው ከተገነባው ቃላቁ የአስዋን ግድብ በፀሐይ ሙቀት ብቻ በትነት ከተከማቸው ውኃ 12% ይባክናል።ይህ በጣም የሚያሳስባቸው ጉዳይ ነው። ብዙ ውኃ ሊይዝ የሚችል ሌላ ትልቅ ግድብ ለመገንባት የሚቻለበት ቦታ ስለሌላቸው ተጨማሪ ውኃ በሃገራቸው ውስጥ ለማከማቸት ያላቸው ዕድል በጣም የመነመነ መሆኑን ተረዱት። በዚህ የተነሣ ጥረታቸውን በኢትዮጵያ ላይ አድርገዋል።በደጋው ኢትዮጵያ ትላልቅ ግድቦች ለገነቡባቸው የሚችሉበት ቦታዎች በርካታ ናቸው። በሚገደቡት ግድቦች የሚከማቸው ውኃ በትነት የመባከን አደጋ አያጋጥመውም።ውኃው ሳይባክን ለብዙ ጊዜ ተጠብቆ የመቆየት ዕድል አለው።ኤሌክትሪክ ለማምረት እየተባለ ከሚገነቡት ግድቦች ከሚለቀቀው ውኃ ምን ያህል ተጨማሪ ውኃ ሊገኝ እንደሚችል ግብፃውያን አስጠንተው ውቀውታል።
በጥናቱ መሠረት በኢትዮጵያ 23 ትላልቅ ግድቦችን በአባይ መጋቢ ወንዞች ላይ መገንባት የሚቻልባቸው ቦታዎች ተለይተው ታውቀዋል፤መነሻ ጥናት ተካሄዶባቸዋል፤እንደጥናቱ በእነዚህ ቦቻዎች በሚገነቡ ግድቦች ብዙ ቢሊዮን ሜትር ኩብ መጠን ያለው ውኃ ይከማቻል።ከዚያም በያንዳንዱ ግድብ የሚተከሉት የኤሌክትሪክ ማመንጫ ተርባይን ለማሽከርከር ውኃ ይለቀቃል።የአባይ ወንዝ በሚሞላበት ወቅት የአገራችንን ድንበር አልፎ ሱዳን ሲገባ የሚያፈሰው የውኃ መጠን 400 ሜትር ኩብ ውኃ በሰኮንድ ሲሆን አባይ ደረቀ በሚባልበት በበጋው ወቅት ደግሞ 4 ሜትር ኩብ ውኃ በሰኮንድ ይፈሳል።
ልዩነቱን አጢኑት በበጋው የሚፈሰው በአንድ መቶ ጊዜ ይቀንሳል።ከዚህ ሁኔታ መገንዘብ የሚቻለው በሱዳንም ሆነ በግብፅ በክረምት ወራት ከኢትዮጵያ የሚፈስላቸውን ውኃ ገድበው በመያዝ በበጋ ወራት እየለቀቁ መጠነኛ የእርሻ ሥራ ከማካሄድ ውጭ የመስኖ እርሻ እንቅስቃሴ አያካሄዱም ማለት ነው። በኢትዮጵያ ግድቦች ተገንብተው ውኃ እየለቀቁ ተርባይኖችን ማሽከርከር ሰንጀምር ግን ይህ
ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። ከተጠኑት 23 የግድብ ሥፍራዎች ውስጥ አነስተኛ ውኃ የማከማቸት አቅም ያላቸው አራት ግድቦች ቢገነቡና በየአንዳንዱ ግድብ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት፤ አራት አራት
ተርባይኖች ቢተከሉና እነዚህን ተርባይኖች ለማሽከርከር 20 ሜትር ኩብ ውኃ በሰኮንድ ቢለቀቅ ሱዳንና ግብፅን አባይ ሲደርቅ 80 ሜትር ኩብ ውኃ በሰኮንድ ያገኛሉ ማለት ነው።
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ብቻ ለማምረት ፈልጋ ግድብ ከገደበችና ተርባይኖችን ለማሽከርከር አንድ ጊዜ ውኃ መልቀቅ ከጀመረች በኋላ ውኃውን በከፊል ወይም በሙሉ ለመስኖ እርሻ ልማት መጠቀም
ብትሞክር የሱዳንና የግብፅን ሕዝቦች በረሃብ ፈጀች፤ የአባይን አቅጣጫ ቀየረች፤ በሚል ሰበብ ለጦርነት መነሳታቸው አይቀርም። በዓለም አቀፍ ደረጃም እንድትወገዝ ፓለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ጫና
እንዲወድቅባት ያደርጋሉ።
በዚህ ምክንያት በአባይ ወይም በአባይ ገባር ወንዞች ላይ ግድብ ገንብተን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከመጀመራችን በፊት ውሎ አድሮ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ሁኔታ አለመፍጠሩን ከብዙ አቅጣጫዎች መመርመር አለብን። እንደሚታወቀው የኤሌክትሪክ ኃይል ለማንኛውም አገር ዕድገትና ሥልጣኔ ወሳኝ ኃይል ነው። ኃይል እንደመሆኑ ሁሉ ኢትዮጵያም የኢሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛ ደረጃ ያስፈልጋታል። በቀላል መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት ደግሞ ያላትን የውኃ ኃይል መጠቀም ይኖርባታል። በውኃው ኃይል ኤሌክትሪክ ስናመርት ግን ተርባይኖቹን የሚያሽከረክረው ውኃ ተለቆ የሚሄድ ሳይሆን ለመስኖ ልማት ላይ መዋል ይኖርበታል።ግድብ ፣ገድበን ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ስናስብ፣ የሚለቀቀው ውኃ እታች ወርዶ ማሳውን እንዲያጠጣ ተደርጎ መታቀድ ይኖርበታል።በዚህ አኳኋን ካልታቀደ በከፍተኛ ወጪ ያጠራቀምነውን ውኃ ያለምንም ክፍያ ለሱዳንና ለግብፅ አሳለፈን ሰጠን ማለት ነው። ከዚህ ግንዛቤ በመነሣት በደርግ ጊዜ የመልካ ዋከና የኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያ ሲገነባ በተጓዳኝ በኡጋዴን ጎዴ አካባቢ ተርባይኑን ለማሽከርከር የሚለቀቀው ውኃ ተጠልፎ እስከ 50ሺ ሄክታር የመስኖ እርሻ እንዲያጠጣ ታቅዶ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ሥራ እንደጀመረ የ20ሺ ሄክታር ማሳ እንዲያለማ ተደርጎ ነበር።
በሌላ በኩል ከልማት ጋር ሣይያያዝ የተገነባው የፊንጫ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ጣቢያ የሚለቀቀው ውኃ ያለጥቅም መፍሰሱን በመመልክት ለስኳር ፋብሪካ ጥሬ ዕቃ የሚሆን ሸንኮራ አገዳ በ10ሺ ሄክታር ማሳ እንዲያለማ ታቅዶ ሥራው ተጀምሮ ነበር።የጣናን ሃይቅ በማሳደግ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ሲወሰን በተመሳሳይ መንገድ የሚለቀቀውን ውኃ በመጠቀም በበለስ ሸለቆ እስከ 100ሺ
ሄክታር የመስኖ እርሻ ለማት ለማካሄድ እንቅስቃሴው ተጀምሮ ነበር።በሌሎች አካባቢዎችም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በሚታሰብበት ጊዜ የሚለቀቀው ውኃ ጥቅም ላይ ውሎ የአገራችንን ኤኮኖሚ ለማሳደግና በምግብም ራሳችንን እንድንችል እንዲረዳ ጎን ለጎን መታቀድ ነበረበት።
ከመስኖ ልማት ጋር ሳይያያዝ ግድብ መገንባትና ኤሌክትሪክ ማመንጨት የግብፅን ፍላጎት በፍቃደኝነት ማሟላት ማለት ነው።ግብፅ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን በኢትዮጵያ ትላልቅ ግድቦችን ለመገንባት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የሚለቀቀውን ውኃ ሳይቀናነስ እንድትወስድ ማረጋገጫ ቢሰጣት ያለ ማቅማማት እንደምትስማማ በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል።ግብፅ ውኃውን ከምንም ነገር አስበልጣ ስለምትፈልገው በኢትዮጵያ ግድቦች ቢገነቡና ኤሌክትሪክ በቻ እንዲመረት ቢደረግ ምንም ዓይነት ተቃውሞ አታሰማም።ለማስረጃ ያህል በጣና ሃይቅ የአባይ ወንዝ መውጪያ ላይ የተወሰነ ግድብ ተገንበቶ የጣና ውኃ መጠን እንዲጨምር ከተደረገ በኋላ በምዕራብ አቅጣጫ ጣና ተሸነቁሮ ውኃውን ቁልቁል በመልቀቅ ተርባይን እንዲያሽከረከር ተደርጎ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከተጀመረ
ቆየት ብሏል፤ የተከዜ ወንዝ ተገድቦ የተጠራቀመው ውኃ እየተለቀቀ ኤሌክትሪክ ማምረት ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል።ታዲያንስ ግብፅች የተጠራቀመ ውኃ በጣም በሚያስፈልጋቸው በድርቅ ጊዜ
ሳይቋረጥ የሚያገኙት መሆናቸውን ስለሚያውቁ ለምን በጣና ሃይቅ ኤሌክትሪክ ይመረታል፣በተከዜ ወንዝ ላይ ግድብ ተገንብቶ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ለምን ተጀመረ ጥቅማችንን ይጎዳል ብለው አልተናገሩም ፤ ተቃውምም አላሰሙም፤ ምክንያቱ ተጠቃሚዎቹ እነሱ ናቸውና።
አባይን አስመልክቶ ይህን ያህል ከተነጋገርን ስለ’’ ታላቁ የሚሊኒዮም ግድብ’’ አንዳንድ ነገር ብናነሳ መልካም ይመስለኛል።እንደተነገረን ግድቡ የሚገነባው በቤኒሻንጉል ክልል ከሱዳን ድንበር 17 ኪሎሜትር ርቀት በሚገኝ ቦታ ላይ ነው። ግድቡ 62 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ ይይዛል።የግንባታው ወጪ 80 ቢሊዮን ብር ሲሆን በኢትዮጵያ ሕዝብ መዋጮ ይሸፈናል ተብሏል።በግድቡ ውኃ ከ6ሺ በላይ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ይመነጫል።እንግዲህ ከግድቡ ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ መሆኑ ነው።ግብፅና ሱዳን ግን ተጨማሪ ውኃ ያገኛሉ። ኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት ምን ያህል ተርባይኖች እንደሚተከሉ አይታወቅም።
6000ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ ለማምረት አንዱ ተርባይን 50 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ቢሆን እንኳን ከ 100 ተርባይኖች በላይ መተከል ይኖርባቸዋል።አንዱን ተርባይን ለማሽከርከር 5 ሜትር ኩብ ውኃ በሰኮንድ መልቀቅ ያስፈልጋል ቢባል እንኳን 100 ተርባይኖችን ለማሽከርከር 500 ሜትር ኩብ ውኃ በሰኮንድ መልቀቅ ያስፈልጋል ማለት ነው። አባይ ሲሞላ በክረምት ወራት ከተጠራቀመው ውኃ
ተርባይኖችን ለማሽከርከር መልቀቅ አስፈላጊ አይሆንም። ወንዙ በግድቡ ላይ ሰለሚያልፍ እግር መንገዱን ተርባይኖቹን እያሽከረከረ ያልፋል።በግድቡ የተከማቸውን ውኃ መልቀቅ የሚያስፈልገው በበጋ ወራት አባይ ሲደርቅ ነው።ተርባይኖች ከዓመት ዓመት መሽከርከር ሰለአለባቸው ከግድብ እየተለቀቀ የሚወርደው ውኃ በቋሚነት ያስፈልጋል። በዚህ አሠራር በክረምት ወራት አባይ ሲሞላ ከሚገኘው
የውኃ መጠን የበለጠ ግብፅና ሱዳን በበጋ ወራት ያገኛሉ ማለት ነው።ይህ መጠን በተፈጥሮ ከሚያገኙት በእጅጉ ይበልጣል።በተፈጥሮ የሚያገኙት ውኃ እየቆጨን እያለ እያንዳንዱ እትዮጵያዊ
እየተመጠጠ በተሰበሰበው ገንዘብ ትልቅ ግድብ ገድበን ውኃ አጠራቅመን በተጨማሪ መስጠታችን እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የተረዳው ወይም የተገነዘበው አይመስልም።ሕዝቡ የሚመስለው ወንዙ ተገድቦ ለልማት ውሎ ከረሃብ እንደሚወጣ ነው።
በጥቅሉ አባይ ሊገደብ ነው እየተባለ ይነገረዋል።በሚገደበው ግድብ ከሚከማቸው ውኃ አንድ ሄክታር መሬት እንኳን በመስኖ እንደማይለማ አይነገረውም። ከታላቁ ግድብ ጋር ምንም የመስኖ ልማት ፕሮግራም አልተያዘም። ወደፊት ውኃውን ለልማት እናውለዋለን እንዳይባል ከግድቡ በታች ለእርሻ የሚሆን መሬት የለም። በርባራ አካባቢ ነው፤ ከዚያም ቢሆን ውኃው ተለቆ ተርባይን ከአሽከረከረ በኋላ በቀጥታ ሱዳን ውስጥ ይገባል።ምክንያቱም በሱዳን ጠረፍና በግድቡ መሐል 17 ኪሎ ሜትር ብቻ እርቀት ነው ያለው።የውኃ ጉዳይ ለግብፅ የመኖር ወይም ያለመኖር ጥያቄ ነው። ከኢትዮጵያ
የምትወጣዋን ውኃ ትቆጣጠራለች። ይህ አዲሱ ግድብ ሥራው ተጠናቆ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ውኃ መልቀቅ ከጀመረ በኋላ ውኃውን ማቆም አይቻልም።ምክንያቱም ከዓመት ዓመት የሚፈሰው ውኃ እየተለካ ይመዘገባል።
ኤሌክትሪክ ማምረት አቆማለሁ ብላ ኢትዮጵያ ብታቆም ጦርነት እንደማወጅ ተቆጥሮ በግብፅና ከሱዳን ጋር ውጊያ መግጠምን ያስከትላል።በመሆኑም ዛሬ የሐገር ፍቅር ስሜታችንን ቀስቅሰው በሚገባ ግልፅ ሳይሆንልን የግድቡን ሥራ መደገፋችን ገንዘብ ማውጣታችን ወደፊት መዘዝ ያስከትልብናል። ‘አባይ ሊያለማን ወይስ ሊያጠፋን’ ብለን መጠየቅም ይኖርብናል። ግድቡ የመስኖ ልማት
ጋር ቢያያዝ ከረሃብ ከድህነት ልንወጣ ስለምንችል ማንኛውንም ዓይነት መስዋዕትነት ሕዝብ ቢከፍል ተገቢ በሆነ ነበር፤ ከሕዝብ ጎን ጋር ያልተዛመደ ግዙፍ ሥራ መወጠኑ በኋላ አሁን ለሚደረገው የሚያስጠይቅ ሊሆን ይችላል።
የሚገርመው ደግሞ ከዚህ ድንቅ ከተባለው ግድብ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ለሱዳንና ለግብፅ ይሸጣል መባሉ ነው።የሚሸጠውም በጣም በአነስተኛ ዋጋ ነው።በአሁኑ ጊዜ ለሱዳን አንድ ኪሎዋት የሚሸጠው በስድስት ሳንቲም የአሜሪካን ሲሆን፣ሱዳን በሃገሯ እስከአሁን የምትሸጠው ሃያ ስድስት ሳንቲም የአሜሪካ ነው።በዚህ ዓይነት የ ሃያ ሳንቲም ትርፍ ታገኛለች ማለት ነው። ሱዳንና ግብፅ በውኃችን የተነሣ ጠላት አድርገውን ብዙ ጎድተውናል።ወደፊትም ይጎዱናል። ሃገራችንን ለመከፋፈልና ለመገነጠል ለተሰለፉት ዛሬ ኤርትራን ገንጥለው ለሚያስዳድሩትና የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘር በጎሣ ከፋፍለው ለሚመሩት ቡድኖች አጋር ሆነው ቆይተዋል።’አንዳንዴ የአባይ ግድብ ለነዚህ ሃገሮች ወሮታ ይሆን’ ብለው የሚጠይቁ ሃገር ወዳዶች አሉ። ታዲያ በዚህ የጠላትነት መንፈስ እየተመለከቱን እያሉ ኤሌክትሪክን ያህል የልማት ኃይል አቅራቢ ሆነን እንዲያድጉና እንዲበለጽጉ በወታደራዊ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ እንዲዳብሩ መርዳታችን እንደሆነ መገንዘብ አልቻልንም።
ኤሌክትሪክ ለጎረቤት አገሮች የመሸጥ ሐሣብ በደርግ ዘመን ተነስቶ ነበር።የጦር መሣሪያ ከማስታጠቅ አይተናነስም ተብሎ ሐሣቡ ውድቅ ተደርጎ ነበር።ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የኤሌክትሪክ ኃይል ሌሎች ወንዞች ማመንጨት ይቻላል ተብሎ፤በግልገል ግቤ በርካታ ግድቦች ተገድበው በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመረትበት ቦታ የሌለ ይመስል ታላቁ ግድብ ኤሌክትሪክ በኤሌክትሪክ ያደርገናል ችግራችን በሙሉ ይወገዳል፤እየተባለ የሚካሄደው አዳናጋሪ ፕሮፓጋንዳ ወደፊት ሃቁ መታወቁ አይቀርም።እኔ እንደምገምተው ከግብፅ ጋር ስምምነት አድርገው በጋራ የነደፉት ፕሮጀክት
ይመስለኛል።በጥናቱም ላይ የግብፅ እጅ ይኖርበታል የሚል ግምት አለኝ።የዚህ ግድብ ሥራ ግብፅን የሚጎዳ ቢሆን ኖሮ በዓለም ከፍተኛ ጩህትና የፖለቲካ ትረምስ ይሰማ ነበር። ግብፅ ያለችው ነገር ቢኖር ቴክኒካል ወረቀቶቹን ስጡኝ ነው፤ይህም ለማለት ያህል እንጂ ቴክኒካል ጥናቱ ቀድሞ በእጇ ይገኛል።
አሁን ለግብፅና ለሱዳን የሚጠቅም ሥራ ኢትዮጵያ በማንቀሳቀሷ ከዚህ በፊት በአባይ ጉዳይ ላይ አልነጋገርም፤ ስምምነትም በአዲስ መልክ አላደርግም ሲሉ የነበሩ ሁለቱ አገሮች በጉዳዩ ላይ ንደራደራለን የሚል አቋም ይዘዋል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ማውጣቱን እንዲቀጥል ብቻ አለፍ አለፍ እያሉ በለሆሳስ የግድቡ ሥራ አሳስቦናል ይላሉ። ዘለዓለማዊ የሃገር መታደግና ዕድገት ሳይሆን ዘለዓለማዊ ጠንቅ እንዳይተከልባት ለምን? ለማን? እንዴት? የሚለው የሃገር ጥቅም መለኪያ፣ሊተኮርበት ይገባል።ከራስ እያወለቁ ጠላትን እያስታጠቁ ግንባታ ስንኩል ስለሆነ አባይ መዘዝ ሳይሆን ሕዝብ አገዝ እንዲሆን ሁሉም ዕድሉ አሁን መሆኑን መገንዘብ ይገባዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢዮብ መኮንን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ

5 Comments

  1. Mr. Author, instead of looking river Abay flowing with giving nothing, it is better gaining some income from electric power with the consideration of downstream countries.,,,it is known that the construction of the dam will benefit not only ethiopia but also Sudan and Egypt………..The dam will create income of 200million euro per day and….it seems you r saying that instead of getting this much amount of income per day, starting irrigation and creating war b/n Ethiopia and Down stream countires…….don’t forget that it is international river and u can not stop the flow of the river.

  2. Are you really an Ethiopian Author ? Your writing based on furstiration and misconception of the reality on the ground.Your writing mixing with emotion and will. The dam is not our precious goal. Our goal is to claim Abay belongs to Ethiopia not Egypt. Do not forget that Egypt blocking money coming to Ethiopia from IMF that helping to construct dam on the tributary of Abay River. Ethiopia whether builds dams on Nile river or its tributary, Ethiopia cannot get loan from IMF as far as Egypt interfering .Now your political atmosphere is now changed from Muslim Activities to Abay. Because you lost the hope of coming back to power to Art kilo through Egyptian Muslim brotherhood, moreover the Muslim brotherhood is being crashed in Egypt, and the activities of Muslims in Ethiopia already has been controlled and dealt accordingly. Before I read article, I already understood what are inside the articles just opposing the dam on Nile River. How diaspora politics is full of disgustful and aimless. Please come Ethiopia when your age is 70 as sugar dad and leave the politics to the young generation. Your faulty calculation of politics you lost Ethiopia to the derg Junta by paving the ways for the Derg to kill those money precious intellectual Ethiopians in red terror in 1960s. You are still living in the faulty calculation of politics. Lol, Ethiopia is in right track. I invite you to come to Ethiopia as Sugar Dad again!!!!!

  3. Ahune gedebu megedebu yemayker mehonune setaweku lemekawem belala aktacha metachue nesuhe helena yefterlachu sew endate yehagerune lemate siyakefafa enkelfuñe ateto yadral abo lebe yestehe.

  4. You are one of egyptian writer,so I did not expect postive thinking from you.what ever it is you have to stand with your poor society.don’t forget party or leade they change it whith in time, so this dam stay fore ever.you have to think like positive .

Comments are closed.

Share