የመንግስቱ ኃይለማርያም አጃቢ “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጢሮች” የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመው በተኑ

(ዘ-ሐበሻ) ዙምባብዌ በስደት የሚገኙት የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በስማቸው የሚወጣው መጽሐፍ ቁጥር በ10ሮች የሚቆጠሩ ሲሆኑ እርሳቸው ግን አንድ መጽሐፍ ብቻ አውጥተዋል። “የመንግስቱ ትዝታዎች”። ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የፕሬዚዳንቱ የቀድሞ አጃቢ ያሳተመውና “የሌ/ኮ መንግስቱ ምስጢሮች” የተሰኘ መጽሐፍ መሰራጨቱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።
በቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም የቤተመንግስትና የሥራ ህይወት ዙሪያ እንደተጻፈ የሚነገርለት ይኸው “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጥሮች” የተሰኘው መፅሀፍ የተጻፈው የቀድሞው ልዩ ኃይል አባል እና የፕሬዝዳንት መንግስቱ አጃቢ በነበሩት እሸቱ ወንድሙ ወልደስላሴ እንደሆነ ታውቋል። ይህ መጽሐፍ ባለ 120 ገፅ እንደሆነ የገለጹት የዘሐበሻ ዘጋቢዎች የመጽሐፉ ደራሲ ለ14 ዓመታት በልዩ ጥበቃነት መስራታቸውን አስታውቀዋል። እኚሁ የቀድሞው የመንግስቱ ኃይለማርያም አጃቢ ካሁን ቀደም “ህይወት በመንግስቱ ቤተመንግስት” በሚል ርዕስ ሁለት ቅፅ መጻሕፍትን ያሳተሙ መሆኑ ይታወሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ታሰሩ

8 Comments

  1. It is clear alemu womdimu was the right hand of mengistu. that means he is the most responsible for most hidden killings . Alemu wondimu may have blood relationship with tesfaye woledeselaise.

  2. I want to completely forget about this butcher who hand over the country to the worst butcher in the history of man kind TPLF(WOYANE). Who want to spend money to read his senseless folktale.

  3. የሚገርመው ፖለቲከኞች እርስ በርሳችሁ ትንጫጫላችሁ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይሠማችሁም እንኳን የድሮ ሠዎች የሠሩት ሥህተት ሊያለያየነን አሁን እናንተም እናውቅላችጏለን በምትሉን የበሠበ ሠአስተሣሠብ አንቃረንም የትግራይም ትሁን ኦሮምያ የሲዳማም ትሁን ሀዲያ ኢትዮጵያዊ እናታችን በአዳፋ ቀሚሷ ወስጥ እናያታለን ከጉያዋ ያቀፈችው ወንድማችን ነው

  4. The book, sorry to say book, is live example to tell that all collection of papers is not book.

Comments are closed.

Share