August 18, 2013
12 mins read

እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች – ይህ ነው አቋማችን!

ከአቡ ዳኡድ ኦስማን

እኛ ኢትዬጲያያን ሙሊሞች……………………

-ከክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ጋር በሃገራችን ኢትዬጲያ ከ 1400 አመታት በላይ በሰላም፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ እየኖርን እንገኛለን፡፤ ሁላችንም የኢትዬጲ ልጆች በመሆናችን ወንድማማቾች ነን፡፡ይህን አለምን የሚያስደምመውን አብሮ ተከባብሮ እና ተረዳድቶ የመኖር ልዩ ባህላችንን የሚያደፈርሱ ማንኛውም አይነት ድርጊቶችን እንቃወማለን፡፤

-መንግስት በአሁኑ ሰአት ሙስሊሙን ማህበደሰብ ከክርስቲያኑ ማህበረሰብ ጋር ለማጋጨት እና በሌሎች ሃገሮች የምናያቸውን እና የምንሰማቸውን የእርስ በእርስ ጦርነቶች በኢትዬጲያ ምድር ለማስፈን የሚያደርገውን ከንቱ ጥረት እናወግዘዋለን፡፤እኛ ሙስሊሞች የመንግስትን በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ መግባቱን አስኪያቆም እና ህገ መንግስቱን እስኪያከበር ድረስ ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ድፍን ሁለት አመታት ሊያስቆጥር ያለው ሰላማዊ ትግላችን የማንንም ሃይማኖት ህልውና እና የማንንም የሰው መብት የማይጋፋ ስለመሆኑ በተግባር ለአለም ህዝብ ለሁለት አመታት አሳይተናል፡፤፡፤ጥያቄዎቻችንን ሶስት ግልፅ እና ቀላል የሆኑ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ብቻ ናቸው፡፡

-ኢስላማዊ መንግስት መመስረት ጥያቄያችን አይደለም፡፤ የሸሪአ መንግስት ይመስረትልን የሚል ጥያቄ በግልፅም ሆነ በድብቅ አልጠየቅንም፡፡ ህገ መንግስቱ ይከበር ጥያቄያችን ነው!!! በሃይማኖታችን ላይ መንግስት እጁን አስገብቷል በመሆኑም እጁን ከትከሻችን ላይ ያንሳልን ጥያቄያችን ነው!!! የኢትዬጲያን የቀድሞ ታሪክ እና ባህሏን የሚያውቅ ሰው ኢስላማዊ መንግስት ይመስረትልን ብሎ ጥያቄ አያቀርብም፡፡ ኢትዬጲያ የሁሉም ሃይማኖቶች ሃገር እንጂ የአንድ እምነት ተከታዬች ሃገር አይደለችም፡፤መንግስት የሃገሪቱን ህዝቦች ለማፋጀት እና ክርስቲያን ወገኖችን በሙስሊሙ ላይ በማነሳሳት እና ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች የጠየቁትን ቀላል ጥያቄዎች ሌላ ድብቅ አጀንዳ እንዳለው በማስመሰል ጥያቄዎቻችንን ለመደፍጠጥ የሚያደርገውን ከንቱ ሙከራ በፅኑ እንቃወማለን፡፡

-ህገ መንግስቱ ብዙ ሺህ ዜጎች ለነፃነት ሲሉ ደማቸውን እና አጥንታቸውን ከስክሰው ያመጡት በመሆኑ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ህገ መንግስቱ የተከፈለለትን መስዋትነት ዘንግተን ለመናድ የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡ ህገ መንግስቱን የማስከበር ግዴታ ለመንግስት ብቻ የተተወ ሳይሆን በሁሉም ዜጎች ላይ ግዴታ በመሆኑ መንግስት ህገ መንግስቱ ከወረቀት የዘለለ ሚና እንዳይኖረው እርቃኑን እያስቀረው በመሆኑ ህገ መንግስቱን የማስከበር ግዴታችንን ለመወጣት ሰላማዊ ትግል ከጀመርን እነሆ ድፍን ሁለት አመታት ሊሞላን ወራት ብቻ ይቀሩታል፡፡በህዝብ ስልጣን ሽፋን ህገ መንግስቱን ለመናድ የሚደረገውን ሩጫ እኛ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በፅፅፅፅፅኑኑኑ እንቃወማለን!!!

-የብዙሃ ሃይማኖቶች ሃገር በሆነችው ኢትዬጲያ ውስጥ ኢስላማዊ መንግስትም፣ክርስቲያናዊ መንግስትም፣ የዋቄፈታ መንግስትም ሊኖር እና ሊመሰረት እንደማይችል ጠንቅቀን እናውቃለን፡፤ይህን ደግሞ መንግስት ነግሮን ሳይሆን ንፁህ ኢትዬጲያዊ በመሆናችን ብቻ ልንረዳው የምንችለው በመሆኑ ነው፡፤ መንግስት የኢትዬጲያን ሙስሊሞች ሌላ አረብ ሃገራቶች ላይ የተፈጠረውን አይነት ሁኔታ በኢትዬጲያም ሊፈፅሙ ነው በማለት የብዝሃ ሃይማኖት ሃገር የሆነችውን ኢትዬጲያን በሃሰት ፕሮፖጋንዳ ለማሸበር የሚያደርገውን ጥረት ማቆም ይገባል ብለን እናምናለን፡፡ስለ ኢትዬጲያ ሙስሊሞች ማንነት ከመንግስት በበለጠ መልኩ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች በደንብ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፤ በመሆኑም የመንግስት ተራ ወሬ እና ዛዛታ ህዝብን ከማደንቆር ሌላ የሚያተረፈው እንዳችም ትርፍ እንደማይኖረው በፅኑ እናምናለን፡፤

-በማንኛውም ሃይማኖቶች ውስጥ የሚኖረውን አክራሪነት እና ፅንፈኝነትን እንቃወማለን፡፡አክራሪነት እና ፅንፈኝነትን የምንቃወመው ህግ እንዳይጣስ ብቻ ብለን ሳይሆን በቅድሚያ የምንከተለው ሃይማኖታችን ኢስላም ከአክራሪነትን እና ከፅንፈኝነትን እንድንርቅ ስላስተማረን ነው፡፤ የኢትዬጲያ ህገ መንግስት አክራሪነትን እና ፅንፈኝነትን ቢፈቅድ እንኳን እኛ ሙስሊሞች አንቀበለውም፡፡ ምክንያቱን ኢስላም በሁሉም ነገራቶች ላይ በእምነታችን ላይ ፣ በአምልኮ ላይ ፣በስራ ላይ ፣በማህበራዊ ኑሮ ላይ ፣በአስተሳሰባችን ላይ ሚዛናዊ እና መካከለኛ እንድንሆን ስላዘዘን ነው፡፤

– በኢስላም ውስጥም ሆነ በክርስተና ሃይማኖቶች ውስጥ በሚፈጠሩ የአክራሪነት እና የፅንፈኝነት ዝንባሌዎች በሃይማኖት ስም ጥቂት የሃይማኖቱ ተከታይ ፅንፈኞች የሚፈፅሙትን ጥፋቶች ሁላችንም እናወግዛለን፡፡ ከሃይማኖቱ ተከታዮች መካከል እፍኝ የማይሞሉ ሰዎች በተጠናወታቸው ፅንፈኝነት ተገፋፍተው በሚፈፅሙት ወንጀል እና ጥፋት ሁሉም የእምነቱ ተከታዬችን በጅምላ የጥፋቱ አካል አድርጎ መፈረጅ ተገቢ ስላልሆነ አንቀበለውም፡፡

-በጥቂት ሰዎች የሚፈጸመውን ቤተ አምልኮዎችን ማቃጠል፣ቤተ አምልኮዎችን ማፍረስ፣ገዳማትን መድፈር፣የሃይማኖት አባቶችን እና ቀሳውስቶችን መግደል ኢስላም በጥብቅ የሚያወግዘው ተግባር በመሆኑ ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ ይህን ተግባር ያወግዘዋል፡፡ ኢስላም በሰላም ጊዜ ብቻ ሳይሆን በጦርነት ጊዜ እንኳን ቤተ አምልኮዎችን ማቃጠል፣ገዳማትን መድፈር፣የሓይማኖት አባቶች ላይ ጥቃት ማድረስ፣ሴቶችን እና ህፃናትን መግደል አንዲሁም እንስሳትን ያለአግባብ መግደል እና ፣ዛፎችን ያለ አግባብ መቁረጥን በጥብቅ ይከለክለናል፡፡ በመሆኑም እኛም ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በሃገራችን ውስጥ በጥቂት ፅንፈኞች እንዲሁም በጸብ አጫሪ ድርጊቶች ላይ ቁጣን መቆጣጠር ባለመቻል የሚፈጸሙ እና ሆን ተብሎ ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን ለማጋጨት በመንግስት የሚፈጸሙ ቤተ አምልኮዎችን ማለትም ቤተ ክርስቲያናትን እና መስጂደችን የማቃጠል እና የማፍረስ ድርጊት በፅኑ እናወግዛለን፡፤ለምሳሌ በሃገራችን ኢትዬጲያ ከአመታት በፊት በጅማ ከተማ በሁለቱም ወገኖች የተፈፀመውን ጥፋቶች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የተፈጸሙትን የቤተክርስትያን ቃጠሎ እና በጉራጌ ዞን የተፈጸመውን የጅምላ መስጂዶች ቃጠሎ ጥፋቶች ከላይ በጠቀስናቸው ምክንያቶች የተፈጸሙ በመሆናቸው የምናወግዘው ሲሆን ድርጊቱም የሚወክለው የድርጊቱን ፈፃሚ ግለሰቦች እንጂ ሌላውን የእምነቱ ተከታዬች አለመሆኑን እናምናለን፡፤፡በመሆኑም መስጂድንም ሆነ ቤተክርስቲያኖችን የሚያቃጥሉ ሰዎች በሃይማኖታዊም ሆነ በህግ ደረጃ ወንጀለኞች በመሆናቸው ተገቢውን ክትትል ተደርጎ ሊቀጡ ይገባል ስንል እናምናለን፡፤

-ሆን ተብሎ የእምነት ምፅሃፍቶችን ቅዲስ ቁርአንን እና መፀሃፍ ቅዱስን መቅደድ፣ማቃጠል እና ለሽንት ቤት አገልግሎት ተግባር ማዋልን እንቃወማለን፡፡ይህ ድርጊት በብዛት የሚፈፀመው ፅንፈኛ አስተሳሰብ ባላቸው ግለሰቦች እና የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የሁለቱን እምነቶች ለማጋጨት በማሰብ በመንግስት ሃይሎች የሚፈጸም በመሆኑ በዚህ መሰሉ ጸረ ሃይማኖት ወንጀል ላይ የሚሳተፉ አካላት ተገቢው እርምጃ ይወሰድባቸው ዘንድ አቋማችን ነው፡፤

አላህ ለሃገራችን ኢትዬጲያ ሰላም፣ፍቅር እና ብልፅግናን እንዲለግሳት እንማፀነዋለን!!!

አሚን!!!

abunapauolos1
Previous Story

ለአቡነ ጳውሎስ የመቃብር የነሐስ ሐውልት የተመደበው 1.5 ሚልዮን ብር ነው

Next Story

ዓባይ ሊያለማን ወይስ ሊያጠፋን? – የሕዳሴው ግድብና ዐባይ፣ የሚሊኒየሙ ዐባይ ተጋቦት

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop