የደም እንጀራ

ከቴድሮስ ሐይሌ(TADYHA@GMAIL.COM)
‘’የጤፍ መወደደድ ምክንያቱ ቀድሞ ሊመገብ የማይችለው አርሶ አደር እንጀራ መብላት በመጀመሩ ነው’’ በማለት የተናገረው የሙት ራዕይ ለማስፈጸም ሽር ጉድ እያለ የሚገኘው የከተማ ልጆች በቁሙ የሞተ ሲሉ የሚሳለቁበት ሃይለማርያም ደሳለኝ ፓርላማ ለተባለው የወያኔው አውጫጭኝ የቀድሞ አለቃው መለስ ዜናዊ ስኳርን በተመለከተ በአንድ ወቅት የተናገረውን ምንም ሳይገለበጥ ለጤፍም ችግር መመለሱን ባለፈው ሰሞን ሰምተናል።
መጽሃፉ ሙታንን ለሙታን ተዋቸው እንዲል የበድን ጣዖት አምላኪ ወያኔና ጭፍሮቹን ለግዜው እንተዋቸውና ይህንን የሕገ አራዊት አገዛዝ እታገላለሁ የሚለውና በሃገሩ የመኖር ነጻነት አጥቶ የተሰደደው በተለይም በምዕራቡ ሃገራት የሚኖረው ኢትዮጽያዊ ዲያስፖራ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀጥታ በሃገር ውስጥ ያለውን ደሃ ወገኑ ላይ ከባድ የኑሮ ክብደት ጫና ሲፈጥር በአንጻሩ የወያኔውን አገዛዝ በውጭ ምንዛሪ እየደጎመ ጥቂት የአገዛዙ ግብርአበር ነጋዴዎችን ኪስ ሲያደልብ ከምናስተውልባቸው የንግድ ዘርፎች ውስጥ ከሃገር ቤት በቀጥታ በአይሮፕላን ተጭኖ ለንግድ የሚቀርበው የእንጀራ መጠን ከቀን ወደቀን እየደገ መምጣቱ ማየት ካስፈለገ በየሃበሻው ሱቅ ያለውን አቅርቦት መታዘብ በቂ ነው።
እድሜ ለዲያስፖራ ፤ መብላት አልቻልንም እንጀራ! ሲሉ አምርረው በውጭ ሃገር ያለንውን የሚወቅሱ ወገኖች መኖራቸውን በቅርቡ ወደ ሃገር ቤት ተጉዞ የነበረ ወዳጄ አጫውቶኛል። ከቅርብ ግዜያት ወዲህ የጤፍ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቶ ከገበያ እስከ መጥፋትና ዋጋው በየእለቱ እየጨመረ በመሄዱ እንጀራ መመገብ ለከተሜው ነዋሪ ወደዓለመቻል ደርሶዋል ። እስከዚህ የጭለማ ዘመን ድረስ በከተማ ይሁን በገጠር ሃብታም ይሁን ደሃ በማባያውና በቀለሙ አይነት ይለያይ እንጂ እንጀራ በመመገብ እኩል ነበር ። ለጤፍ እንዲህ እጅግ መናር ዋነኛ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ወደ ተለያዩ ሃገሮች በጥሬው ኤክስፖርት የሚደረገውን ሳይጨም ወደ ሰሜን አሜሪካ ብቻ የተጋገረው እንጀራ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ አንዱና ከፍተኛው የጤፍ መወደድ ምክንያቱ እንደሆነ ከላይ እንደሰፈረው ቃላት አዋዝተው በግልጽ የሚናገሩ ሰዎች ወዳጄን ገጥመውታል።
እድሜ ለዲያስፖራ ፤ መብላት አልቻልንም እንጀራ! ሲሉ አምርረው በውጭ ሃገር ያለንውን የሚወቅሱ ወገኖች መኖራቸውን በቅርቡ ወደ ሃገር ቤት ተጉዞ የነበረ ወዳጄ አጫውቶኛል። ከቅርብ ግዜያት ወዲህ የጤፍ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቶ ከገበያ እስከ መጥፋትና ዋጋው በየእለቱ እየጨመረ በመሄዱ እንጀራ መመገብ ለከተሜው ነዋሪ ወደዓለመቻል ደርሶዋል ። እስከዚህ የጭለማ ዘመን ድረስ በከተማ ይሁን በገጠር ሃብታም ይሁን ደሃ በማባያውና በቀለሙ አይነት ይለያይ እንጂ እንጀራ በመመገብ እኩል ነበር ። ለጤፍ እንዲህ እጅግ መናር ዋነኛ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ወደ ተለያዩ ሃገሮች በጥሬው ኤክስፖርት የሚደረገውን ሳይጨም ወደ ሰሜን አሜሪካ ብቻ የተጋገረው እንጀራ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ አንዱና ከፍተኛው የጤፍ መወደድ ምክንያቱ እንደሆነ ከላይ እንደሰፈረው ቃላት አዋዝተው በግልጽ የሚናገሩ ሰዎች ወዳጄን ገጥመውታል።
ይህው ወዳጄ በሃገር ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት በተለይ በምግብ ላይ በየግዜው እየጨመረ ያለው የገንዘብ መጠን ለአብዛኛው ከተሜ ሠርቶ አደር ህብረተሰብ ክፍል የሚያነገደግድ እየሆነ መምጣቱን ተዘዋውሮ ከተመለከተበት አጋጣሚ ውስጥ የመጨረሻ ሊባል ከሚችል የታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ከሚስተናገድባቸው የመንደር ምግብ ቤት በአንዱ ያለውን ሜኑ ፎቶ አንስቶ የአደረሰሽኝ መረጃ የዛሬ አምስት አመት ሁለትና ሦስት ብር የነበረ አንድ ተራ ራሃብ መክሊያ ቁርስ ሰባት እጥፍ ዋጋ ጨምሮ መገኘቱ የወገናችንን ኑሮ ምን ያህል የከፋ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። አበው ‘’ እርስ በእርሱ ስጋን በኩበት ጠበሱ’’ እንዲሉ ለወገናችን መራብ በማወቅም ይሁን በአለማወቅ በዲያስፖራ ያለንው አስተዋጽዖ እንዲህ የሚታይና የሚጨበጥበት ደረጃ ከደረሰ መነጋገሩ የሚበጅ ከመሆኑም በላይ በታሪክም በእግዚያብሄርም የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ከህዝባችን አፍ ተነጥቆ ያውም በውድ ዋጋ የቀረበልንን የደም እንጀራ ባለመግዛት ልንተባበር ግድ ይለናል። በእርግጥ ማንም ከትውልድ ሃገሩ የሚመጣለትን ቁሳቁስና ምግብ መግዛትና መጠቀሙ ሊያስገኝ ከሚችለው የመንፈስ እርካታ ባሻገር ሊፈጥር የሚችለው ኢኮኖሚያዊ አቅም ለሃገር እድገት የሚኖረው አንድምታ ቀላል አለመሆኑ ለማንም የሚሳት ባይሆንም እንደኛ ሃገር ለዜጎቹ ክብርና ደንታ በሌለው ሕገ አራዊት አገዛዝ ወገናችንን ደፍጥጦ ባለበት ሁኔታ እድገትን ማፋጠን ሳይሆን መከራን ማርዘም በመሆኑ በገንዘባችን ወገናችንን ጎድተን ጎጂዎቹንም ማጠናከራችንን ልንረደውና ልናቆመው ይገባል።
በዚህ የትዝብት መጣጥፍ ማስረገጥ የምፈልገው በኢኮኖሚ ዕቀባ አገዛዙን ስለመታገል ብቻ አይደለም ይህ ሃሳብ በተለያየ ጫፍ ሊያቆመን ይችላል ፥ ነገር ግን በሰብዓዊነት አንጻር እንድንመለከተው ይበልጥ ለመጋበዝ ነው በአሁኒቷ ኢትዮጽያ ባለው የኑሮ ውድነት ወገናችን የእለት ጉርሱን ቀምሶ መዋል ያልቻለበት ልጆቹን በፈረቃ ለመመገብ የተገደደበት ህጻናት በምግብ እጥረት ትምህርታቸውን መከታተል እየተሳናቸው በጠኔ ሲወድቁ የታየበት ሕዝባዊ ውርደትና ሃገራዊ ውድቀት ላይ በደረስንበት ሁኔታ ውስጥ ከዚህ አሳፋሪና አዋረጅ ሁኔታ ለመላቀቅ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ በመታገል ከተጫነን የድህነትና የሽብር አገዛዝ ለመገላገል የሚያስችለንን ትግል በጋራ ማከናወን ለግዜው ባንችልም ወገናችንን ከሚጎዳ አጉል ደርጊት ራሳችንን በመቆጠብ ያውም አማራጭ ባልጠፋበት የሚኖረው ዲያስፖራ ከተራበ ወገኑ አፍ እየተቀማ በውድ ዋጋ የሚቀርብለትን የደም እንጀራ ባለመግዛት አቋም ሊጸና ይገባል።
ወራቱ የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወቅት ነው የነማርቲን ሉተር ሰማዕትነት የሚታሰብበት የሮዛ ፓርክ በሰላማዊ ትግል የዘረኛ ነጮች የትራንስፖርት ኩባንያ በኪሳራ እንዲሽመደመድ የተደረገበት ጥቁር ወንድሞቻችን አማራጫቸው እጅግ በጠበበበት ሁኔታ ውስጥ እንኳ ሆነው በአንድነትና በጽናት ቆመው ከነርሱ አልፎ ለኛም በተረፈው የነጻነት አገር እየኖርን ሃገርና ወገንን ከሚጎዳ ተግባር ቢያንስ እራሰችንን ማቀብ እየተሳነን ለብዙ ጉዳት ተዳርገናል፤ ጎበዝ ከተቆራኘን ግለኝነትና ምንቸገረኝነት ልንላቀቅ ይገባል ዋጋ ባልከፈልንበት ቅንጣት አስተዋጽዖ ባለረግንበት በአያሌ የሲቪል ራይት ሰማዕታት በተቀዳጀነው የነጻነት ዓለም ውስጥ ምቾትና ሰላማችን ተጠብቆ ብንኖርም ሃገራችንን ልናስብ ስለወገናችን ድምጻችንን ልናሰማ ግድ ሊለን ይገባል
እግዚያብሔር ሃገራችንን ይጠብቅልን !!!
አሜን!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎጃም ክልል ይመስረት - ከይገርማል

3 Comments

  1. do you think that diasporas haven’t a right to eat injera?

    read the principle of “the survival of the fittest”

    • Jallo,read the article properly he is not talking about provoke diaspora right not to eat Enjera of course we have right to eat but all Ethiopian people have a problem to feed them well because woyane ship out Enjera under the name of Ethiopian comiunity stores to north America in this case they will get a big forgien exchange so they will keep them self on power for a long time this is what we call it boy cote so join the program not to bay Ethiopian Enjera.by the way it is a very good article good work.

Comments are closed.

Share