መንጋውን ጠባቂ አርጎ ሰይሟችሁ
ዋ ለ እናንተ ይብላኝ በቃል ለጠፋችሁ
የነብስን አደራ ሜዳ ስትበትኑ
ጠባቂ በማጣት መምህናን ማስኑ ፤
ተኩላ ሲናጠቀው የጌታውን መንጋ
ስይሙን እረስቶ ስለተዘናጋ
አቤት ይብላኝለት ለሚከፈለው ዋጋ
መሆኑን ረስቶት ፈራሽበስባሽ ስጋ
በ አምላክ ስም ነግዶ ሸቅጦ መክበሩ
በከለ ተጠቅልሎ ሲታሹ ቢኖሩ
በ ቆብ ተከልለው ቢቆሙም ከጥሩ
አቡን መሰኝቱ በ አባ መከበሩ
መኖር ከመረጡ እያጭበረበሩ
ለ ሞቱለት ዓለም ዳግም ነብስ ከዘሩ
መንፈሳዊን ስራ እስካልተገበሩ
ውርደት እንደው አይቀር ምን ቢሽቀረቀሩ ፤
እስኪ ቆም በላችሁ ስራችሁን አስተወሉ
ምን ነበር ያላችሁ ፈጣሪ በቃሉ ??
ጥቦቴን አደራ በጎቼን አደራ
ትወዱኝ እንደሆን ዳግም እስክጣራ
በሎ ሲሰጣችኹ እኛን አድርጎ ምርኮ
ኀርአያ እንድትሆኑን መካር እንድትሆኑን የሾማችኹ እኮ
አደራውን በጁእንድታስረክቡት
ከ ተኩላ መንጋ እንደትታደጉት
በሰጣችሁ መክሊት ብዙ እንደታፈሩ
በ ወይንግንድ አምሳል እንዲያ እስክትጠሩ
ወዶ አቅርቧችሁ እምነትን ሰጥቷችኹ
ከ ሰጣችሁ ክብር ለምንጎደላችኹ ??
አላምር ስላለች ወይኑ ፍሬ አጥታ
መፅደቅ ቢገርባት ግንድ ሆና ቀርታ
ጌታዋ ተናዶ ቢሰኝም ቁረጣት
አገልጋዩ ለምኖ በ ፋንድያ አርሷት
አንድ ዕድል ለምኖ ለማፍሪያ ችሮታ
ዳግም እንደቆመች ለ ዓመት ጊዜ አግኝታ
እንአንተም ዝቅ በሉ ውደቁ ለምኑ
በንስሃ ከብራችሁ ዳግም እንድትፀኑ
ዐመፅ መለያየት የናንተ አይሁኑ
እናንትተ ፈርሳችሁ እዝቡን አትበትኑ
ይልቅ ዝቅ በሉ መተለቅ ካሻችኹ
አምላክን ምስሉት ፍጹም በልባችኹ
በባዶ መሰቀል ስለማይጠቅማችኹ
እስኪ እግር ያዙ እንደ ፈጣሪያችኹ
…………………^………………
እሱ እግር ያጠበው የዚን ተራ ፈጥረት
እኛ እንድንኖረው ነው እንድንከብርበት
…………………….//…………………..
ተጻፈ በ ፭ ፪ሺ፭ ዓም
ሴካ